Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




አሞጽ 6:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ፍር​ድን ወደ ቍጣ፥ የእ​ው​ነ​ት​ንም ፍሬ ወደ እሬት ለው​ጣ​ች​ኋ​ልና፥ በውኑ ፈረ​ሶች በጭ​ንጫ ላይ ይሮ​ጣ​ሉን? ወይስ በሬ​ዎች በዚያ ላይ ያር​ሳ​ሉን?

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ፈረሶች በጭንጫ ላይ ይሮጣሉን? ሰውስ እዚያ ላይ በበሬ ያርሳልን? እናንተ ግን ፍትሕን ወደ መርዝነት፣ የጽድቅንም ፍሬ ወደ መራራነት ለወጣችሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በውኑ ፈረሶች በዓለታም መሬት ላይ ይጋልባሉን? ወይስ ሰው በበሬዎች በዚያ ላይ ሊያርስ ይችላልን? ነገር ግን እናንተ ፍርድን ወደ ሐሞት፥ የጽድቅንም ፍሬ ወደ እሬት ለወጣችሁ፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ፈረሰኛ በቋጥኝ ላይ ሊጋልብ ይችላልን? ገበሬስ በባሕር ላይ በሬ ጠምዶ ማረስ ይችላልን? እናንተ ግን ፍርድን ወደ መርዝ ለወጣችሁ፤ እውነትንም እንደ ሬት መራራ አደረጋችሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12-13 ፍርድን ወደ ሐሞት፥ የጽድቅንም ፍሬ ወደ እሬት የለወጣችሁ፥ በከንቱም ነገር ደስ የሚላችሁ፦ በኃይላችን ቀንድ የወሰድን አይደለምን? የምትሉ፥ እናንተ ሆይ፥ በውኑ ፈረሶች በጭንጫ ላይ ይጋልባሉን? ወይስ በሬዎች በዚያ ላይ ያርሳሉን?

Ver Capítulo Cópia de




አሞጽ 6:12
17 Referências Cruzadas  

አንተ እል​ከኛ፥ አን​ገ​ት​ህም የብ​ረት ጅማት፥ ግን​ባ​ር​ህም ናስ እንደ ሆነ ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤


አቤቱ! ዐይ​ኖ​ችህ ለሃ​ይ​ማ​ኖት አይ​ደ​ሉ​ምን? አንተ ቀሥ​ፈ​ሃ​ቸ​ዋል፤ ነገር ግን አላ​ዘ​ኑም፤ ቀጥ​ቅ​ጠ​ሃ​ቸ​ው​ማል፤ ነገር ግን ተግ​ሣ​ጽን እንቢ አሉ፤ ፊታ​ቸ​ውን ከድ​ን​ጋይ ይልቅ አጠ​ን​ክ​ረ​ዋል፤ ይመ​ለ​ሱም ዘንድ እንቢ አሉ።


ዐመ​ፅን ለምን ተከ​ላ​ችሁ? ኀጢ​አ​ት​ንስ ለምን አጨ​ዳ​ችሁ፤ የሐ​ሰ​ት​ንም ፍሬ በል​ታ​ች​ኋል፤ በሠ​ረ​ገ​ሎ​ች​ህና በሠ​ራ​ዊ​ትህ ብዛት ታም​ነ​ሃል።


የማ​ይ​ረ​ባ​ውን የሐ​ሰት ቃል ይና​ገ​ራሉ፤ ቃል ኪዳ​ንም ያደ​ር​ጋሉ፤ ስለ​ዚህ መር​ዛም ሣር በእ​ርሻ ትልም ላይ እን​ደ​ሚ​በ​ቅል ፍርድ ይበ​ቅ​ል​ባ​ቸ​ዋል።


ፈራ​ጅ​ንም ከመ​ካ​ከ​ልዋ አጠ​ፋ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አለ​ቆ​ች​ዋን ሁሉ እገ​ድ​ላ​ለሁ” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“በፊቷ የሚ​መ​ጣ​ባ​ትን አላ​ወ​ቀ​ችም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በሀ​ገ​ራ​ቸው ቅሚ​ያ​ንና ግፍን የሚ​ያ​ከ​ማቹ ናቸው።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍር​ድን በሰ​ማይ ያደ​ር​ጋል፤ ጽድ​ቅ​ንም በም​ድር ላይ ይመ​ሠ​ር​ታል።


እጆቻቸውን ለክፋት ያነሣሉ፥ አለቃውና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፥ እንዲሁም ክፋትን ይጐነጕናሉ።


የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉት ሰዎች በሰላም ይዘራል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios