Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሐዋርያት ሥራ 8:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ያነ​በው የነ​በረ የመ​ጽ​ሐፉ ቃልም እን​ዲህ የሚል ነበር፤ “እንደ በግ ወደ መታ​ረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦ​ትም በሚ​ሸ​ል​ተው ፊት እን​ደ​ማ​ይ​ና​ገር እን​ዲሁ አፉን አል​ከ​ፈ​ተም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ጃንደረባው ያነብብ የነበረው የመጽሐፍ ክፍል ይህ ነበር፤ “እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፤ በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ፣ አፉን አልከፈተም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ያነበውም የነበረ የመጽሐፉ ክፍል ይህ ነበረ፤ “እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦትም በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 እርሱም ያነበው የነበረው የቅዱስ መጽሐፍ ክፍል የሚከተለው ነበረ፦ “እርሱ ለመታረድ እንደሚነዳ በግ ነበረ፤ ሲሸልቱትም ዝም እንደሚል ጠቦት፤ እርሱም ለመናገር አፉን አልከፈተም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ያነበውም የነበረ የመጽሐፉ ክፍል ይህ ነበረ፤ እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፥ የበግ ጠቦትም በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።

Ver Capítulo Cópia de




ሐዋርያት ሥራ 8:32
18 Referências Cruzadas  

ከጥ​ፋት ጕድ​ጓድ ከረ​ግ​ረግ ጭቃም አወ​ጣኝ፥ እግ​ሮ​ቼ​ንም በዓ​ለት ላይ አቆ​ማ​ቸው፥ አረ​ማ​መ​ዴ​ንም አጸና።


በታ​ላቅ ጉባኤ ጽድ​ቅ​ህን አወ​ራሁ፤ እነሆ፥ ከን​ፈ​ሮ​ችን አል​ከ​ለ​ክ​ልም፤ አቤቱ፥ አንተ ጽድ​ቄን ታው​ቃ​ለህ።


እኔም ለመ​ታ​ረድ እን​ደ​ሚ​ነዳ እንደ የዋህ ጠቦት በግ ሆንሁ፤ እነ​ር​ሱም በእ​ን​ጀ​ራው ዕን​ጨት እን​ጨ​ምር ስሙም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ እን​ዳ​ይ​ታ​ሰብ ከሕ​ያ​ዋን ምድር እና​ጥ​ፋው ብለው ክፉ ምክ​ርን እን​ዳ​ሰ​ቡ​ብኝ አላ​ወ​ቅ​ሁም ነበር።


አንተ ግን አቤቱ! ዐው​ቀ​ኸ​ኛል፤ አይ​ተ​ኸ​ኛል፤ ልቤ​ንም በፊ​ትህ ፈት​ነ​ሃል፤ እንደ በጎች ለመ​ታ​ረድ ጐት​ተህ ለያ​ቸው፤ ለመ​ታ​ረ​ድም ቀን አዘ​ጋ​ጃ​ቸው።


እንደ ጠቦ​ቶ​ችና እንደ አውራ በጎች፥ እንደ አውራ ፍየ​ሎ​ችም ወደ መታ​ረድ አወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤


ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አባት ሆይ፥ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ኣያ​ው​ቁ​ምና ይቅር በላ​ቸው” አለ፤ በል​ብ​ሱም ላይ ዕጣ ተጣ​ጣ​ሉና ተካ​ፈሉ።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ዮሐ​ንስ ወደ እርሱ ሲመጣ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን አይቶ እን​ዲህ አለ፤ “እነሆ፥ የዓ​ለ​ሙን ኀጢ​ኣት የሚ​ያ​ስ​ወ​ግድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ።


ጃን​ደ​ረ​ባ​ውም፥ “ያስ​ተ​ማ​ረኝ ሳይ​ኖር በምን አው​ቀ​ዋ​ለሁ?” አለው፤ ወደ ሰረ​ገ​ላ​ውም ወጥቶ አብ​ሮት ይቀ​መጥ ዘንድ ፊል​ጶ​ስን ለመ​ነው።


መጽ​ሐፍ እን​ዳለ፥ “ስለ አንተ ዘወ​ትር ይገ​ድ​ሉ​ናል፤ እን​ደ​ሚ​ታ​ረዱ በጎ​ችም ሆነ​ናል።”


እኔ የተ​ማ​ር​ሁ​ትን አስ​ቀ​ድሜ መጽ​ሐፍ እን​ደ​ሚል እን​ዲህ ብዬ አስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ችሁ፥ “ክር​ስ​ቶስ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ሞተ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios