Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘዳግም 4:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ያስ​ተ​ም​ርህ ዘንድ ከሰ​ማይ ድም​ፁን አሰ​ማህ፤ በም​ድ​ርም ላይ ታላ​ቁን እሳት አሳ​የህ፤ ከእ​ሳ​ቱም መካ​ከል ቃሉን ሰማህ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ሊገሥጽህ ድምፁን ከሰማይ እንድትሰማ አደረገ፤ በምድርም ላይ አስፈሪ እሳቱን አሳየህ፤ ከእሳቱም ውስጥ ቃሉን ሰማህ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ያስተምራችሁ ዘንድ ከሰማይ ድምፁን አሰማችሁ፥ በምድርም ላይ ታላቁን እሳቱን አሳያችሁ፥ ከእሳቱም መካከል የእርሱን ድምፅ ሰማችሁ።።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 እናንተን ለማስተማር ከሰማይ ድምፁን አሰማችሁ፤ በምድርም አስፈሪ እሳቱን እንድታዩ ፈቀደላችሁ፤ ከእሳቱም መካከል የእርሱን ድምፅ ሰማችሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ያስተምርህ ዘንድ ከሰማይ ድምፁን አሰማህ፤ በምድርም ላይ ታላቁን እሳት አሳየህ፤ ከእሳትም ውስጥ ቃሉን ሰማህ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘዳግም 4:36
12 Referências Cruzadas  

ወደ ሲናም ተራራ ወረ​ድህ፤ ከሰ​ማ​ይም ተና​ገ​ር​ሃ​ቸው፤ ቅኑን ፍር​ድና እው​ነ​ቱን ሕግ፥ መል​ካ​ሙ​ንም ሥር​ዐ​ትና ትእ​ዛዝ ሰጠ​ሃ​ቸው፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ሳት ስለ ወረ​ደ​በት የሲና ተራራ ሁሉ እንደ ምድጃ ጢስ ይጤስ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም እንደ እቶን ጢስ ያለ ጢስ ይወጣ ነበር፤ ተራ​ራ​ውም ሁሉ እጅግ ይና​ወጥ ነበር፤ ሕዝ​ቡም ፈጽ​መው ደነ​ገጡ።


የቀ​ንደ መለ​ከ​ቱም ድምፅ እጅግ እየ​ፈ​ጠነ በር​ትቶ ይሰማ ነበር። ሙሴም ተና​ገረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በድ​ምፅ መለ​ሰ​ለት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን፥ “ከአ​ንተ ጋር ስነ​ጋ​ገር ሕዝቡ እን​ዲ​ሰሙ፥ ደግ​ሞም ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዲ​ያ​ም​ኑ​ብህ፥ እነሆ፥ በዐ​ምደ ደመና ወደ አንተ እመ​ጣ​ለሁ” አለው። ሙሴም የሕ​ዝ​ቡን ቃል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነገረ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር በሲና ተራራ ላይ ወረደ፤ ደመ​ና​ውም ስድ​ስት ቀን ሸፈ​ነው፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከደ​መ​ናው ውስጥ ሙሴን ጠራው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ሳት መካ​ከል ሆኖ ተና​ገ​ራ​ችሁ፤ የቃ​ልን ድምፅ ሰማ​ችሁ፤ ከድ​ምፅ በቀር መል​ክን ግን አላ​ያ​ች​ሁም።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኮ​ሬብ ተራራ በእ​ሳት መካ​ከል ሆኖ በተ​ና​ገ​ራ​ችሁ ቀን መል​ኩን ከቶ አላ​ያ​ች​ሁ​ምና ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን እጅግ ጠብቁ፤


አንተ ከእ​ሳት መካ​ከል ሆኖ ሲና​ገር የሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድምፅ እንደ ሰማ​ህና በሕ​ይ​ወት እን​ዳ​ለህ ሌላ ሕዝብ ሰምቶ እንደ ሆነ፥


ሰውም ልጁን እን​ደ​ሚ​ገ​ሥጽ እን​ዲሁ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አን​ተን እን​ዲ​ገ​ሥጽ በል​ብህ ዕወቅ።


ሊዳ​ሰስ ወደ​ሚ​ችል ወደ​ሚ​ቃ​ጠ​ልም እሳት ወደ ጭጋ​ግም፥ ወደ ጨለ​ማም ወደ ዐውሎ ነፋ​ስም፥


ለሚ​ና​ገ​ረው እንቢ እን​ዳ​ትሉ ተጠ​ን​ቀቁ፤ እነ​ርሱ በደ​ብረ ሲና የተ​ገ​ለ​ጠ​ላ​ቸ​ውን እንቢ ስለ አሉት ካል​ዳኑ፥ ከሰ​ማይ ከመ​ጣው ፊታ​ች​ንን ብን​መ​ልስ እኛማ እን​ዴታ?


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios