Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሐዋርያት ሥራ 28:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ነገር ግን በዚህ ነገር በየ​ስ​ፍ​ራው ሁሉ እን​ዲ​ጣሉ በእኛ ዘንድ ታው​ቋ​ልና የአ​ን​ተን ዐሳብ ደግሞ ከአ​ንተ እን​ሰማ ዘንድ እን​ወ​ድ​ዳ​ለን።”

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ይሁን እንጂ፣ ሰዎች ስለዚህ የእምነት ክፍል በየቦታው ክፉ እንደሚያወሩበት እናውቃለን፤ የአንተ አስተሳሰብ ደግሞ ምን እንደ ሆነ መስማት እንፈልጋለን።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ነገር ግን ስለዚህ ወገን በየስፍራው ሁሉ እንዲቃወሙ በእኛ ዘንድ ታውቆአልና የምታስበውን ከአንተ እንሰማ ዘንድ እንፈቅዳለን፤” አሉት።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ይህን አንተ የምትከተለውን የሃይማኖት ክፍል በየቦታው ሰዎች እንደሚቃወሙት እናውቃለን፤ ስለዚህ የአንተ አሳብ ምን እንደ ሆነ መስማት እንፈልጋለን።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ነገር ግን ስለዚህ ወገን በየስፍራው ሁሉ እንዲቃወሙ በእኛ ዘንድ ታውቆአልና የምታስበውን ከአንተ እንሰማ ዘንድ እንፈቅዳለን” አሉት።

Ver Capítulo Cópia de




ሐዋርያት ሥራ 28:22
14 Referências Cruzadas  

ብዙ ነገ​ርን ታያ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን አት​ጠ​ባ​በ​ቁ​ትም፤ ጆሮ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ተከ​ፍ​ተ​ዋል፤ ነገር ግን አት​ሰ​ሙም።


ስም​ዖ​ንም ባረ​ካ​ቸው፤ እና​ቱን ማር​ያ​ም​ንም እን​ዲህ አላት፤ “እነሆ፥ ይህ ሕፃን ከእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ለብ​ዙ​ዎች ለመ​ው​ደ​ቃ​ቸ​ውና ለመ​ነ​ሣ​ታ​ቸው፥ ለሚ​ቃ​ወ​ሙ​ትም ምል​ክት ይሆን ዘንድ የተ​ሠ​የመ ነው፤


ነገር ግን ካመ​ኑት ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ወገን አን​ዳ​ን​ዶች ተነ​ሥ​ተው፥ “ትገ​ዝ​ሩ​አ​ቸው ዘን​ድና የሙ​ሴን ሕግ እን​ዲ​ጠ​ብቁ ታዝ​ዙ​አ​ቸው ዘንድ ይገ​ባል” አሉ።


ነገር ግን ይህን አረ​ጋ​ግ​ጥ​ል​ሃ​ለሁ፤ እኔ በሕግ ያለ​ውን፥ በነ​ቢ​ያ​ትም የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ አምኜ እነ​ርሱ ክህ​ደት ብለው በሚ​ጠ​ሩት ትም​ህ​ርት የአ​ባ​ቶ​ችን አም​ላክ አመ​ል​ከ​ዋ​ለሁ።


ሊመ​ሰ​ክ​ሩም ከወ​ደዱ እኔ ፈሪ​ሳዊ ሆኜ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ሕግ እን​ደ​ም​ኖር ከጥ​ንት ጀምሮ እነ​ርሱ ያው​ቁ​ል​ኛል።


ሊቀ ካህ​ና​ቱና አብ​ረ​ውት የነ​በ​ሩት የሰ​ዱ​ቃ​ው​ያን ወገ​ኖ​ችም ቀን​ተው በእ​ነ​ርሱ ላይ ተነሡ።


አስ​ቀ​ድሜ ስለ ሁላ​ችሁ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ፤ ማመ​ና​ችሁ በዓ​ለም ሁሉ ተሰ​ም​ታ​ለ​ችና።


ከእ​ና​ንተ የተ​መ​ረ​ጡት ወን​ድ​ሞች ተለ​ይ​ተው እን​ዲ​ታ​ወቁ ትለ​ያዩ ዘንድ ግድ ነው።


ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።


በክርስቶስ ያለውን መልካሙን ኑሮአችሁን የሚሳደቡ ሰዎች ክፉን እንደምታደርጉ በሚያሙበት ነገር እንዲያፍሩ በጎ ሕሊና ይኑራችሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios