Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘዳግም 24:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 “ስለ ለምጽ ደዌ ሌዋ​ው​ያን ካህ​ናት ያስ​ተ​ማ​ሩ​ህን ሁሉ ፈጽ​መህ እን​ድ​ት​ጠ​ብቅ እን​ድ​ታ​ደ​ር​ግም ተጠ​ን​ቀቅ፤ እኔ ያዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ውን እን​ዲሁ ታደ​ርግ ዘንድ ጠብቅ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የለምጽ ደዌን በተመለከተ ሌዋውያን ካህናት የሚሰጡህን መመሪያ በትክክል ለመፈጸም ጥንቃቄ አድርግ። እኔ ለእነርሱ የሰጠሁትን ትእዛዝ በጥንቃቄ ተከተል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 “የለምጽ ደዌን በተመለከተ ሌዋውያን ካህናት የሚሰጡህን መመሪያ በትክክል ለመፈጸም ጥንቃቄ አድርግ። እኔ ለእነርሱ የሰጠሁትን ትእዛዝ በጥንቃቄ ተከተል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 “ብርቱ ጥንቃቄ በማድረግ ከሥጋ ደዌ በሽታ ተጠበቁ፤ እኔ ባዘዝኳቸው መሠረት ሌዋውያን ካህናት የሚሰጡአችሁን መመሪያ በጥንቃቄ ጠብቁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በለምጽ ደዌ ሌዋውያን ካህናት ያስተማሩህን ሁሉ ፈጽመህ እንድትጠብቅ እንድታደርግም ተጠንቀቅ፤ እኔ ያዘዝኋቸውን እንዲሁ ታደርግ ዘንድ ጠብቅ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘዳግም 24:8
11 Referências Cruzadas  

የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ቀ​ርብ፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን የሚ​ያ​ቃ​ጥል፥ ሁል​ጊ​ዜም የሚ​ሠዋ ሰው ከሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት ዘንድ በእኔ ፊት አይ​ታ​ጣም።”


በል​ብ​ሱም ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከቆዳ በተ​ደ​ረገ ነገር ላይ ደግሞ ቢታይ፥ የወጣ ለምጽ ነው፤ ደዌው ያለ​በ​ትን ነገር ያቃ​ጥ​ሉት።


ካህ​ኑም ከበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ደም ወስዶ የሚ​ነ​ጻ​ውን ሰው የቀኝ ጆሮ​ውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁ​ንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግ​ሩ​ንም አውራ ጣት ይቀ​ባ​ዋል።


“ለምጽ ለያ​ዘው ሰው ሕጉ ይህ ነው፤ ከለ​ምጽ በነ​ጻ​በት ቀን ወደ ካህኑ ይወ​ስ​ዱ​ታል።


በሚ​ረ​ክ​ስና በሚ​ነጻ ጊዜ እን​ዲ​ያ​ስ​ታ​ውቅ ይህ የለ​ምጽ ሕግ ነው።”


ኢየሱስም “ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ሙሴ ያዘዘውን መባ አቅርብ” አለው።


“ለማንም አንዳች እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ ያዘዘውን አቅርብ፤” አለው።


ባያ​ቸ​ውም ጊዜ፥ “ወደ ካህን ሂዱና ራሳ​ች​ሁን አስ​መ​ር​ምሩ” አላ​ቸው፤ ሲሄ​ዱም ነጹ።


ለማ​ንም እን​ዳ​ይ​ና​ገር ከለ​ከ​ለው፤ “ነገር ግን ሄደህ ራስ​ህን ለካ​ህን አስ​መ​ር​ምር፤ ምስ​ክ​ርም ይሆ​ን​ባ​ቸው ዘንድ ስለ ነጻህ ሙሴ እንደ አዘዘ መባ​ህን አቅ​ርብ” ብሎ አዘ​ዘው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios