Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፀአት 10:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 አን​በ​ጣም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ ላይ ወጣ፤ በግ​ብ​ፅም ዳርቻ ሁሉ ላይ ተቀ​መጠ፤ እጅ​ግም ብዙና ጠን​ካራ ነበር፤ ይህ​ንም የሚ​ያ​ህል አን​በጣ በፊት አል​ነ​በ​ረም፤ ወደ​ፊ​ትም ደግሞ እንደ እርሱ አይ​ሆ​ንም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እነርሱም ግብጽን በሙሉ ወረሩ፤ ስፍር ቍጥር የሌላቸው ሆነው የሀገሪቱን ዳር ድንበር ሁሉ አለበሱ። እንዲህ ያለ የአንበጣ መዓት ከዚህ ቀደም አልነበረም፤ ወደ ፊትም ደግሞ አይኖርም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 አንበጣዎችም በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ወጡ፥ በግብጽም አገር ሁሉ ላይ ተቀመጡ፤ እጅግም ብዙ ነበሩ፥ ይህንም የሚያህል አንበጣ በፊት አልነበረም፥ ወደፊትም ደግሞ እንደ እርሱ ያለ አይሆንም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እነርሱም በመርመስመስ መጥተው አገሪቱን ወረሩ፤ ይህን ያኽል ብዛት ያለው የአንበጣ መንጋ ከዚያ በፊት ታይቶ አይታወቅም፤ ወደ ፊትም ሊታይ አይችልም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 አንበጣዎችም በግብፅ አገር ሁሉ ላይ ወጡ፤ በግብፅም ዳርቻ ሁሉ ላይ ተቀመጡ፤ እጅግም ብዙ ነበሩ፤ ይህንም የሚያህል አንበጣ በፊት አልነበረም፤ ወደፊትም ደግሞ እንደ እርሱ አይሆንም።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፀአት 10:14
13 Referências Cruzadas  

“በም​ድር ላይም ራብ፥ ወይም ቸነ​ፈር፥ ወይም ዋግ፥ ወይም አረ​ማሞ ቢሆን፥ አን​በጣ፥ ወይም ኩብ​ኩባ ቢመጣ፥ የሕ​ዝ​ብ​ህም ጠላት ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው በአ​ን​ዲቱ ከብቦ ቢያ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ቸው፥ መቅ​ሠ​ፍ​ትና ደዌ ሁሉ ቢሆን፥


በግ​ብ​ፅም ሀገር ሁሉ አስ​ቀ​ድሞ እንደ እርሱ ያል​ሆነ፥ ኋላም ደግሞ እንደ እርሱ የማ​ይ​ሆን ታላቅ ጩኸት ይሆ​ናል።


እነሆ፥ ከተ​መ​ሠ​ረ​ተች ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንደ እርሱ ያለ በግ​ብፅ ሆኖ የማ​ያ​ውቅ እጅግ ታላቅ በረዶ ነገ በዚህ ጊዜ አዘ​ን​ባ​ለሁ።


ወይ​ኔን ባዶ ምድር አደ​ረ​ገው፤ በለ​ሴ​ንም ሰበ​ረው፤ ተመ​ለ​ከ​ተ​ውም፥ ጣለ​ውም፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹም ነጡ።


ብዙ ዘርም ወደ እርሻ ታወ​ጣ​ለህ፤ አን​በ​ጣም ይበ​ላ​ዋ​ልና ጥቂት ትሰ​በ​ስ​ባ​ለህ።


ዛፍ​ህን ሁሉ፤ የም​ድ​ር​ህ​ንም ፍሬ ሁሉ ኩብ​ኩባ ያጠ​ፋ​ዋል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios