Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሐዋርያት ሥራ 28:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እጅግ ታላቅ ክብ​ርም አከ​በ​ሩን፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ ለመ​ሄድ በተ​ነ​ሣን ጊዜ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ንን ስንቅ ሰጡን።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እኛንም በብዙ መንገድ አከበሩን፤ በመርከብም ለመሄድ በተዘጋጀን ጊዜ፣ የሚያስፈልገንን ሁሉ ጫኑልን።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በብዙ ክብርም ደግሞ አከበሩን፤ በተነሣንም ጊዜ በመርከብ ላይ የሚያስፈልገንን ነገር አኖሩልን።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ሰዎቹ ብዙ ስጦታ አመጡልን፤ አክብሮታቸውንም ገለጡልን፤ በመርከብ ለመሄድ በተነሣንም ጊዜ የሚያስፈልገንን ሁሉ በመርከብ ላይ ጫኑልን።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በብዙ ክብርም ደግሞ አከበሩን፥ በተነሣንም ጊዜ በመርከብ ላይ የሚያስፈልገንን ነገር አኖሩልን።

Ver Capítulo Cópia de




ሐዋርያት ሥራ 28:10
15 Referências Cruzadas  

አዛ​ሄ​ልም ሊገ​ና​ኘው ሄደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ከደ​ማ​ስቆ መል​ካ​ሙን ነገር ሁሉ የአ​ርባ ግመል ጭነት ገጸ በረ​ከት ወሰደ፤ መጥ​ቶም በፊቱ ቆመና፥ “ልጅህ የሶ​ርያ ንጉሥ ወልደ አዴር፦ ከዚህ በሽታ እድ​ና​ለ​ሁን? ሲል ወደ አንተ ልኮ​ኛል” አለው።


ያባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ያከ​ብር ዘንድ ይህን ነገር በን​ጉሡ ልብ ያኖረ፥


ደዌ​ያ​ቸው በዛ፤ ከዚ​ያም በኋላ ተፋ​ጠኑ፤ በደም ማኅ​በ​ራ​ቸው አል​ተ​ባ​በ​ርም። ስማ​ቸ​ው​ንም በአፌ አል​ጠ​ራም።


ከሦ​ስት ወር በኋ​ላም በዚ​ያች ደሴት ወደ ከረ​መ​ችው ወደ እስ​ክ​ን​ድ​ርያ መር​ከብ ወጣን፤ በዚ​ያች መር​ከብ ላይም የዲ​ዮ​ስ​ቆ​ሮስ ምል​ክት ነበ​ረ​ባት፤ ይኸ​ውም “የመ​ር​ከ​በ​ኞች አም​ላክ” የሚ​ሉት ነው።


ያደ​ረ​ገ​ው​ንም ይህን ተአ​ምር ባዩ ጊዜ በዚ​ያች ደሴት ያሉ​ትን ድው​ያን ሁሉ አመ​ጡ​ለት፤ ፈወ​ሳ​ቸ​ውም።


ፈጣ​ሪዬ እንደ ባለ​ጸ​ግ​ነቱ መጠን፥ በክ​ብር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የም​ት​ሹ​ትን ሁሉ ይፈ​ጽ​ም​ላ​ች​ኋል።


የክርስቶስም ሐዋርያት እንደ መሆናችን ልንከብድባችሁ ስንችል፥ ከእናንተ ቢሆን ወይም ከሌሎች ክብርን ከሰው አልፈለግንም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios