Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘዳግም 30:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ፈጽ​መህ እን​ደ​ም​ት​ጠፋ እኔ ዛሬ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ረህ ትወ​ር​ሳት ዘንድ በም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር ዘመ​ንህ አይ​ረ​ዝ​ምም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በርግጥ እንደምትጠፉ እኔ በዛሬው ዕለት እነግራችኋለሁ፤ ዮርዳኖስን ተሻግረህ ትወርሳት ዘንድ በምትገባባት ምድር ብዙ አትኖሩባትም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ፈጽመህ እንደምትጠፋ እኔ ዛሬ እነግርሃለሁ፤ ዮርዳኖስን ተሻግረህ እንድትወርሳትም በምትገባባት ምድር ረጅም ዘመን አትኖርም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እንደምትደመሰስ እነሆ፥ ዛሬ አስጠነቅቅሃለሁ። ዮርዳኖስን ተሻግረህ በምትወርሳት ምድር ለረጅም ዘመን አትኖርም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ፈጽማችሁ እንድትጠፉ እኔ ዛሬ እነግራችኋለሁ፤ ዮርዳኖስን ተሻግረህ ትወርሳት ዘንድ በምትገባባት ምድር ዘመናችሁን አታስረዝሙም።

Ver Capítulo Cópia de




ዘዳግም 30:18
10 Referências Cruzadas  

እር​ሱን ትታ​ች​ሁ​ታ​ልና ዳግ​መ​ኛም በም​ድረ በዳ ትታ​ች​ሁ​ታል፤ በዚ​ችም ማኅ​በር ሁሉ ላይ ትበ​ድ​ላ​ላ​ችሁ።”


ልብህ ግን ቢስት፥ አን​ተም ባት​ሰማ፥ ብት​ታ​ለ​ልም፥ ለሌ​ሎች አማ​ል​ክ​ትም ብት​ሰ​ግድ፥ ብታ​መ​ል​ካ​ቸ​ውም፥


በዚ​ያም ቀን ቍጣዬ ይነ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ እተ​ዋ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ ፊቴ​ንም ከእ​ነ​ርሱ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም መብል ይሆ​ናሉ፤ በዚ​ያም ቀን፦ በእ​ው​ነት አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትቶ​ና​ልና፥ በእ​ኛም መካ​ከል የለ​ምና ይህ ክፉ ነገር ሁሉ አገ​ኘን እስ​ኪሉ ድረስ ብዙ ክፉ ነገ​ርና ጭን​ቀት ይደ​ር​ስ​ባ​ቸ​ዋል።


ዛሬ ወደ ማል​ሁ​ላ​ቸው ምድር ገና ሳላ​ገ​ባ​ቸው ክፋ​ታ​ቸ​ውን አው​ቃ​ለ​ሁና፥ ከአ​ፋ​ቸ​ውና ከል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም አፍ አት​ረ​ሳ​ምና ብዙ ክፉ ነገ​ርና ጭን​ቀት በደ​ረ​ሰ​ባ​ቸው ጊዜ ይህች መዝ​ሙር ምስ​ክር ሆና በፊ​ታ​ቸው ትቆ​ማ​ለች።”


ከሞ​ትሁ በኋላ ፈጽ​ማ​ችሁ እን​ድ​ት​ረ​ክሱ፥ ካዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁም መን​ገድ ፈቀቅ እን​ድ​ትሉ አው​ቃ​ለ​ሁና። በእ​ጃ​ች​ሁም ሥራ ታስ​ቈ​ጡት ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ስላ​ደ​ረ​ጋ​ችሁ፥ በኋ​ለ​ኛው ዘመን ክፉ ነገር ያገ​ኛ​ች​ኋል።”


“ልጆ​ችን፥ የልጅ ልጆ​ች​ንም በወ​ለ​ዳ​ችሁ ጊዜ፥ በም​ድ​ሪ​ቱም ረዥም ዘመን በተ​ቀ​መ​ጣ​ችሁ ጊዜ፥ በበ​ደ​ላ​ች​ሁም ጊዜ፥ በማ​ና​ቸ​ውም ቅርጽ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል ባደ​ረ​ጋ​ችሁ ጊዜ፥ ታስ​ቈ​ጡ​ትም ዘንድ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ የሆ​ነ​ውን ነገር በሠ​ራ​ችሁ ጊዜ፥


ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ራ​ችሁ ከም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር ፈጥ​ና​ችሁ እን​ድ​ት​ጠፉ እኔ ዛሬ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በእ​ና​ንተ አስ​መ​ሰ​ክ​ራ​ለሁ፤ ፈጽ​ሞም ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ እንጂ ረዥም ዘመን አት​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios