Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ቈላስይስ 4:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እኔ ጳው​ሎስ በእጄ ጽፌ ሰላም አል​ኋ​ችሁ፤ እስ​ራ​ቴን አስቡ፤ ጸጋ ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን፤ አሜን። በሮሜ ተጽፋ በቲ​ኪ​ቆስ እጅ ወደ ቈላ​ስ​ይስ ሰዎች የተ​ላ​ከ​ችው መል​እ​ክት ተፈ​ጸ​መች። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን። አሜን።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ይህን ሰላምታ በገዛ እጄ የጻፍሁት እኔ ጳውሎስ ነኝ። እስራቴን አስቡ። ጸጋ ከእናንተ ጋራ ይሁን።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ይህን ሰላምታ እኔ ጳውሎስ በገዛ እጄ ጽፌዋለሁ። እስራቴን አስቡ። ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ይህን ሰላምታ በገዛ እጄ የጻፍኩት እኔ ጳውሎስ ነኝ፤ በሰንሰለት ታስሬ እንዳለሁ አስታውሱ። የእግዚአብሔር ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በገዛ እጄ የተጻፈ የእኔ የጳውሎስ ሰላምታ ይህ ነው። እስራቴን አስቡ። ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።

Ver Capítulo Cópia de




ቈላስይስ 4:18
14 Referências Cruzadas  

የሰ​ላም አም​ላ​ክም ፈጥኖ ሰይ​ጣ​ንን ከእ​ግ​ራ​ችሁ በታች ይቀ​ጥ​ቅ​ጠው፤ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጸጋ ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን፤ አሜን።


ይህ​ችን መል​እ​ክት የጻ​ፍ​ኋት እኔ ጤር​ጥ​ዮስ በጌ​ታ​ችን ስም ሰላም እላ​ች​ኋ​ለሁ።


እኔ​ንና አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ና​ትን ሁሉ በእ​ን​ግ​ድ​ነት የተ​ቀ​በለ ጋይ​ዮ​ስም ሰላም ብሎ​አ​ች​ኋል፤ የከ​ተ​ማው መጋቢ አር​ስ​ጦ​ስና ወን​ድ​ማ​ችን ቁአ​ስ​ጥ​ሮ​ስም ሰላም ብለ​ዋ​ች​ኋል።


እኔ ጳው​ሎስ ይህን ሰላ​ምታ በእጄ ጻፍሁ።


ስለ እና​ንተ ይህን ላስብ ይገ​ባ​ኛል፤ በም​ታ​ሰ​ር​በ​ትና በም​ከ​ራ​ከ​ር​በት፥ ወን​ጌ​ል​ንም በማ​ስ​ተ​ም​ር​በት ጊዜ ከእኔ ጋራ በጸጋ ስለ ተባ​በ​ራ​ችሁ በልቤ ውስጥ ናች​ሁና።


ስለ እርሱ የታ​ሰ​ር​ሁ​ለ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሥ​ጢር እን​ድ​ን​ና​ገር፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃ​ሉን በር ይከ​ፍ​ት​ልን ዘንድ ለእ​ኛም ደግሞ ጸል​ዩ​ልን፤ ለም​ኑ​ል​ንም፤


በገዛ እጄ የተጻፈ የእኔ የጳውሎስ ሰላምታ ይህ ነው፤ የመልእክቴ ሁሉ ማስረጃ ይህ ነው፤ እንዲህ እጽፋለሁ።


ይህ እውቀት አለን ብለው አንዳንዶች ስለ እምነት ስተዋልና። ጸጋ ከአንተ ጋር ይሁን።


እንግዲህ በጌታችን ምስክርነት ወይም በእስረኛው በእኔ አትፈር፤ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ኀይል መጠን ስለ ወንጌል አብረኸኝ መከራን ተቀበል፤


ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመንፈስህ ጋር ይሁን። ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን፤ አሜን።


ከእኔ ጋር ያሉት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል። በእምነት ለሚወዱን ሰላምታ አቅርብልን። ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን።


የጌ​ታ​ችን ጸጋዉ ከሁ​ላ​ችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን። ወደ ዕብ​ራ​ው​ያን የተ​ላ​ከው መል​እ​ክት ተፈ​ጸመ፤ በኢ​ጣ​ልያ ተጻፈ፤ በጢ​ሞ​ቴ​ዎስ እጅ ተላከ። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን። አሜን።


ከእ​ነ​ርሱ ጋር አብ​ራ​ች​ኋ​ቸው እንደ ታሰ​ራ​ችሁ ሆና​ችሁ እስ​ረ​ኞ​ችን ዐስቡ፤ መከራ የጸ​ና​ባ​ቸ​ው​ንም በሥ​ጋ​ችሁ ከእ​ነሱ ጋር እን​ዳ​ላ​ችሁ ሆና​ችሁ ዐስቡ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios