Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መክብብ 10:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 የሰ​ማይ ዎፍ ቃል​ህን ያወ​ጣ​ዋ​ልና፥ ክንፍ ያለ​ውም ነገ​ር​ህን ያወ​ራ​ዋ​ልና በል​ብህ ዐሳብ እን​ኳን ቢሆን ንጉ​ሥን አት​ሳ​ደብ፥ በመ​ኝታ ቤት​ህም ባለ​ጠ​ጋን አት​ሳ​ደብ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በሐሳብህም እንኳ ንጉሥን አትንቀፍ፤ በመኝታ ክፍልህም ባለጠጋን አትርገም፤ የሰማይ ወፍ ቃልህን ልትወስድ፣ የምትበረዋም ወፍ የምትለውን ልታደርስ ትችላለችና።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 የሰማይ ወፍ ቃሉን ይወስደዋልና፥ ባለ ክንፎችም ነገሩን ይናገራሉና በልብህ አሳብ እንኳ ቢሆን ንጉሥን አትስደብ፥ በመኝታ ቤትህም ባለጠጋን አትስደብ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 የሚሰማብኝ የለም ብለህ በስውር እንኳ ቢሆን ንጉሥን አትማ፤ በተኛህበት አልጋህ ላይ ሆነህም ባለጸጋን አትስደብ፤ ምሥጢርህን የሰሙ ነገር ጠላፊዎች ክንፍ እንዳለው ወፍ በረው ሊነግሩብህ ይችላሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 የሰማይ ወፍ ቃሉን ይወስደዋልና፥ ባለ ክንፎችም ነገሩን ይናገራሉና በልብህ አሳብ እንኳ ቢሆን ንጉሥን አትስደብ፥ በመኝታ ቤትህም ባለጠጋን አትስደብ።

Ver Capítulo Cópia de




መክብብ 10:20
11 Referências Cruzadas  

ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም አንዱ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ሀገር ነቢዩ ኤል​ሳዕ ያለ አይ​ደ​ለ​ምን? በእ​ል​ፍ​ኝህ ውስጥ ሆነህ የም​ት​ና​ገ​ረ​ው​ንና ቃል​ህን ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እርሱ ይነ​ግ​ረ​ዋል፤” አለ።


ልብሱ ነውና፥ ዕር​ቃ​ኑ​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ን​በት ይህ ብቻ ነውና፤ የሚ​ተ​ኛ​በ​ትም ሌላ የለ​ው​ምና፤ ወደ እኔም ቢጮኽ ፈጥኜ እሰ​ማ​ዋ​ለሁ፤ መሓሪ ነኝና።


“ፈራ​ጆ​ችን አት​ስ​ደብ፥ የሕ​ዝ​ብ​ህ​ንም አለቃ ክፉ አት​ና​ገ​ረው።


ወን​ዙም ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ችን ያፈ​ላል፤ ወጥ​ተ​ውም ወደ ቤትህ፥ ወደ መኝታ ቤትህ፥ ወደ አል​ጋ​ህም፥ ወደ ሹሞ​ች​ህም ቤት፥ በሕ​ዝ​ብ​ህም ላይ፥ ወደ ቡሃ​ቃ​ዎ​ች​ህም፥ ወደ ምድ​ጃ​ዎ​ች​ህም ይገ​ባሉ፤


በዚ​ህም በር​ግጥ ጽኑ ረኃብ ይመ​ጣ​ባ​ች​ኋል፤ በተ​ራ​ባ​ች​ሁም ጊዜ ትጨ​ነ​ቃ​ላ​ችሁ፤ በአ​ለ​ቆ​ችና በመ​ኳ​ን​ን​ቱም ላይ ክፉ ትና​ገ​ራ​ላ​ችሁ፤ ወደ ላይ ወደ ሰማይ ትመ​ለ​ከ​ታ​ላ​ችሁ።


ማርታ ግን ብዙ በማ​ዘ​ጋ​ጀት ትደ​ክም ነበር፤ ቆማም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እኅቴ ትታኝ ብቻ​ዬን ስሠራ አያ​ሳ​ዝ​ን​ህ​ምን? ርጃት በላት” አለ​ችው።


እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እነ​ዚህ ዝም ቢሉ እኒህ ድን​ጋ​ዮች ይጮ​ሀሉ።”


ጳው​ሎ​ስም፥ “ወን​ድ​ሞች፥ ሊቀ ካህ​ናት መሆ​ኑን አላ​ው​ቅም መጽ​ሐፍ ‘በሕ​ዝ​ብህ አለቃ ላይ ክፉ አት​ና​ገር’ ይላ​ልና” አላ​ቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios