Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘዳግም 10:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በተ​ራ​ራው ላይ በእ​ሳት መካ​ከል የተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁን ዐሠ​ር​ቱን ቃላት ቀድሞ ተጽ​ፈው እንደ ነበረ በጽ​ላቱ ላይ ጻፈ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እነ​ር​ሱን ለእኔ ሰጠኝ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እግዚአብሔር በስብሰባው ቀን፣ በእሳት ውስጥ ሆኖ ለእናንተ የተናገራቸውንና ቀድሞ ጽፏቸው የነበሩትን ዐሥሩን ትእዛዞች በእነዚህ ጽላት ላይ ጻፋቸው። እግዚአብሔርም እነርሱን ለእኔ ሰጠኝ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ዐሥርቱን ቃላት ጌታ በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገራችሁ ተሰብስባችሁበት በነበረበት ቀን፥ ቀድሞ ተጽፈው እንደነበረው በጽላቶቹ ላይ ጻፈ፥ እነርሱንም ጌታ ለእኔ ሰጠኝ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እግዚአብሔርም በተራራው ግርጌ ተሰብስባችሁ በነበረበት ቀን በእሳት ውስጥ ሆኖ የገለጠላችሁን ዐሥሩን ትእዛዞች እንደ ቀድሞው ጽሑፍ አድርጎ በአሁኖቹ ጽላቶች ላይ ጻፈ፤ ጽላቶቹንም ለእኔ ሰጠኝ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ስብሰባ ተደርጎ በነበረበትም ቀን እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ የተናገራችሁን አሠርቱን ቃላት ቀድሞ ተጽፈው እንደ ነበረ በጽላቶቹ ላይ ጻፈ፤ እግዚአብሔርም እነርሱን ለእኔ ሰጠኝ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘዳግም 10:4
10 Referências Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር በሲና ተራራ የተ​ና​ገ​ረ​ውን በፈ​ጸመ ጊዜ ሁለ​ቱን የም​ስ​ክር ጽላት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት የተ​ጻ​ፈ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ጽላት ለሙሴ ሰጠው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ሁለት የድ​ን​ጋይ ጽላት እንደ ፊተ​ኞቹ አድ​ር​ገህ ቅረጽ፤ ወደ እኔም ወደ ተራራ ውጣ፤ በሰ​በ​ር​ሃ​ቸው በፊ​ተ​ኞቹ ጽላት የነ​በ​ሩ​ትን ቃላት እጽ​ፍ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።


በዚ​ያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ነበረ፤ እን​ጀ​ራም አል​በ​ላም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣም። በጽ​ላ​ቱም ዐሥ​ሩን የቃል ኪዳን ቃሎች ጻፈ።


አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በኮ​ሬብ በተ​ሰ​በ​ሰ​ባ​ች​ሁ​በት ቀን፦ ‘እን​ዳ​ን​ሞት የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድምፅ ደግሞ አን​ስማ፤ ይህ​ችን ታላቅ እሳት ደግሞ አንይ’ ብላ​ችሁ እንደ ለመ​ና​ች​ሁት ሁሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት የተ​ጻ​ፉ​ትን ሁለት የድ​ን​ጋይ ጽላት ሰጠኝ፤ በተ​ሰ​በ​ሰ​ባ​ችሁ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​ራ​ራው ላይ የነ​ገ​ረኝ ቃል ሁሉ ተጽ​ፎ​ባ​ቸው ነበር።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios