Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሐዋርያት ሥራ 25:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 በማ​ግ​ሥ​ቱም አግ​ሪ​ጳና በር​ኒቄ በብዙ ግርማ መጡ፤ ከመ​ሳ​ፍ​ን​ቱና ከከ​ተ​ማው ታላ​ላቅ ሰዎች ጋርም ወደ ፍርድ ቤት ገቡ፤ ፊስ​ጦ​ስም ጳው​ሎ​ስን እን​ዲ​ያ​መ​ጡት አዘዘ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 በማግስቱም አግሪጳና በርኒቄ በታላቅ ክብር መጥተው፣ ከከፍተኛ መኰንኖችና ከከተማዪቱ ታላላቅ ሰዎች ጋራ ወደ መሰብሰቢያው አዳራሽ ገቡ፤ በፊስጦስም ትእዛዝ ጳውሎስ እንዲቀርብ ተደረገ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 በነገውም አግሪጳና በርኒቄ በብዙ ግርማ መጥተው ከሻለቆችና ከከተማው ታላላቆች ጋር ወደ ፍርድ ቤት ገቡ፤ ፊስጦስም ባዘዘ ጊዜ ጳውሎስን አመጡት።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ስለዚህ በማግስቱ አግሪጳና በርኒቄ ልብሰ መንግሥታቸውን ለብሰውና በታላቅ ግርማ ሆነው በጦር አለቆችና በከተማው ታላላቅ ሰዎችም ታጅበው መጡና ወደ ፍርድ አዳራሽ ገቡ፤ ከዚያም በኋላ ፊስጦስ ጳውሎስን አስጠራ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 በነገውም አግሪጳና በርኒቄ በብዙ ግርማ መጥተው ከሻለቆችና ከከተማው ታላላቆች ጋር ወደ ፍርድ ቤት ገቡ፤ ፊስጦስም ባዘዘ ጊዜ ጳውሎስን አመጡት።

Ver Capítulo Cópia de




ሐዋርያት ሥራ 25:23
18 Referências Cruzadas  

ሰባ​ኪው፥ “ከንቱ፥ ከንቱ፥ የከ​ንቱ ከንቱ ሁሉ ከንቱ ነው” ይላል።


ከክ​ብ​ርህ ወደ ሲኦል ወደ​ቅህ፤ በበ​ታ​ች​ህም ብል ተነ​ጥ​ፎ​አል፤ ትልም መደ​ረ​ቢ​ያህ ሆኖ​አል” ብለው ይመ​ል​ሱ​ል​ሃል።


ሲኦ​ልም ሆድ​ዋን አስ​ፍ​ታ​ለች፤ አፍ​ዋ​ንም ያለ ልክ ከፍ​ታ​ለች፤ የተ​ከ​በ​ሩና ታላ​ላቅ ሰዎች ባለ​ጠ​ጎ​ቻ​ቸ​ውና ድሆ​ቻ​ቸ​ውም ወደ እር​ስዋ ይወ​ር​ዳሉ።


የግ​ብ​ፅን ቀን​በር በዚያ በሰ​በ​ርሁ ጊዜ በጣ​ፍ​ናስ ቀኑ ይጨ​ል​ማል፤ የኀ​ይ​ል​ዋም ትዕ​ቢት ይጠ​ፋ​ባ​ታል፤ ደመ​ናም ይጋ​ር​ዳ​ታል፤ ሴቶች ልጆ​ች​ዋም ይማ​ረ​ካሉ።


በኀ​ያ​ላን ሰይፍ ኀይ​ል​ህን እጥ​ላ​ለሁ፤ ሁሉ የአ​ሕ​ዛብ ጨካ​ኞች ናቸው፤ የግ​ብ​ፅ​ንም ትዕ​ቢት ያጠ​ፋሉ፤ ኀይ​ል​ዋም ሁሉ ይደ​መ​ሰ​ሳል።


ምድ​ሪ​ቱ​ንም ባድ​ማና ውድማ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ የኀ​ይ​ል​ዋም ስድብ ይቀ​ራል፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተራ​ሮች ባድማ ይሆ​ናሉ፤ ማንም አያ​ል​ፍ​ባ​ቸ​ውም።


ከአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ከሁሉ የሚ​ከ​ፉ​ትን አመ​ጣ​ለሁ፤ ቤታ​ቸ​ው​ንም ይወ​ር​ሳሉ፥ የኀ​ያ​ላ​ን​ንም ትዕ​ቢት አጠ​ፋ​ለሁ፤ መቅ​ደ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ይረ​ክ​ሳሉ።


ሄሮድስም በተወለደበት ቀን ለመኳንንቱና ለሻለቆቹ ለገሊላም ሹማምንት ግብር ባደረገ ጊዜ ምቹ ቀን ሆነላትና


ከዚ​ህም በኋላ አንድ ቀን ሄሮ​ድስ ልብሰ መን​ግ​ሥ​ቱን ለብሶ፥ በአ​ደ​ባ​ባይ ተገ​ኝቶ ይፈ​ርድ ጀመረ።


ከጥ​ቂት ቀን በኋ​ላም ንጉሥ አግ​ሪ​ጳና በር​ኒቄ ወደ ቂሣ​ርያ ወር​ደው ፊስ​ጦ​ስን ተገ​ና​ኙት።


ከዚ​ህም በኋላ ንጉሡ፥ ሀገረ ገዥ​ውም፥ በር​ኒ​ቄም፥ ሹሞ​ቻ​ቸ​ውም ተነሡ።


ጌታ​ች​ንም እን​ዲህ አለው፥ “ተነ​ሥና ሂድ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብና በነ​ገ​ሥ​ታት፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ፊት ስሜን ይሸ​ከም ዘንድ ለእኔ የተ​መ​ረጠ ዕቃ አድ​ር​ጌ​ዋ​ለ​ሁና።


የበሉ እን​ዳ​ል​በሉ ይሆ​ናሉ፤ የጠ​ጡም እን​ዳ​ል​ጠጡ ይሆ​ናሉ፤ የዚህ ዓለም ተድላ ሁሉ ያል​ፋ​ልና።


ፀሐይ ከትኵሳት ጋር ይወጣልና፥ ሣርንም ያጠወልጋልና፥ አበባውም ይረግፋልና፥ የመልኩም ውበት ይጠፋልና፤ እንዲሁ ደግሞ ባለ ጠጋው በመንገዱ ይዝላል።


“ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios