Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፀአት 14:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ውኃ​ውም ተመ​ልሶ በኋ​ላ​ቸው ወደ ባሕር የገ​ቡ​ትን ሰረ​ገ​ሎ​ችን፥ ፈረ​ሰ​ኞ​ች​ንም፥ የፈ​ር​ዖ​ን​ንም ሠራ​ዊት ሁሉ ከደነ፤ ከመ​ጡ​ትም ሁሉ አንድ ስንኳ የቀረ የለም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ውሃውም ተመልሶ እስራኤላውያንን ተከትለው ወደ ባሕሩ የገቡትን ሠረገሎች፣ ፈረሰኞች፣ መላውን የፈርዖን ሰራዊት ሁሉ ሸፈነ። አንድም እንኳ አልተረፈም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ውኆቹም ተመልሰው በኋላቸው ወደ ባሕር የገቡትን ሰረገሎችን ፈረሰኞችን የፈርዖንንም ሠራዊት ሁሉ ከደኑ፤ ከእነርሱም አንድ ስንኳ አልቀረም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ውሃውም ተመልሶ እስራኤላውያንን ይከተሉ የነበሩትን ሠረገሎችን፥ ፈረሰኞችንና መላውን የግብጽ ሠራዊት ሸፈነ፤ ከእነርሱ አንድ ሰው እንኳ አልተረፈም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ውኃውም ተመልሶ በኋላቸው ወደ ባሕር የገቡትን ሰረገሎችን፥ ፈረሰኞችንም፥ የፈርዖንንም ሠራዊት ሁሉ ከደነ፤ ከእነርሱም አንድ ስንኳ አልተረፈም።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፀአት 14:28
16 Referências Cruzadas  

ሰረ​ገ​ሎ​ችም፥ ፈረ​ሰ​ኞ​ችም ከእ​ርሱ ጋር ወጡ፤ ሠራ​ዊ​ቱም ብዙ ነበር።


ውኃ​ውም አሸ​ነፈ፤ በም​ድር ላይም እጅግ በዛ፤ መር​ከ​ቢ​ቱም በውኃ ላይ ተን​ሳ​ፈ​ፈች።


የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ወደ ምድረ በዳው መጠ​በ​ቂያ ግንብ በመጡ ጊዜ ሕዝ​ቡን አዩ፤ እነ​ሆም፥ በም​ድሩ ሁሉ ሬሳ ሞልቶ ነበር፤ ያመ​ለ​ጠም ሰው አል​ነ​በ​ረም።


ከፊ​ታ​ቸ​ውም ባሕ​ሩን ከፈ​ልህ፤ በባ​ሕ​ሩም መካ​ከል በደ​ረቅ ዐለፉ፤ የተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውን ግን ድን​ጋይ በጥ​ልቅ ውኃ እን​ዲ​ጣል በቀ​ላይ ውስጥ ጣል​ሃ​ቸው።


የም​ስ​ጋና መሥ​ዋ​ዕ​ትም ይሠ​ዉ​ለት፥ በደ​ስ​ታም ሥራ​ውን ይን​ገሩ።


ሙሴም ለሕ​ዝቡ፥ “አት​ፍሩ፤ ዛሬ የም​ታ​ዩ​አ​ቸ​ውን ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አታ​ዩ​አ​ቸ​ው​ምና ቁሙ፤ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማዳን እዩ።


ነፋ​ስ​ህን ላክህ፤ ባሕ​ርም ከደ​ና​ቸው፤ በብዙ ውኆች ውስጥ እንደ አረር ሰጠሙ።


“የፈ​ር​ዖን ፈረ​ሶች ከሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹና ከፈ​ረ​ሰ​ኞቹ ጋር ወደ ባሕር ገቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የባ​ሕ​ሩን ውኆች መለ​ሰ​ባ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን በባ​ሕሩ መካ​ከል በየ​ብስ አለፉ፤ ውኃ​ውም ለእ​ነ​ርሱ በቀኝ እንደ ግድ​ግዳ፥ በግ​ራም እንደ ግድ​ግዳ ሆነ​ላ​ቸው።”


ሕዝብህን ለመታደግ፥ የቀባኸውንም ለማዳን ወጣህ፣ የኃጢአተኛውን ቤት ራስ ቀጠቀጥህ፣ መሠረቱን እስከ አንገቱ ድረስ ገለጥህ።


በተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ች​ሁም ጊዜ በኤ​ር​ትራ ባሕር ውኃ እን​ዳ​ሰ​ጠ​ማ​ቸው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስከ ዛሬ ድረስ እን​ዳ​ጠ​ፋ​ቸው፥ በግ​ብፅ ጭፍራ በፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም፥ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም ያደ​ረ​ገ​ውን፥


በደ​ረቅ ምድር እንደ መሄድ የኤ​ር​ት​ራን ባሕር በእ​ም​ነት ተሻ​ገ​ሩ​አት፤ የግ​ብፅ ሰዎች ግን ሲሞ​ክሩ ሰጠሙ።


ባር​ቅም ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ሠራ​ዊ​ቱን እስከ አሕ​ዛብ አሪ​ሶት ድረስ አባ​ረረ፤ የሲ​ሣ​ራም ሠራ​ዊት ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት ወደቀ፤ አንድ እንኳ አል​ቀ​ረም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios