Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘዳግም 10:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ስለ​ዚህ ለሌ​ዋ​ው​ያን ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር ክፍ​ልና ርስት የላ​ቸ​ውም፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ራ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስ​ታ​ቸው ነውና።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ሌዋዊ በወንድሞቹ መካከል ድርሻም ሆነ ርስት የሌለው ከዚህ የተነሣ ነው፤ አምላክህ እግዚአብሔር በነገረው መሠረት ርስቱ እግዚአብሔር ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ስለዚህ ለሌዊ ከወንድሞቹ ጋር ክፍልና ርስት የለውም፥ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው ጌታ ርስቱ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የሌዊ ነገድ ከሌሎቹ ወንድሞቹ ጋር ርስት እንዲኖረው ያልተደረገበትም ምክንያት ይኸው ነው፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ አስቀድሞ እንደ ተናገረ ካህናት ሆነው የማገልገልን መብት በማግኘታቸው ራሱ እግዚአብሔር ለሌዋውያን ርስታቸው ነው።)

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ስለዚህ ለሌዊ ከወንድሞቹ ጋር ክፍልና ርስት የለውም፤ አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው እግዚአብሔር ርስቱ ነው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘዳግም 10:9
9 Referências Cruzadas  

“ርስት አይ​ሆ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ እኔ ርስ​ታ​ቸው ነኝ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ዘንድ ርስት አት​ስ​ጡ​አ​ቸው፤ እኔ ርስ​ታ​ቸው ነኝ፤


ከአ​ንድ ወርም ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉ ወን​ዶች ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ቈ​ጠሩ ሃያ ሦስት ሺህ ነበሩ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች መካ​ከል ርስት አል​ተ​ሰ​ጣ​ቸ​ው​ምና ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጋር አል​ተ​ቈ​ጠ​ሩም።


በዚህ ነገር ዕድ​ልና ርስት የለ​ህም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ልብህ የቀና አይ​ደ​ለ​ምና።


እና​ን​ተም፥ ወን​ዶች ልጆ​ቻ​ች​ሁና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ቻ​ች​ሁም፥ ከእ​ና​ንተ ጋር ክፍ​ልና ርስት ስለ​ሌ​ለው በደ​ጆ​ቻ​ችሁ ውስጥ የተ​ቀ​መ​ጠው ሌዋ​ዊም በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


ድር​ሻና ርስት ከአ​ንተ ጋር ስለ​ሌ​ለው በከ​ተ​ማህ ውስጥ ያለ​ውን ሌዋዊ ቸል አት​በል።


ሌዋ​ዊ​ዉም፥ ከአ​ንተ ጋር ክፍ​ልና ርስት የለ​ው​ምና፥ በከ​ተ​ማህ ውስጥ ያለ መጻ​ተኛ፥ ድሃ-አደ​ግም፥ መበ​ለ​ትም መጥ​ተው ይበ​ላሉ፤ ይጠ​ግ​ባ​ሉም፤ ይኸ​ውም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ታ​ደ​ር​ገው በእ​ጅህ ሥራ ሁሉ ይባ​ር​ክህ ዘንድ ነው።


ለሁ​ለቱ ነገ​ድና ለእ​ኩ​ሌ​ታው ነገድ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ሙሴ ርስት ሰጥቶ ነበር፤ ነገር ግን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ለሌ​ዋ​ው​ያን ርስት አል​ሰ​ጣ​ቸ​ውም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios