Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤፌሶን 5:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ከቶ ሥጋ​ውን መጥ​ላት የሚ​ቻ​ለው የለም፤ ክር​ስ​ቶስ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንን እንደ መገ​ባት መግቡ፤ ጠብ​ቁም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ማንም የለም፤ ይመግበዋል፤ ይንከባከበዋል፤ ክርስቶስም ለቤተ ክርስቲያን ያደረገው ልክ እንደዚሁ ነው፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ማንም የራሱን እካል የሚጠላ ከቶ የለምና፤ ይመግበዋል፤ ይንከባከበውማል። ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን ያደረገው እንዲህ ነው፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 የገዛ ራሱን አካል የሚጠላ ማንም የለም፤ ይልቅስ ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን እንደሚያደርገው ዐይነት ራሱን ይመግባል፤ ይንከባከባልም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29-30 ማንም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና፥ ነገር ግን የአካሉ ብልቶች ስለሆንን፥ ክርስቶስ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን እንዳደረገላት፥ ይመግበዋል ይከባከበውማል።

Ver Capítulo Cópia de




ኤፌሶን 5:29
13 Referências Cruzadas  

ያን ጊዜም አዳም አለ፥ “ይህች አጥ​ንት ከአ​ጥ​ንቴ ናት፤ ሥጋ​ዋም ከሥ​ጋዬ ናት፤ እር​ስዋ ከባ​ልዋ ተገ​ኝ​ታ​ለ​ችና ሚስት ትሁ​ነኝ።”


ቸር ሰው ለነፍሱ መልካም ያደርጋል፤ ጨካኝ ግን ሥጋውን ይጐዳል።


ሰነፍ እጆ​ቹን ኰር​ትሞ ይቀ​መ​ጣል፥ የገዛ ሥጋ​ው​ንም ይበ​ላል።


መን​ጋ​ውን እንደ እረኛ ያሰ​ማ​ራል፤ ጠቦ​ቶ​ቹን በክ​ንዱ ሰብ​ስቦ በብ​ብቱ ይሸ​ከ​ማል፤ የሚ​ያ​ጠ​ቡ​ት​ንም በቀ​ስታ ይመ​ራል።


የም​ድረ በዳ ዛፍም ፍሬ​ውን ይሰ​ጣል፤ ምድ​ርም ቡቃ​ያ​ዋን ትሰ​ጣ​ለች፤ በም​ድ​ራ​ቸ​ውም በሰ​ላም ታም​ነው ይኖ​ራሉ፤ የቀ​ን​በ​ራ​ቸ​ው​ንም ማነቆ በሰ​በ​ርሁ ጊዜ፥ ከሚ​ገ​ዙ​አ​ቸ​ውም እጅ ባዳ​ን​ኋ​ቸው ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።


“ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ! ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም።


ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፤ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?


የማ​ያ​ስ​ተ​ውሉ፥ ዝን​ጉ​ዎች፥ ፍቅ​ርም፥ ምሕ​ረ​ትም የሌ​ላ​ቸው ናቸው።


እን​ዲ​ሁም ወን​ዶች ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን እንደ ራሳ​ቸው አድ​ር​ገው ይው​ደዱ፤ ሚስ​ቱ​ንም የወ​ደደ ራሱን ወደደ።


እኛ የአ​ካሉ ሕዋ​ሳት ነንና።


“ስለ​ዚ​ህም ወንድ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን ይተ​ዋል፤ ከሚ​ስ​ቱም ጋር አንድ ይሆ​ናል፤ ሁለ​ቱም አንድ አካል ይሆ​ናሉ።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios