Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መክብብ 3:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ደግ​ሞም ሰው ሁሉ ይበ​ላና ይጠጣ ዘንድ በድ​ካ​ሙም ሁሉ መል​ካ​ምን ያይ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጦታ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ሰው ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ፣ በሚደክምበትም ሁሉ ርካታን ያገኝ ዘንድ ይህ የአምላክ ችሮታ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ደግሞም የእግዚአብሔር ስጦታ ሰው ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ በድካሙም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ሰው ጥሮ ግሮ ባገኘው የድካም ዋጋ በልቶና ጠጥቶ መደሰት የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ደግሞም ሰው ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ በድካሙም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።

Ver Capítulo Cópia de




መክብብ 3:13
14 Referências Cruzadas  

ከት​ን​ሽ​ነቴ ጀምሮ ሁል​ጊዜ ተሰ​ለ​ፉ​ብኝ፤ ነገር ግን አል​ቻ​ሉ​ኝም።


ስለ በጎ ፋንታ ክፉን መለ​ሱ​ልኝ፥ ሰው​ነ​ቴ​ንም ልጆ​ችን አሳ​ጡ​አት።


ለሰው ከመ​ብ​ላ​ትና ከመ​ጠ​ጣት በድ​ካ​ሙም ለሰ​ው​ነቱ መል​ካም ነገር ከሚ​ያ​ሳ​ያት በቀር በጎ ነገር የለም፤ ይህ ደግሞ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ እንደ ተሰጠ አየሁ።


የሰው ልጆች በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው ዘመን ሁሉ ከፀ​ሐይ በታች የሚ​ሠ​ሩት መል​ካም ነገር ምን እንደ ሆነ እስ​ካይ ድረስ ልቤ በጥ​በብ እየ​መ​ራኝ፥ ሰው​ነ​ቴን በወ​ይን ደስ ለማ​ሰ​ኘት፥ ስን​ፍ​ና​ንም ለመ​ያዝ በልቤ መረ​መ​ርሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ሀብ​ት​ንና ጥሪ​ትን ክብ​ር​ንም ሰጠው፥ ከወ​ደ​ደ​ውም ሁሉ ለሰ​ው​ነቱ የከ​ለ​ከ​ላት የለም፤ ነገር ግን ሌላ ሰው ይበ​ላ​ዋል እንጂ ከእ​ርሱ ይበላ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አላ​ሠ​ለ​ጠ​ነ​ውም፤ ይህም ከን​ቱና ክፉ ደዌ ነው።


ከሚ​በ​ላ​ውና ከሚ​ጠ​ጣው፥ ደስም ከሚ​ለው በቀር ለሰው ከፀ​ሓይ በታች ሌላ መል​ካም ነገር የለ​ው​ምና እኔ ደስ​ታን አመ​ሰ​ገ​ንሁ፤ ይህም ከፀ​ሓይ በታች ከድ​ካሙ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ይ​ወቱ ዘመን ለእ​ርሱ የሰ​ጠው ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ​ህን ተቀ​ብ​ሎ​ታ​ልና፦ ና እን​ጀ​ራ​ህን በደ​ስታ ብላ፥ በበጎ ልቡ​ናም የወ​ይን ጠጅ​ህን ጠጣ።


በዚ​ያም በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ብሉ፤ እጃ​ች​ሁ​ንም በም​ት​ዘ​ረ​ጉ​በት፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በባ​ረ​ካ​ችሁ ነገር ሁሉ፥ እና​ን​ተና ቤተ​ሰ​ባ​ችሁ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


አን​ተም በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አኑ​ረው፥ በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስገድ። አን​ተም፥ በመ​ካ​ከ​ል​ህም ያለ ሌዋ​ዊና መጻ​ተኛ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ን​ተና ለቤ​ትህ በሰ​ጠው ቸር​ነት ሁሉ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios