Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘዳግም 22:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 በእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ላይ ክፉ ስም አም​ጥ​ቶ​አ​ልና መቶ የብር ሰቅል ያስ​ከ​ፍ​ሉት፤ ለብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም አባት ይስ​ጡት፤ እር​ስ​ዋም ሚስት ትሁ​ነው፤ በዕ​ድ​ሜ​ውም ዘመን ሁሉ ሊፈ​ታት አይ​ገ​ባ​ውም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ይህ ሰው የአንዲት እስራኤላዊት ድንግል ስም አጥፍቷልና አንድ መቶ ሰቅል ብር ያስከፍሉት፤ ገንዘቡንም ለልጅቱ አባት ይስጡት፤ ሴቲቱም ሚስቱ ሆና ትኖራለች፤ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሊፈታት አይችልም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በእስራኤል ድንግል ላይ ክፉ ስም አምጥቶአልና መቶ የብር ሰቅል በማስከፈል ለብላቴናይቱም አባት ይስጡት፥ እርሷም ሚስቱ ሆና ትኑር፥ በዕድሜውም ዘመን ሁሉ ሊፈታት አይገባውም።”

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በተጨማሪም አንድ መቶ ጥሬ ብር መቀጫ አስከፍለው ገንዘቡን ለልጅትዋ አባት ይስጡት፤ ያ ሰው ድንግል የሆነችውን የአንዲት እስራኤላዊት ልጃገረድ ስም አጒድፎአል፤ ከዚህም በቀር የእርሱ ሚስት ሆና ትኖራለች፤ እስከ ሕይወቱ ፍጻሜ ድረስ ሊፈታት አይገባም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 በእስራኤል ድንግል ላይ ክፉ ስም አምጥቶአልና መቶ የብር ሰቅል ያስከፍሉት፥ ለብላቴናይቱም አባት ይስጡት፤ እርስዋም ሚስት ትሁነው፥ በዕድሜውም ዘመን ሁሉ ሊፈታት አይገባውም።

Ver Capítulo Cópia de




ዘዳግም 22:19
6 Referências Cruzadas  

“ሁለት ሰዎች እርስ በር​ሳ​ቸው ቢጣሉ፥ ያረ​ገ​ዘ​ች​ንም ሴት ቢያ​ቈ​ስሉ ተሥ​ዕ​ሎተ መል​ክእ ያል​ተ​ፈ​ጸ​መ​ለት ፅን​ስም ቢያ​ስ​ወ​ር​ዳት፥ የሴ​ቲቱ ባል የጣ​ለ​በ​ትን ያህል ካሳ ይክ​ፈል፤


የዚ​ያች ከተማ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ያን ሰው ወስ​ደው ይገ​ሥ​ጹት፤


“ነገሩ ግን እው​ነት ቢሆን፥ የብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም ድን​ግ​ል​ናዋ ባይ​ገኝ፥


ያ የደ​ፈ​ራት ሰው አምሳ የብር ሰቅል ለብ​ላ​ቴ​ና​ዪቱ አባት ይስጥ፤ አስ​ነ​ው​ሮ​አ​ታ​ልና ሚስት ትሁ​ነው፤ በዕ​ድ​ሜ​ውም ዘመን ሁሉ ሊፈ​ታት አይ​ገ​ባ​ውም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios