Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መክብብ 10:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ሰነፍ ነገ​ርን ያበ​ዛል፤ ሰውም የሆ​ነ​ው​ንና ወደ ፊት የሚ​ሆ​ነ​ውን አያ​ው​ቅም፤ ከእ​ርሱ በኋላ የሚ​ሆ​ነ​ው​ንስ ማን ይነ​ግ​ረ​ዋል?

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ሞኙም ቃልን ያበዛል። የሚመጣውን የሚያውቅ ሰው የለም፤ ከርሱ በኋላ የሚሆነውንስ ማን ሊነግረው ይችላል?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ሰነፍ ቃሉን ያበዛል፥ ሰው ግን የሚሆነውን አያውቅም፥ ከእርሱስ በኋላ የሚሆነውን ማን ይነግረዋል?

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ሞኝ ሰው ልፍለፋ ያበዛል። ወደፊት የሚሆነውን የሚያውቅ የለም፤ ሰው ከሞተ በኋላ የሚሆነውን ነገር የሚያስረዳው የለም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ሰነፍ ቃሉን ያበዛል፥ ሰው ግን የሚሆነውን አያውቅም፥ ከእርሱስ በኋላ የሚሆነውን ማን ይነግረዋል?

Ver Capítulo Cópia de




መክብብ 10:14
13 Referências Cruzadas  

በኀ​ጢ​አ​ቶ​ችህ ላይ እን​ዳ​ት​ጨ​ምር፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ብዙ መና​ገር በደል ይሆ​ን​ብ​ሃል።”


ኢዮብ ግን አፉን በከ​ንቱ ይከ​ፍ​ታል፥ ያለ ዕው​ቀ​ትም ቃሉን ያበ​ዛል።”


ኃጥእ ከነገር ብዛት የተነሣ ከኀጢአት አያመልጥም፤ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው።


የጠቢባን ምላስ መልካም ነገርን ታውቃለች፤ የአላዋቂዎች አፍ ግን ክፋትን ይናገራል።


የሰ​ነፍ ድካሙ ያሠ​ቃ​የ​ዋል፥ ወደ ከተማ መሄ​ድን አያ​ው​ቅ​ምና።


ያም ዕድል ፋን​ታው ነውና ሰው በሥ​ራው ደስ ከሚ​ለው በቀር ሌላ መል​ካም ነገር እን​ደ​ሌ​ለው አየሁ፤ ከእ​ርሱ በኋ​ላስ የሚ​ሆ​ነ​ውን ያይ ዘንድ የሚ​ያ​መ​ጣው ማን ነው?


ሕልም በብዙ መከራ፥ እን​ዲ​ሁም የሰ​ነፍ ቃል በብዙ ነገር ይመ​ጣ​ልና።


ሰው በከ​ንቱ ወራቱ ቍጥ​ርና እንደ ጥላ በሚ​ያ​ሳ​ል​ፈው ዘመኑ በሕ​ይ​ወቱ ሳለ ለሰው የሚ​ሻ​ለ​ውን የሚ​ያ​ውቅ ማን ነው? ወይስ ለሰው ከፀ​ሓይ በታች ከእ​ርሱ በኋላ የሚ​ሆ​ነ​ውን ማን ይነ​ግ​ረ​ዋል?


በመ​ል​ካም ቀን ደስ ይበ​ልህ ፤ በክ​ፉም ቀን ተመ​ል​ከት፤ ሰው ከእ​ርሱ በኋላ መር​ምሮ ምንም እን​ዳ​ያ​ገኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ንም ያንም እን​ደ​ዚያ ሠራ።


የሚ​ሆ​ነ​ው​ንም ምንም የሚ​ያ​ውቅ የለም፤ እን​ዴ​ትስ እን​ደ​ሚ​ሆን የሚ​ነ​ግ​ረው ማን ነው?


ይህን ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ለልቤ ሰጠሁ፥ ጻድ​ቃ​ንና ጠቢ​ባን ሥራ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ እንደ ሆኑ፥ ይህን ሁሉ ልቤ ተመ​ለ​ከ​ተች፤ ፍቅር ወይም ጥል ቢሆን ሰው አያ​ው​ቅም፥ ሁሉ ወደ ፊታ​ቸው ነው።


አንተ አፍ​ህን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ እንደ አደ​ረ​ግህ እኔ ሰም​ቼ​አ​ለሁ።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios