Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘዳግም 19:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሰው ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ጋር እን​ጨት ሊለ​ቅም ወደ ዱር ቢሄድ፥ ዛፉ​ንም ሲቈ​ርጥ ምሳሩ ከእጁ ቢወ​ድቅ፥ ብረ​ቱም ከእ​ጄ​ታው ቢወ​ልቅ፥ በባ​ል​ን​ጀ​ራ​ውም ላይ ቢወ​ድ​ቅና ቢገ​ድ​ለው፥ ከእ​ነ​ዚህ ከተ​ሞች በአ​ን​ዲቱ ተማ​ጥኖ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፤

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እነሆ፤ አንድ ሰው ከባልንጀራው ጋራ ዕንጨት ለመቍረጥ ወደ ጫካ ቢሄድ፣ ዛፉን ለመጣል መጥረቢያውን በሚሰነዝርበት ጊዜ ብረቱ ከእጀታው ወልቆ ባልንጀራውን በመምታት ቢገድለው፣ ያ ሰው ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ በመሸሽ ሕይወቱን ማትረፍ ይችላል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አንድ ሰው ከባልንጀራው ጋር እንጨት ሊቆርጥ ወደ ጫካ ቢሄድ፥ ዛፉን ለመጣል መጥረቢያውን በሚሰነዝርበት ጊዜ ብረቱ ከእጀታው ወልቆ ባልንጀራውን በመምታት ቢገድለው፥ ያ ሰው ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ በመሸሽ ሕይወቱን ማትረፍ ይችላል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ለምሳሌ፥ ሁለት ሰዎች እንጨት ለመቊረጥ ቢሄዱና አንደኛው እንጨቱን ሲቈርጥ የመጥረቢያው ራስ ከዛቢያው ወልቆ በድንገት ሲወረወር ሌላውን ሰው መትቶ ቢገድል፥ ገዳዩ ከእነዚህ ከሦስት ከተማዎች ወደ አንዲቱ ሄዶ ሕይወቱን ያትርፍ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5-6 ሰው ከባልንጀራው ጋር እንጨት ሊቈርጥ ወደ ዱር ቢሄድ፥ ዛፉንም ሊቈርጥ ምሳሩን ሲያነሣ ብረቱ ከእጀታው ቢወልቅ፥ ባልንጀራውንም እስኪሞት ድረስ ቢመታው፥ ደም ተበቃዩ ነፍሰ ገዳዩን በልቡ ተናድዶ እንዳያሳድደው መንገዱም ሩቅ ስለ ሆነ አግኝቶ እንዳይገድለው፥ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ ሸሽቶ በሕይወት ይኖራል፤ አስቀድሞ ጠላቱ፤ አልነበረምና ሞት አይገባውም።

Ver Capítulo Cópia de




ዘዳግም 19:5
7 Referências Cruzadas  

ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሄደ፤ ወደ ዮር​ዳ​ኖ​ስም በደ​ረሱ ጊዜ እን​ጨት ቈረጡ።


ሰውም ቃሉን ይሰ​ው​ራል፤ በውኃ እን​ደ​ሚ​ጠ​ል​ቅም ይሰ​ወ​ራል፤ ክብ​ሩም በደ​ረቅ ምድር እን​ደ​ሚ​ፈ​ስስ ውኃ በጽ​ዮን ይገ​ለ​ጣል።


ማኅ​በ​ሩም ነፍሰ ገዳ​ዩን ከባለ ደሙ እጅ ያድ​ኑ​ታል፤ ማኅ​በ​ሩም ወደ ሸሸ​በት ወደ መማ​ፀ​ኛው ከተማ ይመ​ል​ሱ​ታል፤ በቅ​ዱስ ዘይ​ትም የተ​ቀ​ባው ታላቁ ካህን እስ​ኪ​ሞት ድረስ በዚያ ይቀ​መ​ጣል።


“የነ​ፍሰ ገዳይ ሕግ ይህ ነው፤ ቀድሞ ጠላቱ ሳይ​ሆን ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ሳያ​ውቅ የገ​ደለ ወደ​ዚያ ሸሽቶ በሕ​ይ​ወት ይኑር።


ባለ ደሙ ነፍሰ ገዳ​ዩን በልቡ ተና​ድዶ እን​ዳ​ያ​ሳ​ድ​ደው መን​ገ​ዱም ሩቅ ስለ​ሆነ አግ​ኝቶ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ለው፥ አስ​ቀ​ድሞ ጠላቱ አል​ነ​በ​ረ​ምና ሞት አይ​ገ​ባ​ውም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios