Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘዳግም 32:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 አም​ላ​ካ​ችን እንደ አም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው አይ​ደ​ለ​ምና፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንም ሰነ​ፎች ናቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 የእነርሱ መጠጊያ ዐለት እንደ እኛ መጠጊያ ዐለት አይደለምና፤ ጠላቶቻችንም እንኳ ይህን አይክዱም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ጠላቶቻችን እንኳ እንደሚስማሙበት፥ ዓለታቸው እንደ እኛ ዓለት አይደለም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ጠላቶቻችን እንኳ እንደሚስማሙበት የእነርሱ አምላክ እንደ እኛ አምላክ አይደለም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 አምላካችን እንደ አማልክቶቻቸው አይደለም፤ 2 ጠላቶቻችንም ሰነፎች ናቸው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘዳግም 32:31
15 Referências Cruzadas  

ከሕ​ዝቡ ሁሉ በእ​ና​ንተ ዘንድ ማንም ቢሆን አም​ላኩ ከእ​ርሱ ጋር ይሁን፤ እር​ሱም በይ​ሁዳ ወዳ​ለ​ችው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይውጣ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ለሚ​ኖ​ረው አም​ላክ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትን ይሥራ፤


የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም መን​ኰ​ራ​ኵር አሰረ፤ ወደ ጭን​ቅም አገ​ባ​ቸው፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እነ​ርሱ ይዋ​ጋ​ላ​ቸ​ዋ​ልና ከእ​ስ​ራ​ኤል ፊት እን​ሽሽ” አሉ።


አሮ​ንም በግ​ብፅ ውኆች ላይ እጁን ዘረጋ፤ ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ቹም ወጡ፤ የግ​ብ​ፅ​ንም ሀገር ሸፈኑ።


ዓለ​ትም ትው​ጣ​ቸ​ዋ​ለች ድልም ይሆ​ናሉ የሸ​ሸም ይያ​ዛል። በጽ​ዮን ዘርእ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቤቶች ያሉት ብፁዕ ነው” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው አደ​ረገ፤ እር​ሱን በድ​ላ​ች​ኋ​ልና፥ ቃሉ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምና ይህ ነገር ሆነ​ባ​ችሁ።


በያ​ዕ​ቆብ ላይ ጥን​ቆላ የለም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ምዋ​ርት የለም፤ በየ​ጊ​ዜው ስለ ያዕ​ቆ​ብና ስለ እስ​ራ​ኤል፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን አደ​ረገ? ይባ​ላል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያል​ረ​ገ​መ​ውን እን​ዴት እረ​ግ​ማ​ለሁ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ያል​ተ​ጣ​ላ​ውን እን​ዴት እጣ​ላ​ለሁ?


እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ የለ​ምና፥ እንደ አም​ላ​ካ​ች​ንም ጻድቅ የለ​ምና፤ አቤቱ፥ ከአ​ን​ተም በቀር ቅዱስ የለም።


ወዮ​ልን! ከእ​ነ​ዚህ ኀያ​ላን አማ​ል​ክት እጅ ማን ያድ​ነ​ናል? እነ​ዚህ አማ​ል​ክት ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን በም​ድረ በዳ በልዩ ልዩ መቅ​ሠ​ፍት የመቱ ናቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios