Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፀአት 10:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ፈር​ዖ​ንም አላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን፤ እነሆ፥ እና​ን​ተን ስለቅ ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም መል​ቀቅ አለ​ብ​ኝን? ክፉ ነገር እን​ደ​ሚ​ገ​ጥ​ማ​ችሁ ዕወቁ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ፈርዖንም እንዲህ አለ፤ “ከሴቶቻችሁና ከልጆቻችሁ ጋራ እንድትሄዱ እለቅቃችኋለሁ፤ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ ይሁን፤ ነገር ግን ተንኰል ዐስባችኋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ጌታ ከእናንተ ጋር ይሁን እናንተንና ልጆቻችሁን እለቅቃለሁ፥ ነገር ግን ክፉ ነገር በፊታችሁ እንደሚሆን ተመልከቱ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ንጉሡም እንዲህ አለ፦ “እስቲ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፤ የዐመፅ ሤራ ማቀዳችሁ ግልጥ ስለ ሆነ ሴቶቻችሁንና ልጆቻችሁን ይዛችሁ እንድትሄዱ አልፈቅድላችሁም!

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ፈርዖንም፦ “እናንተን ከልጆቻችሁ ጋር ስለቅቅ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፤ ነገር ግን ክፉ ነገር በአእምሮአችሁ እንዳለ እወቁ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፀአት 10:10
7 Referências Cruzadas  

አሁ​ንም ሕዝ​ቅ​ያስ አያ​ስ​ታ​ችሁ፤ በእ​ነ​ዚ​ህም ቃላት እን​ድ​ት​ተ​ማ​መኑ አያ​ድ​ር​ጋ​ችሁ፤ አት​መ​ኑ​ትም፤ ከአ​ሕ​ዛ​ብና ከመ​ን​ግ​ሥ​ታት አማ​ል​ክት ሁሉ ሕዝ​ቡን ከእ​ጄና ከአ​ባ​ቶች እጅ ያድን ዘንድ ማንም አል​ቻ​ለም፤ ስለ​ዚ​ህም አም​ላ​ካ​ችሁ ከእጄ ያድ​ና​ችሁ ዘንድ አይ​ች​ልም።”


እን​ዲ​ህም አይ​ደ​ለም፤ እና​ንተ ወን​ዶቹ ሂዱ፤ ይህን ፈል​ጋ​ች​ኋ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አም​ልኩ” አላ​ቸው። ሙሴ​ንና አሮ​ን​ንም ከፈ​ር​ዖን ፊት አስ​ወ​ጡ​አ​ቸው።


ፈር​ዖ​ንም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ጠርቶ፥ “ሂዱ፤ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አም​ልኩ፤ ነገር ግን በጎ​ቻ​ች​ሁ​ንና ከብ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ብቻ ተዉ፤ ልጆ​ቻ​ች​ሁና ሴቶ​ቻ​ችሁ ግን ከእ​ና​ንተ ጋር ይሂዱ” አላ​ቸው።


ሙሴም አለው፥ “እኛ ከታ​ና​ና​ሾ​ቻ​ች​ንና ከሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ችን፥ ከወ​ን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችን ጋር እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በጎ​ቻ​ች​ን​ንና ላሞ​ቻ​ች​ን​ንም እን​ወ​ስ​ዳ​ለን። የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል ነውና።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ገድ ሊያ​ሳ​ያ​ቸው ቀን በዐ​ምደ ደመና፥ ሌሊ​ትም በዐ​ምደ እሳት ይመ​ራ​ቸው ነበር።


ሜም። “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያላ​ዘ​ዘው ይመ​ጣል፥


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios