Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘዳግም 17:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ለእ​ርሱ ፈረ​ሶ​ችን እን​ዳ​ያ​በዛ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ወደ ግብፅ እን​ዳ​ይ​መ​ልስ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በዚ​ያች መን​ገድ መመ​ለ​ስን አት​ድ​ገም ብሎ​አ​ልና።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ንጉሡም ብዙ ፈረሶችን ለራሱ አያብዛ፤ ወይም ደግሞ የፈረሰኞችን ቍጥር ለመጨመር ሕዝቡን ወደ ግብጽ አይመልስ፤ እግዚአብሔር፣ “በዚያ መንገድ ፈጽሞ አትመለሱ” ብሏችኋልና።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ንጉሡም ብዙ ፈረሶችን ለራሱ አያብዛ፤ ወይም ደግሞ ፈረሰኞች ለማብዛት ሕዝቡን ወደ ግብጽ አይመልስ፤ ጌታ፥ ‘በዚያ መንገድ ፈጽሞ አትመለሱ’ ብሎአችኋልና።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ያም ንጉሥ ለሠራዊቱ ብዙ ፈረሶች ያሉት መሆን የለበትም፤ እግዚአብሔር ሕዝቡ ወደ ግብጽ እንዳይመለሱ ስለ አዘዘ ፈረሶችን ለመግዛት ወደ እዚያ ሰዎችን አይላክ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ነገር ግን ለእርሱ ፈረሶችን አያበዛም፤ እግዚአብሔር፦ በዚያ መንገድ ደግማችሁ አትመለሱም ብሎአችኋልና ፈረሶችን ለማብዛት ሕዝቡን ወደ ግብፅ አይመልስም።

Ver Capítulo Cópia de




ዘዳግም 17:16
23 Referências Cruzadas  

ዳዊ​ትም ከእ​ርሱ ሺህ ሰረ​ገ​ላ​ዎ​ችን፥ ሰባት ሺህ ፈረ​ሰ​ኞ​ችን፥ ሃያ ሺህም እግ​ረ​ኞ​ችን ያዘ፤ ዳዊ​ትም የሰ​ረ​ገ​ለ​ኛ​ውን ፈረስ ሁሉ ቋንጃ ቈረጠ፤ ለራ​ሱም መቶ ሰረ​ገ​ላ​ዎ​ችን ብቻ አስ​ቀረ።


የአ​ጊ​ትም ልጅ አዶ​ን​ያስ፥ “ንጉሥ እሆ​ና​ለሁ” ብሎ ተነሣ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን በፊ​ቱም የሚ​ሮጡ አምሳ ሰዎ​ችን አዘ​ጋጀ።


ለሰ​ሎ​ሞ​ንም ሰረ​ገላ የሚ​ስቡ አርባ ሺህ ፈረ​ሶች፥ ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረ​ሰ​ኞች ነበ​ሩት።


አሁ​ንም ከወ​ገኔ እንደ ሲዶ​ና​ው​ያን እን​ጨት መቍ​ረጥ የሚ​ያ​ውቅ እን​ደ​ሌለ ታው​ቃ​ለ​ህና የዝ​ግባ ዛፍ ከሊ​ባ​ኖስ ይቈ​ር​ጡ​ልኝ ዘንድ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን እዘዝ፤ አገ​ል​ጋ​ዮቼም ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ጋር ይሁኑ፤ የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህ​ንም ዋጋ እንደ ተና​ገ​ር​ኸው ሁሉ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።”


የሰ​ሎ​ሞን ፈረ​ሶች መምጫ ከግ​ብ​ፅና ከቴ​ቁሄ ምድር ነበር። በዋጋ ገዝ​ተው ከቴ​ቁሄ የሚ​ያ​መ​ጡ​አ​ቸ​ውም ከሀ​ገር ሽማ​ግ​ሌ​ዎች የሆኑ የሰ​ሎ​ሞን ነጋ​ዴ​ዎች ነበሩ።


ሰሎ​ሞ​ንም ለሰ​ረ​ገ​ሎች አራት ሺህ እን​ስት ፈረ​ሶ​ችና ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረ​ሰ​ኞች ነበ​ሩት፤ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም ከተ​ሞች፥ ከን​ጉሡ ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አኖ​ራ​ቸው።


ንጉሥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተማ​ም​ኖ​አ​ልና፥ በል​ዑ​ልም ምሕ​ረት አይ​ና​ወ​ጥም።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ፈር​ዖን ሕዝ​ቡን በለ​ቀቀ ጊዜ፥ ምንም ቅርብ ቢሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ምድር መን​ገድ አል​መ​ራ​ቸ​ውም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ሕዝቡ ሰል​ፉን በአየ ጊዜ እን​ዳ​ይ​ጸ​ጽ​ተው፥ ወደ ግብ​ፅም እን​ዳ​ይ​መ​ለስ” ብሎ​አ​ልና።


ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን በዙ​ሪያ መን​ገድ በኤ​ር​ትራ ባሕር ባለ​ችው ምድረ በዳ መራ​ቸው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ትው​ልድ ከግ​ብፅ ምድር ወጡ።


ሙሴም ለሕ​ዝቡ፥ “አት​ፍሩ፤ ዛሬ የም​ታ​ዩ​አ​ቸ​ውን ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አታ​ዩ​አ​ቸ​ው​ምና ቁሙ፤ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማዳን እዩ።


ምድ​ራ​ቸ​ውም በብ​ርና በወ​ርቅ ተሞ​ል​ታ​ለች፤ ለመ​ዛ​ግ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቍጥር የለ​ውም፤ ምድ​ራ​ቸ​ውም ደግሞ በፈ​ረ​ሶች ተሞ​ል​ታ​ለች፤ ለሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም ቍጥር የለ​ውም።


እና​ንተ የይ​ሁዳ ቅሬታ ሆይ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ወደ ግብፅ አት​ግቡ ብሎ ተና​ግ​ሮ​ባ​ች​ኋ​ልና ዛሬ እን​ዳ​ስ​ጠ​ነ​ቀ​ቅ​ኋ​ችሁ በእ​ር​ግጥ ዕወቁ።


እርሱ ግን በእ​ርሱ ላይ ሸፈተ፤ ፈረ​ሶ​ች​ንና ብዙ​ንም ሕዝብ ይሰ​ጡት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ወደ ግብፅ ላከ። በውኑ ይከ​ና​ወ​ን​ለት ይሆን? ይህ​ንስ ያደ​ረገ ያመ​ል​ጣ​ልን? ቃል ኪዳ​ን​ንስ ያፈ​ረሰ ያመ​ል​ጣ​ልን?


ኤፍ​ሬም በግ​ብፅ ተቀ​መጠ፤ አሦ​ርም ንጉሡ ነው፤ መመ​ለ​ስን እንቢ ብሎ​አ​ልና።


ከእ​ና​ንተ ጋር ቃልን ውሰዱ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተመ​ለሱ። እን​ዲ​ህም በሉት፥ “ኀጢ​አ​ትን ሁሉ አስ​ወ​ግድ፤ በቸ​ር​ነ​ትም ተቀ​በ​ለን፤ በወ​ይ​ፈ​ንም ፈንታ የከ​ን​ፈ​ራ​ች​ንን ፍሬ ለአ​ንተ እን​ሰ​ጣ​ለን።


በዚያም ቀን ፈረሶችህን ከመካከልህ አጠፋለሁ፥ ሰረገሎችህንም እሰብራለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥


ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ተመ​ል​ሰህ አታ​ያ​ትም ባል​ሁህ መን​ገ​ድም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ር​ከብ ወደ ግብፅ ይመ​ል​ስ​ሃል፤ በዚ​ያም ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ወን​ዶ​ችና ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮች ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ የሚ​ራ​ራ​ላ​ች​ሁም አይ​ኖ​ርም።”


እን​ዲ​ህም አለ፥ “በእ​ና​ንተ ላይ የሚ​ነ​ግ​ሠው የን​ጉሡ ሥር​ዐት ይህ ነው፤ ወን​ዶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን ወስዶ ሰረ​ገላ ነጂ​ዎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞች ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም ፊት ይሮ​ጣሉ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios