Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሐዋርያት ሥራ 8:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 አሁ​ንም ከክ​ፋ​ትህ ተመ​ለ​ስና ንስሓ ግባ። የል​ቡ​ና​ህ​ንም ዐሳብ ይተ​ው​ልህ እንደ ሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለምን።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 አሁንም ስለዚህ ክፋትህ ንስሓ ግባ፤ ወደ ጌታም ጸልይ፤ ምናልባት ይህን የልብህን ሐሳብ ይቅር ይልህ ይሆናል፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እንግዲህ ስለዚህ ክፋትህ ንሰሐ ግባ፤ ምናልባትም የልብህን አሳብ ይቅር ይልህ እንደሆነ ወደ እግዚአብሔር ለምን፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እንግዲህ ከዚህ ከክፋትህ ተጸጽተህ ንስሓ ግባ፤ ምናልባት የልብህን ክፉ አሳብ ይቅር ይልልህ እንደ ሆነ እግዚአብሔርን ለምን።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እንግዲህ ስለዚህ ክፋትህ ንሰሐ ግባ፥ ምናልባትም የልብህን አሳብ ይቅር ይልህ እንደ ሆነ ወደ እግዚአብሔር ለምን፤

Ver Capítulo Cópia de




ሐዋርያት ሥራ 8:22
23 Referências Cruzadas  

ሰነፍ በኀጢአት ይሞታል፤ ነፍሰ ገዳይ ሰውን ርኵሰቱ፥


ክፉ​ውን ጥሉ፤ መል​ካ​ሙ​ንም ውደዱ፤ በበ​ሩም አደ​ባ​ባይ ፍር​ድን አጽኑ፤ ምና​ል​ባት ሁሉን የሚ​ችል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዮ​ሴፍ ቅሬታ ይራራ ይሆ​ናል።


በዮ​ሴፍ ቤት እሳት እን​ዳ​ት​ቃ​ጠል፥ እን​ዳ​ት​በ​ላ​ቸ​ውም የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቤት እሳት የሚ​ያ​ጠ​ፋ​ላ​ቸው እን​ዳ​ያጡ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈልጉ፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።


የመ​ር​ከ​ቡም አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “ምነው ተኝ​ተ​ሃል? እን​ዳ​ን​ጠፋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያድ​ነን ዘንድ ተነ​ሥ​ተህ አም​ላ​ክ​ህን ጥራ” አለው።


እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ይምራን፥ ከጽኑ ቁጣውም ይመለስ እንደሆነ ማን ያውቃል?”


የቀ​ድ​ሞ​ው​ንስ ያለ ማወቅ ዘመን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሳ​ል​ፎ​ታል፤ ዛሬ ግን በመ​ላው ዓለም ንስሓ እን​ዲ​ገቡ ሰውን ሁሉ አዝ​ዞ​አል።


ጴጥ​ሮ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ንስሓ ግቡ፤ ሁላ​ች​ሁም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ተጠ​መቁ፤ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም ይሰ​ረ​ይ​ላ​ች​ኋል፤ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስ​ንም ጸጋ ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ።


እን​ግ​ዲህ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ ይሰ​ረ​ይ​ላ​ችሁ ዘንድ ንስሓ ግቡ፥ ተመ​ለ​ሱም።


ጴጥ​ሮስ ግን እን​ዲህ አለው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጸጋ በገ​ን​ዘብ ልት​ገዛ ዐስ​በ​ሃ​ልና ገን​ዘ​ብህ ከአ​ንተ ጋር ይጥፋ።


ጌታም፥ “ተነ​ሣና ቅን በም​ት​ባ​ለው መን​ገድ ሂድ፤ በይ​ሁዳ ቤትም ከጠ​ር​ሴስ ሀገር የመጣ ሳውል የሚ​ባል ሰው ፈልግ፤ እርሱ አሁን ይጸ​ል​ያ​ልና” አለው።


ወይስ በቸ​ር​ነቱ ብዛት በመ​ታ​ገሡ፥ ለአ​ን​ተም እሺ በማ​ለቱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ዋቂ ልታ​ደ​ር​ገው ታስ​ባ​ለ​ህን? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ቸር​ነቱ አን​ተን ወደ ንስሓ እን​ዲ​መ​ል​ስህ አታ​ው​ቅ​ምን?


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሕያው ነውና፤ የሚ​ሠ​ራም ሁለት ልሳን ካለው ሰይ​ፍም ሁሉ ይልቅ የተ​ሳለ ነው፤ ነፍ​ስ​ንና መን​ፈ​ስ​ንም፥ ጅማ​ት​ንና ቅል​ጥ​ም​ንም እስ​ኪ​ለይ ድረስ ይወ​ጋል፤ የል​ብ​ንም ስሜ​ትና አሳብ ይመ​ረ​ም​ራል።


ንስሓም እንድትገባ ጊዜ ሰጠኋት ከዝሙትዋም ንስሓ እንድትገባ አልወደደችም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios