Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መክብብ 3:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ለሰው ልጆች ሞት አለ​ባ​ቸው፥ ለእ​ን​ስ​ሳም ሞት አለ​ባ​ቸው፤ አንድ ሞት አለ​ባ​ቸው፤ አንዱ እን​ደ​ሚ​ሞት ሌላ​ውም እን​ዲሁ ይሞ​ታል፤ ለሁ​ሉም አንድ እስ​ት​ን​ፋስ አላ​ቸው፥ ሰው ከእ​ን​ስሳ ብል​ጫው ምን​ድን ነው? ሁሉም ከንቱ ነውና ምንም የለ​ውም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 የሰው ዕድል ፈንታ እንደ እንስሳት ነው፤ ሁለቱም ዕጣ ፈንታቸው አንድ ነው፤ አንዱ እንደሚሞት፣ ሌላውም እንዲሁ ይሞታል። ሁሉ አንድ ዐይነት እስትንፋስ አላቸው፤ ሰውም ከእንስሳ ብልጫ የለውም፤ ሁሉም ከንቱ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 የሰው ልጆችና የእንስሳ እድል ፈንታ አንድ ነው፥ አንድ ዓይነት መጨረሻ ይገጥማቸዋል፤ አንዱ እንደሚሞት ሌላውም እንዲሁ ይሞታል፥ የሁሉም እስትንፋስ አንድ ነው፥ ሁሉም ከንቱ ነውና ሰው ከእንስሳ ብልጫ የለውም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በእርግጥም የሰው ልጆችና የእንስሶች ዕድል ፈንታቸው አንድ ዐይነት ነው፤ አንዱ እንደሚሞት ሌላውም እንዲሁ ይሞታል፤ የሁለቱም የተፈጥሮ እስትንፋስ አንድ ዐይነት ነው፤ ታዲያ ሁለቱም ከንቱ ስለ ሆኑ ሰው ከእንስሳ አይሻልም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የሰው ልጆችና የእንስሳ እድል ፈንታ አንድ ነው፥ ድርሻቸውም ትክክል ነው፥ አንዱ እንደሚሞት ሌላውም እንዲሁ ይሞታል፥ የሁሉም እስትንፋስ አንድ ነው፥ ሁሉም ከንቱ ነውና ሰው ከእንስሳ ብልጫ የለውም።

Ver Capítulo Cópia de




መክብብ 3:19
18 Referências Cruzadas  

ሞትን እን​ሞ​ታ​ለ​ንና፥ በም​ድ​ርም ላይ እንደ ፈሰ​ሰና እን​ደ​ማ​ይ​መ​ለስ ውኃ እን​ሆ​ና​ለ​ንና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነፍ​ስን ይወ​ስ​ዳል። የተ​ጣ​ለ​ው​ንም ከእ​ርሱ ያርቅ ዘንድ ያስ​ባል።


ውኃ​ቸ​ውን ደም አደ​ረገ፥ ዓሦ​ቻ​ቸ​ው​ንም ገደለ።


ብራ​ብም አል​ለ​ም​ን​ህም፥ ዓለም ሁሉ በመ​ላው የእኔ ነውና።


የፍ​ሪ​ዳ​ውን ሥጋ አል​በ​ላም፥ የፍ​የ​ሉ​ንም ደም አል​ጠ​ጣም።


ተቀ​ም​ጠህ ወን​ድ​ም​ህን ታማ​ዋ​ለህ፥ ለእ​ና​ት​ህም ልጅ ዕን​ቅ​ፋ​ትን አኖ​ርህ።


ከፀ​ሐይ በታች የተ​ሠ​ራ​ውን ሥራ ሁሉ አየሁ፤ እነ​ሆም፥ ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


ልቤም ብዙ ጥበ​ብ​ንና አእ​ም​ሮን፥ ምሳ​ሌ​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን ተመ​ለ​ከ​ተች። ይህም ነፋ​ስን መከ​ተል እንደ ሆነ አስ​ተ​ዋ​ልሁ።


የጠ​ቢብ ዐይ​ኖች በራሱ ላይ ናቸ​ውና፤ አላ​ዋቂ ግን በጨ​ለማ ይሄ​ዳል፤ ደግሞ የሁ​ለ​ቱም መጨ​ረ​ሻ​ቸው አንድ እንደ ሆነ አስ​ተ​ዋ​ልሁ።


ለብ​ልህ ከአ​ላ​ዋቂ ጋር ለዘ​ለ​ዓ​ለም መታ​ሰ​ቢያ የለ​ውም፤ እነሆ፥ ዘመን ይመ​ጣ​ልና ሁሉም ይረ​ሳል፤ ብል​ህስ ከአ​ላ​ዋቂ ጋር እን​ዴት ይሞ​ታል?


ወደ ግብዣ ቤትም ከመ​ሄድ ወደ ልቅሶ ቤት መሄድ ይሻ​ላል፤ እርሱ የሰው ሁሉ ፍጻሜ ነውና፥ ሕያ​ውም የሆነ ይህን መል​ካም ነገር በልቡ ያኖ​ረ​ዋል።


ሰውም ጊዜ​ውን አያ​ው​ቅም፤ በክፉ መረብ እንደ ተጠ​መዱ ዓሣ​ዎች ፥ በወ​ጥ​መ​ድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እን​ዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድ​ን​ገት ሲወ​ድ​ቅ​ባ​ቸው ይጠ​መ​ዳሉ።


በሁ​ሉም ከን​ቱ​ነት አለ፥ የጻ​ድ​ቁና የበ​ደ​ለ​ኛው፥ የመ​ል​ካ​ሙና የክ​ፉው፥ የን​ጹ​ሑና የር​ኩሱ፥ መሥ​ዋ​ዕ​ትን የሚ​ሠ​ዋ​ውና የማ​ይ​ሠ​ዋው፥ የመ​ል​ካ​ሙና እን​ዲሁ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛው፥ የመ​ሐ​ላ​ኛ​ውና እን​ዲሁ መሐ​ላን የሚ​ፈ​ራው ድርሻ አንድ ነው።


እነ​ዚህ ሰዎች ሰው እን​ደ​ሚ​ሞት ቢሞቱ፥ ወይም መቅ​ሠ​ፍ​ታ​ቸው እንደ ሰው ሁሉ መቅ​ሠ​ፍት ቢሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ላ​ከ​ኝም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios