Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘዳግም 28:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የሆ​ድህ ፍሬ፥ የም​ድ​ር​ህም ፍሬ፥ የከ​ብ​ት​ህም ፍሬ፥ የላ​ም​ህም መንጋ፥ የበ​ግ​ህም መንጋ ቡሩክ ይሆ​ናል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የማሕፀንህ ፍሬ፣ የምድርህ አዝመራ፣ የእንስሳትህ ግልገሎች፣ የከብትህ ጥጃ፣ የበግና የፍየል ግልገሎችህም ይባረካሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 “የማሕፀንህ ፍሬ፥ የምድርህ አዝመራ፥ የእንስሳትህ ግልገሎች፥ የከብትህ ጥጃ፥ የበግና የፍየል ግልገሎችህም ይባረካሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 “እግዚአብሔር ልጆችህን፥ የምድር ፍሬህን፥ የቀንድ ከብትህን፥ የበግንና የፍየል መንጋህን ይባርክልሃል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የሆድህ ፍሬ፥ የምድርህም ፍሬ፥ የከብትህም ፍሬ፥ የላምህም ርቢ፥ የበግህም ርቢ ቡሩክ ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de




ዘዳግም 28:4
16 Referências Cruzadas  

ዘር​ህ​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብ​ትና በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ ፈጽሞ አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ዘር​ህም የጠ​ላት ሀገ​ሮ​ችን ይወ​ር​ሳሉ፤


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በቤቱ ባለ​ውም ሁሉ ላይ ከሾ​መው በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የግ​ብ​ፃ​ዊ​ውን ቤት በዮ​ሴፍ ምክ​ን​ያት ባረ​ከው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በረ​ከት በቤ​ቱም፥ በእ​ር​ሻ​ውም ባለው ሁሉ ላይ ሆነ።


“የእኔ አም​ላክ ረዳህ፤ ከላይ በሰ​ማይ በረ​ከት፥ ሁሉ በሚ​ገ​ኝ​ባት፥ በም​ድር በረ​ከት፥ በጡ​ትና በማ​ኅ​ፀን በረ​ከት ባረ​ከህ፤


ሚስ​ትህ በቤ​ትህ እል​ፍኝ ውስጥ እን​ደ​ሚ​ያ​ፈራ ወይን ትሆ​ና​ለች፤ ልጆ​ች​ህም በማ​ዕ​ድህ ዙሪያ እንደ አዲስ የወ​ይራ ተክል ይሆ​ናሉ።


ኃጥ​ኣን በጀ​ር​ባዬ ላይ መቱኝ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም አበ​ዙ​አት።”


የእግዚአብሔር በረከት በጻድቃን ራስ ላይ ሆና ባለጠጋ ታደርጋለች፥ ኀዘንንም ወደ ልብ አታመጣም።


ደግ ሰው ለልጅ ልጅ ያወርሳል፥ የኀጢአተኞች ብልጽግና ግን ለጻድቃን ይደልባል።


ያለ ነውር ወደ እውነት በንጹሕ የሚሄድ፥ ልጆቹን ብፁዓን ያደርጋቸዋል።


ወደ እና​ን​ተም እመ​ለ​ከ​ታ​ለሁ፤ አባ​ዛ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከፍ ከፍም አደ​ር​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤ ቃል ኪዳ​ኔ​ንም ከእ​ና​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እር​ስ​ዋን ይሰ​ጥህ ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ችህ በማ​ለ​ላ​ቸው በም​ድ​ርህ ላይ፥ በሆ​ድህ ፍሬ፥ በእ​ር​ሻ​ህም ፍሬ፥ ከብ​ቶ​ች​ህን በማ​ብ​ዛት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ​ነ​ቱን ያበ​ዛ​ል​ሃል።


የሆ​ድህ ፍሬ፥ የም​ድ​ር​ህም ፍሬ፥ የላ​ም​ህም መንጋ፥ የበ​ግ​ህም መንጋ ርጉ​ማን ይሆ​ናሉ።


አንተ በከ​ተማ ቡሩክ ትሆ​ና​ለህ፤ በእ​ር​ሻም ቡሩክ ትሆ​ና​ለህ።


መዛ​ግ​ብ​ት​ህና የቀ​ረ​ውም ሁሉ ቡሩክ ይሆ​ናል።


ይወ​ድ​ድ​ህ​ማል፤ ይባ​ር​ክ​ህ​ማል፤ ያባ​ዛ​ህ​ማል፤ ይሰ​ጥ​ህም ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ችህ በማ​ለ​ላ​ቸው ምድር የሆ​ድ​ህን ፍሬ፥ የመ​ሬ​ት​ህ​ንም ፍሬ፥ እህ​ል​ህን፥ ወይ​ን​ህ​ንም፥ ዘይ​ት​ህ​ንም፥ የከ​ብ​ት​ህ​ንም ብዛት፥ የበ​ግ​ህ​ንም መንጋ ይባ​ር​ክ​ል​ሃል።


ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios