Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሐዋርያት ሥራ 4:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እን​ግ​ዲህ እና​ንተ ሁላ​ችሁ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ወገን ሁሉ፥ እና​ንተ በሰ​ቀ​ላ​ች​ሁት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሙ​ታን ለይቶ በአ​ስ​ነ​ሣው በና​ዝ​ሬቱ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ይህ ሰው እንደ ዳነና በፊ​ታ​ች​ሁም እንደ ቆመ በር​ግጥ ዕወቁ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እናንተ በሰቀላችሁት፣ እግዚአብሔር ግን ከሙታን ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መዳኑንና ፊታችሁ መቆሙን እናንተም ሆናችሁ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ይህን ይወቅ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እናንተ በሰቀላችሁት እግዚአብሔርም ከሙታን ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህ ደኅና ሆኖ በፊታችሁ እንደ ቆመ፥ ለእናንተ ለሁላችሁ ለእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ይህ ሰው ድኖ በፊታችሁ የቆመው እናንተ በሰቀላችሁትና እግዚአብሔር ግን ከሞት ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንደ ሆነ ለእናንተ ለሁላችሁና ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እናንተ በሰቀላችሁት እግዚአብሔርም ከሙታን ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህ ደኅና ሆኖ በፊታችሁ እንደ ቆመ፥ ለእናንተ ለሁላችሁ ለእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን።

Ver Capítulo Cópia de




ሐዋርያት ሥራ 4:10
16 Referências Cruzadas  

በነቢያት “ናዝራዊ ይባላል” የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።


እነ​ር​ሱም፥ “የና​ዝ​ሬቱ ኢየ​ሱስ ያል​ፋል” ብለው ነገ​ሩት።


እር​ሱን ኢየ​ሱ​ስን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ነ​ሣው፤ ለዚ​ህም እኛ ሁላ​ችን ምስ​ክ​ሮቹ ነን።


እን​ግ​ዲህ የእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሁሉ እና​ንተ የሰ​ቀ​ላ​ች​ሁ​ትን ኢየ​ሱ​ስን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጌታም መሢ​ሕም እን​ዳ​ደ​ረ​ገው በር​ግጥ ይወቁ።”


እን​ግ​ዲህ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ገ​ኘች ይህቺ ድኅ​ነት ለአ​ሕ​ዛብ እን​ደ​ም​ት​ሆን ዕወቁ፤ እነ​ር​ሱም ይሰ​ሙ​ታል።”


ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ወር​ቅና ብር የለ​ኝም፤ ያለ​ኝን ግን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ እነሆ፥ በና​ዝ​ሬቱ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ተነ​ሥ​ተህ ሂድ” አለው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ በኀ​ይ​ሉና በመ​ን​ፈስ ቅዱስ፥ ከሙ​ታ​ንም ተለ​ይቶ በመ​ነ​ሣቱ ስለ አሳየ ስለ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ፥


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios