Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘዳግም 16:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 “ለአ​ንተ በም​ት​ሠ​ራው በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ አጠ​ገብ ከማ​ና​ቸ​ውም ዛፍ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐጸድ አድ​ር​ገህ አት​ት​ከል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በምትሠራው መሠዊያ አጠገብ የአሼራን ምስል የዕንጨት ዐምድ አታቁም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 “ለአንተ በምትሠራው በአምላክህ በጌታ መሠዊያ አጠገብ ከማናቸውም ዛፍ የማምለኪያ ዐፀድ አድርገህ አትትከል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሠዊያ በምትሠራበት አጠገብ የማምለኪያ ዐፀድ (ዛፍ) አትትከል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ለአንተ በምትሠራው በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ አጠገብ ከማናቸውም ዛፍ የማምለኪያ ዐፀድ አድርገህ አትትከል።

Ver Capítulo Cópia de




ዘዳግም 16:21
10 Referências Cruzadas  

በዚያ ጊዜም ሸም​በቆ በውኃ ውስጥ እን​ደ​ሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ እስ​ራ​ኤ​ልን ይመ​ታል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያስ​ቈጡ ዘንድ የማ​ም​ለ​ኪያ አፀድ ተክ​ለ​ዋ​ልና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ከሰ​ጣ​ቸው ከዚች ከመ​ል​ካ​ሚቱ ምድር እስ​ራ​ኤ​ልን ይነ​ቅ​ላል፤ በወ​ን​ዙም ማዶ ይበ​ት​ና​ቸ​ዋል።


አክ​ዓ​ብም የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ድን አሠራ፤ አክ​ዓ​ብም ሰው​ነቱ እን​ድ​ት​ጠፋ ከእ​ርሱ በፊት ከነ​በ​ሩት ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ይልቅ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​ስ​ቈ​ጣ​ውን ነገር አበዛ።


የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ሁሉ ተዉ፤ ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም የሁ​ለ​ቱን እን​ቦ​ሶች ምስ​ሎች አደ​ረጉ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ድ​ንም ተከሉ፤ ለሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ ሰገዱ፤ በዓ​ል​ንም አመ​ለኩ።


አባ​ቱም ሕዝ​ቅ​ያስ ያፈ​ረ​ሳ​ቸ​ውን የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎች መልሶ ሠራ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አክ​ዓብ እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ለበ​ዓል መሠ​ዊ​ያን ሠራ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ድ​ንም ተከለ፤ ለሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ ሰገደ አመ​ለ​ካ​ቸ​ውም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለዳ​ዊ​ትና ለልጁ ለሰ​ሎ​ሞን፥ “በዚህ ቤት ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገድ ሁሉ በመ​ረ​ጥ​ኋት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስሜን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አኖ​ራ​ለሁ፤


አባ​ቱም ሕዝ​ቅ​ያስ ያፈ​ረ​ሳ​ቸ​ውን የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎች መልሶ ሠራ፤ ለበ​ዓ​ሊ​ምም መሠ​ዊያ ሠራ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ች​ንም ተከለ፤ ለሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ ሰገደ፤ አመ​ለ​ካ​ቸ​ውም።


ነገር ግን መሠ​ው​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውን ታፈ​ር​ሳ​ላ​ችሁ፤ ሐው​ል​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ትሰ​ብ​ራ​ላ​ችሁ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ቻ​ቸ​ውን ትቈ​ር​ጣ​ላ​ችሁ፤ ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ላ​ችሁ፤


“ለእ​ና​ንተ በእጅ የተ​ሠራ ጣዖት አታ​ድ​ርጉ፤ የተ​ቀ​ረ​ጸም ምስል ወይም ሐው​ልት አታ​ቁሙ፤ ትሰ​ግ​ዱ​ለ​ትም ዘንድ በም​ድ​ራ​ችሁ ላይ የተ​ቀ​ረጸ ድን​ጋይ አታ​ኑሩ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።


ነገር ግን እን​ዲህ አድ​ር​ጉ​ባ​ቸው፤ መሠ​ዊ​ያ​ቸ​ውን አፍ​ርሱ፤ ሐው​ል​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሰባ​ብሩ፥ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ቍረጡ፥ የአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ምስል በእ​ሳት አቃ​ጥሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረጉ፤ አም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረስ​ተው በዓ​ሊ​ም​ንና አስ​ታ​ሮ​ትን አመ​ለኩ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios