Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘዳግም 2:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እነ​ር​ሱም ደግሞ እንደ ዔና​ቃ​ው​ያን ራፋ​ይም ተብ​ለው ይታ​ወቁ ነበር፤ ሞዓ​ባ​ው​ያን ግን “ኦሚን” ብለው ይጠ​ሩ​አ​ቸው ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እነዚህም እንደ ዔናቃውያን ሁሉ ራፋይማውያን ናቸው ተብለው ይገመቱ ነበር፤ ሞዓባውያን ግን ኤሚማውያን ብለው ይጠሯቸዋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እነርሱም ደግሞ እንደ ዔናቅ ልጆች ራፋይም ይባሉ ነበር፥ ሞዓባውያን ግን ኤሚም ይሉአቸዋል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እንደ ዐናቃውያንም ረፋያውያን ተብለው ይጠሩ ነበር። ሞአባውያን ግን ኤሚማውያን ብለው ይጠሩአቸው ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እነርሱም ደግሞ እንደ ዔናቅ ልጆች ራፋይም ይባሉ ነበር፤ ሞዓባውያን ግን ኤሚም ይሉአቸዋል።

Ver Capítulo Cópia de




ዘዳግም 2:11
10 Referências Cruzadas  

በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ኮሎ​ዶ​ጎ​ሞ​ርና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ነገ​ሥ​ታት መጡ፤ ረዐ​ይ​ትን በአ​ስ​ጣ​ሮት ቃር​ና​ይም፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ጽኑ​ዓን ሰዎ​ች​ንና ኦሚ​ዎ​ስን በሴዊ ከተማ ገደ​ሉ​አ​ቸው፤


በእ​ነ​ዚ​ያም ወራት ረዓ​ይት በም​ድር ላይ ነበሩ። ከዚ​ያም በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ወደ ሰው ሴቶች ልጆች በገቡ ጊዜ ልጆ​ችን ወለ​ዱ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም በዱሮ ዘመን ስማ​ቸ​ውን ያስ​ጠሩ ኀያ​ላን ሰዎች ሆኑ።


ከራ​ፋ​ይም ወገን የነ​በ​ረው ኤስቢ መጣ፤ የጦ​ሩም ሚዛን ክብ​ደት ሦስት መቶ ሰቅል ናስ ነበር። አዲስ የጦር መሣ​ሪ​ያም ታጥቆ ነበር፤ ዳዊ​ት​ንም ሊገ​ድ​ለው ፈለገ።


ወደ ምድረ በዳም ወጡ፤ ወደ ኬብ​ሮ​ንም ደረሱ፤ በዚ​ያም የዔ​ናቅ ዘሮች አኪ​ማን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ኬብ​ሮ​ንም በግ​ብፅ ካለ​ችው ከጣ​ኔ​ዎስ ከተማ በፊት ሰባት ዓመ​ታት ተሠ​ርታ ነበር።


ነገር ግን በም​ድ​ሪቱ የሚ​ኖሩ ሰዎች ኀያ​ላን ናቸው፤ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም የተ​መ​ሸጉ፥ እጅ​ግም የጸኑ ታላ​ላቅ ናቸው።


በዚ​ያም ግዙ​ፋን የሆ​ኑ​ትን አየን፤ እኛም በእ​ነ​ርሱ ፊት እንደ አን​በ​ጣ​ዎች ሆን፤ እን​ዲ​ሁም በፊ​ታ​ቸው ነበ​ርን፤” እያሉ የሰ​ለ​ሉ​አ​ትን ምድር ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አስ​ፈሪ አደ​ረ​ጓት።


ወዴት እን​ወ​ጣ​ለን? ሕዝቡ ታላ​ቅና ብዙ ነው፤ ከእ​ኛም ይጠ​ነ​ክ​ራሉ፤ ከተ​ሞ​ቹም ታላ​ላ​ቆች፥ የተ​መ​ሸ​ጉም፥ እስከ ሰማ​ይም የደ​ረሱ ናቸው፤ የረ​ዐ​ይ​ት​ንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየ​ና​ቸው ብለው ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ልባ​ች​ንን አስ​ፈ​ሩት።’


ያም ደግሞ የራ​ፋ​ይም ምድር ተብሎ ተቈ​ጠረ፤ ራፋ​ይ​ምም አስ​ቀ​ድሞ በዚያ ተቀ​ም​ጠው ነበረ፤ አሞ​ና​ው​ያን ግን “ዘም​ዞ​ማ​ው​ያን” ብለው ይጠ​ሩ​አ​ቸ​ዋል።


ከራ​ፋ​ይ​ንም ወገን የባ​ሳን ንጉሥ ዐግ ብቻ​ውን ቀርቶ ነበር፤ እነሆ፥ አል​ጋው የብ​ረት አልጋ ነበረ፤ እርሱ በአ​ሞን ልጆች ሀገር ዳርቻ አለ፤ ርዝ​መቱ ዘጠኝ ክንድ ወር​ዱም አራት ክንድ በሰው ክንድ ልክ ነበረ።


አን​ተም የም​ታ​ው​ቃ​ቸው፥ ስለ እነ​ር​ሱም፦ በዔ​ናቅ ልጆች ፊት መቆም ማን ይች​ላል? ሲባል የሰ​ማ​ኸው ታላቅ፥ ብዙና ረዥም ሕዝብ የዔ​ናቅ ልጆች ናቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios