Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፀአት 15:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በቸ​ር​ነ​ትህ የተ​ቤ​ዠ​ሃ​ቸ​ውን ሕዝ​ብ​ህን መራህ፤ በኀ​ይ​ልህ ወደ ቅዱስ ማደ​ሪ​ያህ ጠራ​ሃ​ቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በማይለወጠው ፍቅርህ፣ የተቤዠሃቸው ሕዝብህን ትመራለህ፤ እነርሱን በብርታትህ፣ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ ትመራቸዋለህ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በታማኝ ኪዳንህ የተቤዠሃቸውን ሕዝብህን መራሃቸው፤ በኃይልህ ወደ ቅድስናህ ማደሪያ አስገባሃቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በማይለወጥ ፍቅርህ ያዳንካቸውን ሕዝብ መራህ፤ በብርታትህም ወደ ተቀደሰችው ምድር እንዲገቡ አደረግህ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በቸርነትህ የተቤዠሃቸውን ሕዝብህን መራህ፤ በኃይልህ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ አገባሃቸው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፀአት 15:13
21 Referências Cruzadas  

እር​ሱም በዘ​ገየ ጊዜ እነ​ዚያ መላ​እ​ክት የእ​ር​ሱን እጅ፥ የሚ​ስ​ቱ​ንም እጅ፥ የሁ​ለ​ቱን ሴቶች ልጆ​ቹ​ንም እጅ ይዘው አወ​ጡ​አ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራር​ቶ​ላ​ቸ​ዋ​ልና።


ንጉ​ሡም ሳዶ​ቅን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወደ ከተማ መልስ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይን ሞገስ አግ​ኝቼ እንደ ሆንሁ፥ መልሶ እር​ሷ​ንና ክብ​ሯን ያሳ​የ​ኛል፤


የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መን​ገድ ታበ​ራ​ላ​ቸው ዘንድ ቀን በደ​መና ዐምድ፥ ሌሊ​ትም በእ​ሳት ዐምድ መራ​ሃ​ቸው።


የተ​ራ​በ​ችን ነፍስ አጥ​ግ​ቦ​አ​ልና፥ የተ​ራ​ቈ​ተ​ች​ንም ነፍስ በበ​ረ​ከት ሞል​ቶ​አ​ልና።


ጊዜ​ውን ባገ​ኘሁ ጊዜ እኔ በቅን እፈ​ር​ዳ​ለሁ።


ዓለ​ቱን ይመታ ዘንድ ውኃ​ንም ያፈስ ዘንድ ይች​ላ​ልን? እን​ጀ​ራን መስ​ጠ​ትና ለሕ​ዝ​ቡስ ማዕ​ድን መሥ​ራት ይች​ላ​ልን?”


በረ​ዳ​ታ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፥ ለያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እልል በሉ።


ፍር​ሀ​ትና ድን​ጋጤ ወደ​ቀ​ባ​ቸው፤ የክ​ን​ድህ ብር​ታ​ትም ከድ​ን​ጋይ ይልቅ ጸና፤ አቤቱ፥ ሕዝ​ብህ እስ​ኪ​ያ​ልፉ ድረስ፥ የተ​ቤ​ዠ​ሃ​ቸው እኒህ ሕዝ​ብህ እስ​ኪ​ያ​ልፉ ድረስ፤


አቤቱ፥ አንተ ታስ​ገ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ በመ​መ​ስ​ገ​ኛህ ተራ​ራም ትተ​ክ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ፤ አቤቱ፥ ለማ​ደ​ሪ​ያህ ባደ​ረ​ግ​ኸው ስፍራ፥ አቤቱ፥ እጆ​ችህ ባዘ​ጋ​ጁት መቅ​ደስ፤


“ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ያወ​ጣ​ሁህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ እኔ ነኝ፤


ስለ​ዚ​ህም ፈጥ​ነህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ በላ​ቸው፥ “እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ተገ​ዥ​ነት አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከባ​ር​ነ​ታ​ቸ​ውም አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ በተ​ዘ​ረጋ ክንድ፤ በታ​ላቅ ፍር​ድም እታ​ደ​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤


ባሕ​ሩን ያደ​ረ​ቅሽ፥ ጥል​ቁ​ንም ውኃ ያደ​ረ​ቅ​ሽው፥ የዳ​ኑ​ትም ይሻ​ገሩ ዘንድ ጥል​ቁን ባሕር ጥር​ጊያ ጎዳና ያደ​ረ​ግሽ አይ​ደ​ለ​ሽ​ምን?


ለዘ​ለ​ዓ​ለም በአ​ር​ያም የሚ​ኖር ስሙም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን የሆነ፥ በቅ​ዱ​ሳን አድሮ የሚ​ኖር፥ ለተ​ዋ​ረ​ዱት ትዕ​ግ​ሥ​ትን የሚ​ሰጥ፥ ልባ​ቸ​ውም ለተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ሕይ​ወ​ትን የሚ​ሰጥ ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦


በመ​ል​እ​ክ​ተ​ኛም አይ​ደ​ለም፤ በመ​ል​አ​ክም አይ​ደ​ለም፤ እርሱ ራሱ ያድ​ና​ቸ​ዋል እንጂ። እርሱ ይወ​ዳ​ቸ​ዋ​ልና፥ ይራ​ራ​ላ​ቸ​ዋ​ል​ምና እርሱ ተቤ​ዣ​ቸው፤ ተቀ​በ​ላ​ቸ​ውም፤ በዘ​መ​ና​ቸ​ውም ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አከ​በ​ራ​ቸው።


እነ​ር​ሱም፥ “ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣን፥ በም​ድረ በዳና በባ​ድማ፥ ዕን​ጨ​ትና ውኃ፥ የእ​ን​ጨት ፍሬም በሌ​ለ​በት ምድር፥ ሰው በማ​ያ​ል​ፍ​በ​ትና የሰው ልጅም በማ​ይ​ቀ​መ​ጥ​በት ምድር የመ​ራን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዴት አለ? አላ​ሉም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በም​ሕ​ረቱ ባለ​ጸ​ግ​ነ​ትና በወ​ደ​ደን በፍ​ቅሩ ብዛት፥


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios