Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መክብብ 2:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ወን​ዶ​ችና ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ችን ገዛሁ፤ በቤት የተ​ወ​ለዱ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ነበ​ሩኝ፤ ከእኔ አስ​ቀ​ድ​መው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከነ​በ​ሩት ሁሉ ይልቅ ብዙ የበ​ጎ​ችና የከ​ብ​ቶች መን​ጋ​ዎች ነበ​ሩኝ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ወንድና ሴት ባሪያዎችን ገዛሁ፤ በቤቴም የተወለዱ ሌሎች ባሪያዎች ነበሩኝ። ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ይልቅ ብዙ የከብት፣ የበግና የፍየል መንጋዎች ነበሩኝ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ወንዶችንና ሴቶችን ባርያዎች ገዛሁ፥ የቤት ውልድ ባርያዎችም ነበሩኝ፥ ከእኔ አስቀድመው በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ብዙ ከብቶችና መንጋዎች ነበሩኝ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ወንዶችና ሴቶች ባርያዎችን ገዛሁ፤ ሌሎች የቤት ውልድ አገልጋዮችም ነበሩኝ፤ ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይበልጥ ብዙ የከብት፥ የፍየልና የበግ መንጋ አረባሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ወንዶችንና ሴቶችን ባሪያዎች ገዛሁ፥ የቤት ውልድ ባሪያዎችም ነበሩኝ፥ ከእኔ አስቀድመው በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ብዙ ከብቶችና መንጋዎች ነበሩኝ።

Ver Capítulo Cópia de




መክብብ 2:7
16 Referências Cruzadas  

አብ​ራ​ምም በከ​ብት፥ በብ​ርና በወ​ርቅ እጅግ በለ​ጸገ።


አብ​ራ​ምም የወ​ን​ድሙ ልጅ ሎጥ እንደ ተማ​ረከ በሰማ ጊዜ ወገ​ኖ​ቹ​ንና ቤተ​ሰ​ቦ​ቹን ሁሉ ቈጠ​ራ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ሦስት መቶ ዐሥራ ስም​ንት ሆኑ፤ እስከ ዳን ድረስ ተከ​ትሎ አሳ​ደ​ዳ​ቸው።


አብ​ራ​ምም፥ “ለእኔ ዘር አል​ሰ​ጠ​ኸ​ኝም፤ የዘ​መዴ ልጅ እርሱ ይወ​ር​ሰ​ኛል” አለ።


ከዋ​ሊ​ያና ከሚ​ዳቋ፥ ከበ​ረሃ ፍየ​ልና ከሰቡ ወፎች በቀር ዐሥር ፍሪ​ዳ​ዎች፥ ሃያም የተ​ሰ​ማሩ በሬ​ዎች፥ አንድ መቶም በጎች ነበረ።


የሞ​ዓ​ብም ንጉሥ ሞሳ ባለ በጎች ነበር፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ መቶ ሺህ የጠ​ጕር አውራ በጎ​ች​ንና መቶ ሺህ ጠቦ​ቶ​ችን ይገ​ብ​ር​ለት ነበር።


በም​ድረ በዳ​ውም ግን​ቦ​ችን ሠራ፤ ብዙ ጕድ​ጓ​ድም ማሰ፤ በቆ​ላ​ውና በደ​ጋው ብዙ እን​ስ​ሶች ነበ​ሩ​ትና፤ ደግ​ሞም እርሻ ይወ​ድድ ነበ​ርና በተ​ራ​ራ​ማ​ውና በፍ​ሬ​ያ​ማው ስፍራ አራ​ሾ​ችና የወ​ይን አት​ክ​ል​ተ​ኞች ነበ​ሩት።


የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ልጆች፤ የሳጢ ልጆች፥ የሰ​ፌ​ርታ ልጆች፥ የፋ​ዱ​ርሓ ልጆች፤


እነ​ዚህ ናታ​ኒም ሁሉና የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ።


የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ልጆች፤ የሦ​ጠይ ልጆች፥ የሰ​ፋ​ሬት ልጆች፥ የፈ​ሪዳ ልጆች፥


ከብ​ቶ​ቹም፦ ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመ​ሎች፥ አም​ስት መቶም ጥማድ በሬ፥ አም​ስት መቶም እን​ስት አህ​ዮች ነበሩ፤ እጅግ ብዙም አገ​ል​ጋ​ዮች ነበ​ሩት፤ ሥራ​ውም በም​ድር ላይ ታላቅ ነበረ፤ ያም ሰው በም​ሥ​ራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ገናና ነበረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፊ​ተ​ኛው ይልቅ የኋ​ለ​ኛ​ውን ለኢ​ዮብ ባረከ፤ መን​ጋ​ዎ​ቹም ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፥ ስድ​ስት ሺህም ግመ​ሎች፥ አንድ ሺህም ጥማድ በሬ​ዎች፥ አንድ ሺህም እን​ስት አህ​ዮች ነበሩ።


ነገር ግን ያ ክፉ አገ​ል​ጋይ በልቡ፦ ጌታዬ ቶሎ አይ​መ​ጣም ቢል፥ በጌ​ታው ቤት ያሉ​ት​ንም ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶ​ችን አገ​ል​ጋ​ዮች ሊደ​በ​ድ​ብና ሊያ​ጕ​ላላ ቢጀ​ምር፥ ከሰ​ካ​ራ​ሞ​ችም ጋር ቢበ​ላና ቢጠጣ፥ ቢሰ​ክ​ርም፥


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios