Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘዳግም 13:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ዛሬም እኔ የማ​ዝ​ዝ​ህን ትእ​ዛዝ ሁሉ ብት​ጠ​ብቅ፥ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካ​ምና ጥሩ የሆ​ነ​ውን ብታ​ደ​ርግ፥ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ብት​ሰማ ለእ​ርሱ ልጅ ትሆ​ና​ለህ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ይህም የሚሆነው ዛሬ እኔ የምሰጥህን ትእዛዞቹን ሁሉ በመጠበቅና መልካም የሆነውን በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት በማድረግ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስለ ታዘዝህለት ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ይህም የሚሆነው፥ ዛሬ እኔ የማዝዝህን ትእዛዝ ሁሉ ከጠበቅህ፥ በጌታ በአምላክህ ፊት ትክክል የሆነውን ካደረግህ፥ የጌታ የአምላክህን ቃል ከሰማህ ነው።”

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ዛሬ እኔ የሰጠሁህን ትእዛዞች ብትጠብቅና እርሱ ከአንተ የሚፈልገውንም ሁሉ ብታደርግ ይህ ተስፋ በእርግጥ ይፈጸምልሃል።

Ver Capítulo Cópia de




ዘዳግም 13:18
12 Referências Cruzadas  

ዘር​ህ​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብ​ትና በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ ፈጽሞ አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ዘር​ህም የጠ​ላት ሀገ​ሮ​ችን ይወ​ር​ሳሉ፤


ሰላ​ምን ከሚ​ጠሉ ጋር ነፍሴ ብዙ ጊዜ ታገ​ሠች።


ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።


በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ!’ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።


“ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዐለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል።


በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካ​ምና ጥሩ የሆ​ነ​ውን ነገር ስታ​ደ​ርግ ለአ​ንተ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ችህ መል​ካም እን​ዲ​ሆ​ን​ላ​ችሁ፥ አት​ብ​ላው።


በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካ​ምና ጥሩ የሆ​ነ​ውን ነገር ስታ​ደ​ርግ ለአ​ንተ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ችህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም መል​ካም ይሆ​ን​ላ​ችሁ ዘንድ እኔ የማ​ዝ​ዝ​ህን እነ​ዚ​ህን ቃሎች ሁሉ ሰም​ተህ ጠብቅ።


“እኔ ዛሬ የማ​ዝ​ዝ​ህን ነገር ሁሉ ታደ​ር​ገው ዘንድ ጠብቅ፤ ምንም በእ​ርሱ ላይ አት​ጨ​ምር፤ ከእ​ር​ሱም ምንም አታ​ጕ​ድል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ቅ​ሠ​ፍቱ ቍጣ ይመ​ለስ ዘንድ፥ ለአ​ባ​ቶ​ች​ህም እንደ ማለ​ላ​ቸው ይም​ርህ ዘንድ፥ ይራ​ራ​ል​ህም ዘንድ፥ ያበ​ዛ​ህም ዘንድ፥ ርጉም ከሆ​ነው አን​ዳች ነገር በእ​ጅህ አት​ንካ።


“ለሞተ ሰውም በዐ​ይ​ና​ችሁ መካ​ከል ፊታ​ች​ሁን አት​ንጩ፤ ራሳ​ች​ሁ​ንም አት​ላጩ፤


ርኩ​ስን ነገር ወደ ቤትህ አታ​ግባ፤ እንደ እር​ሱም ርጉም ትሆ​ና​ለህ፤ ርጉም ነውና መጸ​የ​ፍን ተጸ​የ​ፈው፤ መጥ​ላ​ት​ንም ጥላው።


በላ​ዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድ​ን​ጋይ ክምር ከመሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት ተመ​ለሰ። ስለ​ዚ​ህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ዔሜ​ቃ​ኮር ተብሎ ተጠራ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios