Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፀአት 14:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ሙሴ​ንም አሉት፥ “በግ​ብፅ መቃ​ብር ስላ​ል​ኖረ በም​ድረ በዳ እን​ሞት ዘንድ አወ​ጣ​ኸን? ከግ​ብፅ ታወ​ጣን ዘንድ ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ምን​ድን ነው?

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እነርሱም ሙሴን እንዲህ አሉት፤ “በምድረ በዳ እንድንሞት ያመጣኸን በግብጽ መቃብር ቦታ ጠፍቶ ነውን? ከግብጽ አውጥተህ ምን አደረግህልን?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሙሴንም እንዲህ አሉት፦ “በግብጽ መቃብር ስለ ሌለ ነው በምድረ በዳ እንድንሞት ያወጣኸን? ከግብጽ አውጥተህ ምንድነው ያደረግህብን?

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሙሴንም እንዲህ አሉት፦ “ከቶ በግብጽ የመቃብር ቦታ አልነበረምን? ታዲያ በዚህ በረሓ እንድንሞት ያመጣኸን ለምንድን ነው? ከግብጽ አውጥተኸን ምን እንደ ደረሰብን እስቲ ተመልከት!

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሙሴንም “በግብፅ መቃብር ስላልኖረ በምድረ በዳ እንሞት ዘንድ አወጣኸንን? ከግብፅ ታወጣን ዘንድ ይህ ያደረግህብን ምንድር ነው?

Ver Capítulo Cópia de




ዘፀአት 14:11
14 Referências Cruzadas  

እስ​ራ​ኤ​ልም አላ​ቸው፥ “በእኔ ላይ ያደ​ረ​ጋ​ች​ኋት ይህች ክፋት ምን​ድን ናት? በዚ​ያ​ውስ ላይ ሌላ ወን​ድም አለን ብላ​ችሁ ለምን ነገ​ራ​ች​ሁት?”


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ፈር​ዖን ሕዝ​ቡን በለ​ቀቀ ጊዜ፥ ምንም ቅርብ ቢሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ምድር መን​ገድ አል​መ​ራ​ቸ​ውም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ሕዝቡ ሰል​ፉን በአየ ጊዜ እን​ዳ​ይ​ጸ​ጽ​ተው፥ ወደ ግብ​ፅም እን​ዳ​ይ​መ​ለስ” ብሎ​አ​ልና።


ሕዝ​ቡም ሙሴ ከተ​ራ​ራው ሳይ​ወ​ርድ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ፥ ወደ አሮን ተሰ​ብ​ስ​በው፥ “ይህ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ሆነ አና​ው​ቅ​ምና ተነ​ሥ​ተህ በፊ​ታ​ችን የሚ​ሄዱ አማ​ል​ክት ሥራ​ልን” አሉት።


እነ​ር​ሱም፥ “በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ፊት ሽታ​ች​ንን አግ​ም​ታ​ች​ሁ​ታ​ልና፥ ይገ​ድ​ለ​ንም ዘንድ ሰይ​ፍን በእጁ ሰጥ​ታ​ች​ሁ​ታ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ል​ከ​ታ​ችሁ፤ ይፍ​ረ​ድ​ባ​ች​ሁም” አሉ​አ​ቸው።


ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተመ​ለ​ሰና፥ “ጌታ ሆይ፥ ስለ​ምን ይህን ሕዝብ አስ​ከ​ፋህ? ስለ ምንስ ላክ​ኸኝ?


ሕዝ​ቡም በክ​ፋት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አጕ​ረ​መ​ረሙ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰምቶ ተቈጣ፤ እሳ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በእ​ነ​ርሱ ላይ ነደ​ደች፤ ከሰ​ፈ​ሩም አን​ዱን ወገን በላች።


እን​ዲ​ህስ ከም​ታ​ደ​ር​ግ​ብኝ፥ በፊ​ትህ ይቅ​ር​ታን አግ​ኝቼ እንደ ሆነ፥ በእኔ ላይ የሚ​ሆ​ነ​ውን መከራ እን​ዳ​ላይ፥ እባ​ክህ፥ ፈጽሞ ግደ​ለኝ።”


በግ​ብፅ ምድ​ርና በም​ድረ በዳ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ተአ​ም​ራ​ቴ​ንና ክብ​ሬን ያዩ እነ​ዚህ ሰዎች ሁሉ ዐሥር ጊዜ ስለ ተፈ​ታ​ተ​ኑኝ፥ ቃሌ​ንም ስላ​ል​ሰሙ፥


በነ​ጋ​ውም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ፥ “እና​ንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕዝብ ገድ​ላ​ች​ኋል” ብለው በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ አጕ​ረ​መ​ረሙ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios