Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘዳግም 12:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 “አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ረህ ድን​በ​ር​ህን ባሰ​ፋ​ልህ ጊዜ፥ ሰው​ነ​ት​ህም ሥጋ መብ​ላት ስለ ወደ​ደች፦ ሥጋ ልብላ ስትል፥ ሰው​ነ​ትህ ከወ​ደ​ደ​ችው ሁሉ ብላ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 አምላክህ እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት ግዛትህን ሲያሰፋልህ፣ ሥጋ አምሮህ፣ “ሥጋ መብላት እፈልጋለሁ” በምትልበት ጊዜ፣ ያሠኘህን ያህል ሥጋ መብላት ትችላለህ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 “አምላክህ ጌታ በሰጠህ ተስፋ መሠረት ግዛትህን ሲያሰፋልህ፥ ሥጋ አምሮህ፥ ‘ሥጋ መብላት እፈልጋለሁ’ በምትልበት ጊዜ፥ ያሰኘህን ያህል ሥጋ መብላት ትችላለህ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 “በሰጠህ ተስፋ መሠረት እግዚአብሔር ግዛትህን በሚያሰፋበት ጊዜ፥ በሚያሰኝህ ጊዜ ሁሉ ሥጋ መመገብ ትችላለህ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ነገረህ አገርህን ባሰፋ ጊዜ፥ ሰውነትህም ሥጋ መብላት ስለ ወደደች፦ ሥጋ ልብላ ስትል፥ እንደ ሰውነትህ ፈቃድ ሥጋን ብላ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘዳግም 12:20
24 Referências Cruzadas  

ዘር​ህም እንደ ባሕር አሸዋ ይሆ​ናል፤ እስከ ባሕ​ርና እስከ አዜብ እስከ መስ​ዕና እስከ ምሥ​ራቅ ይበ​ዛል፤ ይሞ​ላ​ልም፤ የም​ድ​ርም ሕዝ​ቦች ሁሉ በአ​ንተ፥ በዘ​ር​ህም ይባ​ረ​ካሉ።


አሁ​ንም የአ​ባ​ት​ህን ቤት ከና​ፈ​ቅህ ሂድ፤ ነገር ግን አም​ላ​ኮ​ቼን ለምን ሰረ​ቅህ?”


ንጉ​ሡም ዳዊት አቤ​ሴ​ሎ​ምን መከ​ታ​ተ​ልን ተወ፤ ስለ ሞተው ልጁ ስለ አም​ኖን ተጽ​ና​ንቶ ነበ​ርና።


ዳዊ​ትም፥ “በበሩ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ማን ባጠ​ጣኝ?” ብሎ ተመኘ። ያን​ጊ​ዜም የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ኀይል በቤተ ልሔም ነበረ።


ያግ​ቤ​ጽም፥ “እባ​ክህ፥ መባ​ረ​ክን ባር​ከኝ፥ ሀገ​ሬ​ንም አስ​ፋው፤ እጅ​ህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እን​ዳ​ያ​ሳ​ዝ​ነ​ኝም ምል​ክት አድ​ር​ግ​ልኝ” ብሎ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ጠራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የለ​መ​ነ​ውን ሰጠው።


ካህን ሞዓ​ብም ተስ​ፋዬ ነው፥ በኤ​ዶ​ም​ያስ ላይም ጫማ​ዬን እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ምም ይገ​ዙ​ል​ኛል።


አቤቱ፥ ወደ አንተ የለ​መ​ን​ሁ​ትን ጸሎ​ቴን ስማኝ፥ ከጠ​ላ​ትም ጥር​ጥር ነፍ​ሴን አድ​ናት።


የሕ​ዝ​ብ​ህን ኀጢ​አት ይቅር አልህ፤ ዐበ​ሳ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ሰወ​ርህ።


ድን​በ​ር​ህ​ንም ከኤ​ር​ትራ ባሕር እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ባሕር፥ ከም​ድረ በዳም እስከ ታላቁ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ አሰ​ፋ​ለሁ፤ በም​ድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን በእ​ጅህ እጥ​ላ​ለ​ሁና፤ ከአ​ን​ተም አስ​ወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


አሕ​ዛ​ብን ከፊ​ትህ በአ​ወ​ጣሁ ጊዜ ሀገ​ር​ህን አሰ​ፋ​ለሁ፤ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊትም ለመ​ታ​የት በዓ​መት ሦስት ጊዜ ስት​ወጣ ማንም ምድ​ር​ህን አይ​መ​ኝም።


ነገር ግን በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ያለ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ንቃ​ች​ኋ​ልና፥ በፊ​ቱም፦ ለምን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ኸን? ብላ​ችሁ አል​ቅ​ሳ​ች​ኋ​ልና በአ​ፍ​ን​ጫ​ችሁ እስ​ኪ​ወጣ መር​ዝም እስ​ኪ​ሆ​ን​ባ​ችሁ ድረስ ወር ሙሉ ትበ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ።”


የጐ​መጁ ሕዝብ በዚያ ተቀ​ብ​ረ​ዋ​ልና የዚያ ስፍራ ስም “መቃ​ብረ ፍት​ወት” ተብሎ ተጠራ።


ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የተ​ቀ​ላ​ቀሉ ሕዝብ እጅግ ጐመጁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተቀ​ም​ጠው እን​ዲህ እያሉ አለ​ቀሱ፥ “ሥጋ ማን ያበ​ላ​ናል?


እነ​ር​ሱም ስለ እና​ንተ ይጸ​ል​ያሉ፤ ስለ አደ​ረ​ባ​ችሁ ታላቅ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋም ሊያ​ዩ​አ​ችሁ ይመ​ኛሉ።


የእ​ግ​ራ​ችሁ ጫማ የም​ት​ረ​ግ​ጣት ስፍራ ሁሉ ለእ​ና​ንተ ትሆ​ና​ለች፤ ከም​ድረ በዳም፥ ከአ​ን​ጢ​ሊ​ባ​ኖ​ስም፥ ከታ​ላ​ቁም ከኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ባሕር ድረስ ዳር​ቻ​ችሁ ይሆ​ናል።


“ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰጠህ በረ​ከት፥ እንደ ፈቀ​ድህ፥ በሀ​ገ​ርህ ሁሉ ውስጥ አር​ደህ ሥጋን ብላ፤ ከአ​ንተ ንጹሕ ሰው፥ ንጹ​ሕም ያል​ሆነ ሰው እንደ ሚዳ​ቋና እንደ ዋላ ያለ​ውን ይብ​ላው።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ ስሙ ይጠራ ዘንድ የመ​ረ​ጠው ስፍራ ከአ​ንተ ሩቅ ቢሆ​ንም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ጠህ ከላ​ምና ከበግ መን​ጋህ እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁህ እረድ፤ ሰው​ነ​ት​ህም የወ​ደ​ደ​ች​ውን በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ብላው።


አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ችህ እንደ ማለ​ላ​ቸው ዳር​ቻ​ህን ቢያ​ሰፋ፥ ለአ​ባ​ቶ​ችህ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ ብሎ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ምድር ሁሉ ቢሰ​ጥህ፥


በክ​ር​ስ​ቶስ ፍቅር ሁላ​ች​ሁን እን​ደ​ም​ወ​ዳ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክሬ ነው።


እንደ ታመመ፥ ለሞ​ትም እንደ ደረሰ መስ​ማ​ታ​ች​ሁን ዐውቆ ሊያ​ያ​ችሁ ይሻ​ልና።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios