Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መክብብ 8:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ከሚ​በ​ላ​ውና ከሚ​ጠ​ጣው፥ ደስም ከሚ​ለው በቀር ለሰው ከፀ​ሓይ በታች ሌላ መል​ካም ነገር የለ​ው​ምና እኔ ደስ​ታን አመ​ሰ​ገ​ንሁ፤ ይህም ከፀ​ሓይ በታች ከድ​ካሙ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ይ​ወቱ ዘመን ለእ​ርሱ የሰ​ጠው ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ለሰው፣ ከፀሓይ በታች ከመብላት፣ ከመጠጣትና ከመደሰት ሌላ የተሻለ ነገር ስለሌለ፣ በሕይወት ደስ መሠኘት መልካም ነው አልሁ፤ ስለዚህ አምላክ ከፀሓይ በታች በሰጠው የሕይወት ዘመኑ ሁሉ በሥራው ደስታ ይኖረዋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ከመብላትና ከመጠጣት፥ ደስም ከመሰኘት በቀር ለሰው ልጅ ከፀሐይ በታች ሌላ ምንም መልካም ነገር የለውምና እኔ ደስታን አመሰገንሁ፥ ይህም እግዚአብሔር ከፀሐይም በታች በሰጠው በሕይወቱ ዘመን በድካሙ ከእርሱ ጋር ይኖራል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ስለዚህ ሰው በዚህ ዓለም ሲኖር የተሰጠው ዕድል ፈንታ መብላት፥ መጠጣትና ራሱን ማስደሰት መሆኑን አረጋገጥኩ፤ እግዚአብሔር በዚህ ዓለም በሰጠው ዘመን፥ ሰው ሁሉ ሠርቶ ያገኘውን ሀብት በዚህ ዐይነት ይደሰትበታል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ከሚበላውና ከሚጠጣው ደስም ከሚለው በቀር ለሰው ከፀሐይ በታች ሌላ መልካም ነገር የለውምና እኔ ደስታን አመሰገንሁ፥ ከፀሐይም በታች ከድካሙ እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ይህ ደስታው ከእርሱ ጋር ይኖራል።

Ver Capítulo Cópia de




መክብብ 8:15
11 Referências Cruzadas  

እኔ በልቤ፥ “ና በደ​ስ​ታም እፈ​ት​ን​ሃ​ለሁ፥ እነሆ፥ መል​ካ​ም​ንም እይ” አልሁ፤ ይህም እነሆ፥ ከንቱ ነበረ።


ዐይ​ኖቼ ከፈ​ለ​ጉት ሁሉ አላ​ጣ​ሁም፥ ልቤ​ንም ከደ​ስታ ሁሉ አል​ከ​ለ​ከ​ል​ሁ​ትም፤ ልቤ በድ​ካሜ ሁሉ ደስ ይለው ነበ​ርና፤ ከድ​ካ​ሜም ሁሉ ይህ ዕድል ፋን​ታዬ ሆነ።


ለሰው ከመ​ብ​ላ​ትና ከመ​ጠ​ጣት በድ​ካ​ሙም ለሰ​ው​ነቱ መል​ካም ነገር ከሚ​ያ​ሳ​ያት በቀር በጎ ነገር የለም፤ ይህ ደግሞ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ እንደ ተሰጠ አየሁ።


የሰው ልጆች በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው ዘመን ሁሉ ከፀ​ሐይ በታች የሚ​ሠ​ሩት መል​ካም ነገር ምን እንደ ሆነ እስ​ካይ ድረስ ልቤ በጥ​በብ እየ​መ​ራኝ፥ ሰው​ነ​ቴን በወ​ይን ደስ ለማ​ሰ​ኘት፥ ስን​ፍ​ና​ንም ለመ​ያዝ በልቤ መረ​መ​ርሁ።


ያም ዕድል ፋን​ታው ነውና ሰው በሥ​ራው ደስ ከሚ​ለው በቀር ሌላ መል​ካም ነገር እን​ደ​ሌ​ለው አየሁ፤ ከእ​ርሱ በኋ​ላስ የሚ​ሆ​ነ​ውን ያይ ዘንድ የሚ​ያ​መ​ጣው ማን ነው?


እነሆ፥ እኔ ያየ​ሁት መል​ካ​ምና የተ​ዋበ ነገር፦ ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ጠው በሕ​ይ​ወቱ ዘመን ሁሉ ይበ​ላና ይጠጣ ዘንድ፥ ከፀ​ሐይ በታ​ችም በሚ​ደ​ክ​ም​በት ድካም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ ነው፤ ይህ ዕድል ፈን​ታው ነውና።


በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ፥ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios