Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሐዋርያት ሥራ 26:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እኔም፦ ‘አቤቱ አንተ ማነህ?’ አልሁ፤ ጌታም አለኝ፦ ‘እኔ አንተ የም​ታ​ሳ​ድ​ደኝ ኢየ​ሱስ ነኝ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 “እኔም፣ ‘ጌታ ሆይ፤ አንተ ማን ነህ?’ ” አልሁ። “ጌታም እንዲህ አለኝ፤ ‘እኔ፣ አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እኔም ‘ጌታ ሆይ! ማን ነህ?’ አልሁ። እርሱም አለኝ ‘አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እኔም ‘ጌታ ሆይ! አንተ ማን ነህ?’ አልኩ፤ ጌታም እንዲህ አለኝ፦ ‘እኔ አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እኔም፦ “ጌታ ሆይ፥ ማንነህ?” አልሁ። እርሱም አለኝ፦ “አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ።

Ver Capítulo Cópia de




ሐዋርያት ሥራ 26:15
6 Referências Cruzadas  

ሙሴም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁ​በ​ትን ማን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁን ሰም​ቶ​አ​ልና በመሸ ጊዜ ትበሉ ዘንድ ሥጋን፥ በማ​ለ​ዳም ትጠ​ግቡ ዘንድ እን​ጀ​ራን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ እኛም ምን​ድን ነን? ማን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ነው እንጂ በእኛ ላይ አይ​ደ​ለም” አለ።


ንጉሡም መልሶ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት፤’ ይላቸዋል።


ያን ጊዜ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም፤’ ብሎ ይመልስላቸዋል።


ሁላ​ች​ንም በም​ድር ላይ በወ​ደ​ቅን ጊዜ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቋንቋ፦ ‘ሳውል ሳውል ለምን ታሳ​ድ​ደ​ኛ​ለህ? በሾለ ብረት ላይ መር​ገጥ ለአ​ንተ ይብ​ስ​ሃል’ የሚ​ለ​ኝን ቃል ሰማሁ።


ነገር ግን ተነ​ሣና በእ​ግ​ርህ ቁም፤ እኔን ባየ​ህ​በ​ትና ወደ​ፊ​ትም በም​ታ​ይ​በት ነገር አገ​ል​ጋ​ይና ምስ​ክር አድ​ርጌ ልሾ​ምህ ስለ​ዚህ ተገ​ል​ጬ​ል​ሃ​ለ​ሁና።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios