Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፀአት 14:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በም​ድረ በዳ ከም​ን​ሞት ብን​ገ​ዛ​ላ​ቸው ይሻ​ለ​ና​ልና፦ ‘ተወን፤ ለግ​ብ​ፃ​ው​ያን እን​ገዛ’ ብለን በግ​ብፅ ሳለን ያል​ንህ ቃል ይህ አይ​ደ​ለ​ምን?”

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በግብጽ ሳለን፣ ‘ተወን እባክህ፤ ግብጻውያንን እናገልግል’ አላልንህም ነበርን? በምድረ በዳ ከምንሞት ግብጻውያንን ብናገለግል ይሻል ነበር!”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በግብጽ ሳለን ያልንህ ቃል ይህ አይደለምን? ተወን፥ ግብፃውያንን እናገልግል፤ በምድረ በዳ ከምንሞት ብናገለግላቸው ይሻላልና።”

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ይህ ሁሉ እንደሚሆን ገና ከዚያ ሳንወጣ ነግረንህ አልነበረምን? እንዲያውም ‘እባክህ ተወን፥ ለግብጻውያን ባርያዎች ሆነን እናገልግል’ ብለንህ ነበር፤ በእርግጥም በዚህ በረሓ ከመሞት፥ በዚያ ባርያዎች ሆነን መኖር በተሻለን ነበር።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ‘በምድረ በዳ ከምንሞት ብንገዛላቸው ይሻላልና ተወን፤ ለግብፃውያን እንገዛ’ ብለን በግብፅ ሳለን ያልንህ ቃል ይህ አይደለምን?” አሉት።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፀአት 14:12
11 Referências Cruzadas  

ወደ​ሚ​ኖ​ሩ​በ​ትም ሀገር ይሄዱ ዘንድ የቀና መን​ገ​ድን መራ​ቸው።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ፈር​ዖን ሕዝ​ቡን በለ​ቀቀ ጊዜ፥ ምንም ቅርብ ቢሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ምድር መን​ገድ አል​መ​ራ​ቸ​ውም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ሕዝቡ ሰል​ፉን በአየ ጊዜ እን​ዳ​ይ​ጸ​ጽ​ተው፥ ወደ ግብ​ፅም እን​ዳ​ይ​መ​ለስ” ብሎ​አ​ልና።


አሁ​ንም እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጩኸት ወደ እኔ ደረሰ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ባ​ቸ​ውን ግፍ ደግሞ አየሁ።


እነ​ር​ሱም፥ “በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ፊት ሽታ​ች​ንን አግ​ም​ታ​ች​ሁ​ታ​ልና፥ ይገ​ድ​ለ​ንም ዘንድ ሰይ​ፍን በእጁ ሰጥ​ታ​ች​ሁ​ታ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ል​ከ​ታ​ችሁ፤ ይፍ​ረ​ድ​ባ​ች​ሁም” አሉ​አ​ቸው።


ሙሴም ይህን ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተና​ገረ፤ እነ​ርሱ ግን ከሰ​ው​ነ​ታ​ቸው መጨ​ነቅ፥ ከሥ​ራ​ቸ​ውም ክብ​ደት የተ​ነሣ ቃሉን አል​ሰ​ሙ​ትም።


እን​ዲ​ሁም ኤፍ​ሬም ከጣ​ዖ​ታት ጋር ተጋ​ጠመ፤ ለራ​ሱም ዕን​ቅ​ፋ​ትን አኖረ።


አሁ​ንም አቤቱ! ከሕ​ይ​ወት ሞት ይሻ​ለ​ኛ​ልና እባ​ክህ! ነፍ​ሴን ከእኔ ውሰድ።”


ፀሐ​ይም በወ​ጣች ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትኩስ የም​ሥ​ራቅ ነፋ​ስን አዘዘ፤ ዮና​ስ​ንም እስ​ኪ​ዝል ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለራ​ሱም ተስፋ ቈርጦ፥ “ከሕ​ይ​ወት ሞት ይሻ​ለ​ኛል” አለ።


እርሱም “የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደ ሆንህ አውቄአለሁ! የእግዚአብሔር ቅዱሱ!” ብሎ ጮኸ።


በታላቅ ድምፅም እየጮኸ “የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለኝ? እንዳታሠቃየኝ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤” አለ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios