Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘዳግም 15:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ረ​ጠው ስፍራ አን​ተና ቤተ ሰብህ በየ​ዓ​መቱ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ብላው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እርሱ በሚመርጠው ስፍራ አንተና ቤተ ሰብህ በየዓመቱ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ትበሉታላችሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እርሱ በሚመርጠው ስፍራ አንተና ቤተሰብህ በየዓመቱ በአምላክህ በጌታ ፊት ትበሉታላችሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እነርሱንም እግዚአብሔር በሚመርጠው ቦታ በየዓመቱ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ከቤተሰብህ ጋር ትበላቸዋለህ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 አምላክህ እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ አንተና ቤተሰብህ በየዓመቱ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ብሉአቸው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘዳግም 15:20
6 Referências Cruzadas  

“ለም​ስ​ጋና የሚ​ሆ​ነው የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሥጋም ለእ​ርሱ ነው፤ በሚ​ቀ​ር​ብ​በ​ትም ቀን ይበ​ሉ​ታል፤ ከእ​ርሱ እስከ ነገ ምንም አያ​ተ​ር​ፉም።


በዚ​ያን ጊዜ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ ወደ​ዚያ ወደ መረ​ጠው ስፍራ፥ እኔ የማ​ዝ​ዛ​ች​ሁን ሁሉ፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ ቍር​ባ​ና​ች​ሁ​ንም፥ ዐሥ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ ከእ​ጃ​ችሁ ሥራ ቀዳ​ም​ያ​ቱን የተ​መ​ረ​ጠ​ው​ንም መባ​ች​ሁን ሁሉ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም የተ​ሳ​ላ​ች​ሁ​ትን ሁሉ ውሰዱ።


ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከነ​ገ​ዶ​ችህ ከአ​ንዱ ዘንድ በመ​ረ​ጠው ስፍራ በዚያ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን አቅ​ርብ፤ በዚ​ያም ዛሬ እኔ የማ​ዝ​ዝ​ህን ሁሉ አድ​ርግ።


የእ​ህ​ል​ህን፥ የወ​ይን ጠጅ​ህን፥ የዘ​ይ​ት​ህ​ንም ዐሥ​ራት፥ የላ​ም​ህ​ንና የበ​ግ​ህ​ንም በኵ​ራት፥ የተ​ሳ​ል​ኸ​ው​ንም ስእ​ለት ሁሉ፥ በፈ​ቃ​ድህ ያቀ​ረ​ብ​ኸ​ውን፥ የእ​ጅ​ህ​ንም ቀዳ​ም​ያት በከ​ተ​ሞ​ችህ ሁሉ ውስጥ መብ​ላት አት​ች​ልም።


በዘ​መ​ን​ህም ሁሉ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራ​ትን ትማር ዘንድ፥ ስሙ እን​ዲ​ጠ​ራ​በት በመ​ረ​ጠው ስፍራ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የእ​ህ​ል​ህን፥ የወ​ይ​ን​ህን፥ የዘ​ይ​ት​ህ​ንም ዐሥ​ራት፥ የላ​ም​ህ​ንና የበ​ግ​ህ​ንም በኵ​ራት ብላ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios