Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መክብብ 2:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እጄ የሠ​ራ​ቻ​ትን ሥራ​ዬን ሁሉ፥ የደ​ከ​ም​ሁ​በ​ት​ንም ድካ​ሜን ሁሉ ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ እነሆ፥ ሁሉ ከንቱ፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነበረ፥ ከፀ​ሐይ በታ​ችም ትርፍ አል​ነ​በ​ረም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ሆኖም እጆቼ የሠሩትን ሁሉ፣ ለማግኘትም የደከምሁትን ድካም ሁሉ ሳስብ፣ ሁሉም ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነበር፤ ከፀሓይ በታች ምንም ትርፍ አልነበረም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እጄ የሠራቻትን ሥራዬን ሁሉ የደከምሁበትንም ድካሜን ሁሉ ተመለከትሁ፥ እነሆ፥ ሁሉ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነበረ፥ ከፀሐይ በታችም ትርፍ አልነበረም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ይህን ሁሉ ካደረግሁ በኋላ ያንን የሠራሁትን ነገር ሁሉ ምን ያኽል እንደ ደከምኩበት ስመለከት ከቊጥር የማይገባ ዋጋቢስ መሆኑን ተረዳሁ፤ እንዲያውም ምንም የማይጠቅምና ነፋስን እንደ መጨበጥ የሚያስቈጥር ሆኖ አገኘሁት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እጄ የሠራቻትን ሥራዬን ሁሉ የደከምሁበትንም ድካሜን ሁሉ ተመለከትሁ፥ እነሆ፥ ሁሉ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነበረ፥ ከፀሐይ በታችም ትርፍ አልነበረም።

Ver Capítulo Cópia de




መክብብ 2:11
13 Referências Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የፈ​ጠ​ረ​ውን ሁሉ እጅግ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ ስድ​ስ​ተ​ኛም ቀን ሆነ።


ሙሴም ሥራ​ውን ሁሉ አየ፤ እነ​ሆም፥ አድ​ር​ገ​ውት ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ አድ​ር​ገ​ውት ነበር፤ ሙሴም ባረ​ካ​ቸው።


ከፀ​ሐይ በታች የተ​ሠ​ራ​ውን ሥራ ሁሉ አየሁ፤ እነ​ሆም፥ ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


ልቤም ብዙ ጥበ​ብ​ንና አእ​ም​ሮን፥ ምሳ​ሌ​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን ተመ​ለ​ከ​ተች። ይህም ነፋ​ስን መከ​ተል እንደ ሆነ አስ​ተ​ዋ​ልሁ።


ከፀ​ሐይ በታች በሚ​ደ​ክ​ም​በት ድካም ሁሉ የሰው ትርፉ ምን​ድን ነው?


ለሠ​ራ​ተኛ የድ​ካሙ ትርፍ ምን​ድን ነው?


ብርን የሚ​ወ​ድድ ሰው ብርን አይ​ጠ​ግ​ብም፤ ብዙ እህ​ል​ንም የሚ​ወ​ድድ እን​ዲሁ ነው፤ ይህም ከንቱ ነው።


ይህም ደግሞ የሚ​ያ​ሳ​ዝን ክፉ ደዌ ነው፥ እንደ መጣ እን​ዲሁ ይሄ​ዳ​ልና፥ ለሰ​ው​ነቱ ለሚ​ደ​ክም ሰው ትርፉ ምን​ድን ነው?


እነሆ፥ አሕዛብ ስለ እሳት እንዲሠሩ፥ ወገኖችም ስለ ከንቱነት እንዲደክሙ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ አይደለምን?


“ኑሮዬ ይበቃኛል፤” ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios