Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘዳግም 28:53 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

53 ጠላ​ቶ​ች​ህም በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ከብ​በው ባስ​ጨ​ነ​ቁ​ህና መከራ ባሳ​ዩህ ጊዜ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጥ​ህን የሆ​ድ​ህን ፍሬ፥ የወ​ን​ዶ​ችና የሴ​ቶች ልጆ​ች​ህን ሥጋ ትበ​ላ​ለህ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

53 ጠላቶችህ ከብበው በሚያስጨንቁህ ጊዜ፣ ከሥቃይ የተነሣ፣ አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህን፣ የወገብህ ፍሬ የሆኑትን የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን ሥጋ ትበላለህ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

53 “ጠላቶችህ ከበው በሚያስጨንቁህ ጊዜ፥ ከሥቃይ የተነሣ፥ ጌታ እግዚአብሔር የሰጠህን፥ የሆድህ ፍሬ የሆኑትን የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን ሥጋ ትበላለህ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

53 “ጠላቶችህ ከተሞችህን ከበው በሚያስጨንቁህም ጊዜ፥ የምትበላው አጥተህ ግራ ሲገባህ እግዚአብሔር አምላክህ የሰጠህንና የሆድህ ፍሬዎች የሆኑትን ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን ሥጋ ለመብላት ትገደዳለህ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

53 ጠላቶችህም ከብበው ባስጨነቁህና መከራ ባሳዩህ ጊዜ አምላክህ እግዚአብሔር የሚሰጥህን የሆድህን ፍሬ የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን ሥጋ ትበላለህ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘዳግም 28:53
11 Referências Cruzadas  

የወ​ን​ዶ​ችና የሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሥጋ አበ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ነፍ​ሳ​ቸ​ውን የሚ​ሹት በሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቋ​ቸው ጭን​ቀ​ትና መከ​በብ የባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ሥጋ ይበ​ላሉ።


ሬስ። አቤቱ፥ እይ፤ ተመ​ል​ከት ማንን እን​ዲህ ቃረ​ምህ? በውኑ ሴቶች የማ​ኅ​ፀ​ና​ቸ​ውን ፍሬ፥ ያሳ​ደ​ጓ​ቸ​ውን ሕፃ​ናት ይበ​ላ​ሉን? በውኑ ካህ​ኑና ነቢዩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደስ ውስጥ ይገ​ደ​ላ​ሉን?


ዮድ። የር​ኅ​ሩ​ኆች ሴቶች እጆች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ቀቅ​ለ​ዋል፤ የወ​ገኔ ሴት ልጅ በመ​ቀ​ጥ​ቀ​ጥዋ መብል ሆኖ​አ​ቸው።


ስለ​ዚህ በመ​ካ​ከ​ልሽ አባ​ቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ይበ​ላሉ፤ ልጆ​ችም አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ይበ​ላሉ፤ ፍር​ድ​ንም አደ​ር​ግ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ከአ​ን​ቺም የቀ​ረ​ውን ሁሉ ወደ ነፋ​ሳት ሁሉ እበ​ት​ና​ለሁ።


የወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም ሥጋ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ የሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም ሥጋ ትበ​ላ​ላ​ችሁ።


በዚያችም ወራት ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው።


የሆ​ድህ ፍሬ፥ የም​ድ​ር​ህም ፍሬ፥ የላ​ም​ህም መንጋ፥ የበ​ግ​ህም መንጋ ርጉ​ማን ይሆ​ናሉ።


በአ​ንተ ዘንድ የተ​ደ​ላ​ደ​ለና የተ​ቀ​ማ​ጠለ ሰው በወ​ን​ድሙ፥ አብ​ራ​ውም በም​ት​ተኛ በሚ​ስቱ፥ በቀ​ሩ​ትም ልጆቹ ይቀ​ናል፤


በከ​ተ​ሞ​ችህ ሁሉ ውስጥ ጠላ​ቶ​ችህ ከብ​በው ባስ​ጨ​ነ​ቁ​ህና መከራ ባሳ​ዩህ ጊዜ ሌላ ነገር የቀ​ረው የለ​ምና ከሚ​በ​ላው ከል​ጆቹ ሥጋ ለአ​ንዱ አይ​ሰ​ጥም።


ከአ​ካ​ልዋ የሚ​ወ​ጣ​ውን የእ​ን​ግዴ ልጅ፥ የም​ት​ወ​ል​ዳ​ቸ​ው​ንም ልጆች፤ በደ​ጆ​ችህ ውስጥ ጠላ​ቶ​ችህ፤ ከብ​በው ባስ​ጨ​ነ​ቁ​ህና መከራ ባሳ​ዩህ ጊዜ ሁሉን ስላ​ጣች በስ​ውር ትበ​ላ​ቸ​ዋ​ለች።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios