Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሐዋርያት ሥራ 22:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ሰማ​ዕ​ት​ህን እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስን በገ​ደ​ሉ​ትም ጊዜ እኔ እዚያ አብ​ሬ​አ​ቸው ነበ​ርሁ፤ የገ​ዳ​ዮ​ች​ንም ልብስ እጠ​ብቅ ነበር።’

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ደግሞም የአንተን ሰማዕት የእስጢፋኖስን ደም በሚያፈስሱበት ጊዜ፣ በድርጊታቸው ተስማምቼ በቦታው ቆሜ የገዳዮቹን ልብስ እጠብቅ ነበር።’

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 የሰማዕትህንም የእስጢፋኖስን ደም ባፈሰሱ ጊዜ፥ ራሴ ደግሞ በአጠገባቸው ስቆም ተስማምቼ የገዳዮችን ልብስ እጠብቅ ነበር፤’ አልሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 የአንተ ምስክር የነበረው እስጢፋኖስ በተገደለ ጊዜ እኔም ራሴ በገዳዮቹ አጠገብ ቆሜ ከእነርሱ ጋር በነገሩ ተስማምቼ ነበር፤ ልብሳቸውንም እጠብቅ ነበር፤’

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 የሰማዕትህንም የእስጢፋኖስን ደም ባፈሰሱ ጊዜ፥ ራሴ ደግሞ በአጠገባቸው ስቆም ተስማምቼ የገዳዮችን ልብስ እጠብቅ ነበር አልሁ።

Ver Capítulo Cópia de




ሐዋርያት ሥራ 22:20
8 Referências Cruzadas  

የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሥራ ደስ አሰ​ኝ​ቶ​አ​ች​ኋል፤ የም​ት​መ​ሰ​ክ​ሩ​ባ​ቸ​ውም እና​ንተ ራሳ​ችሁ ናችሁ፤ እነ​ርሱ የገ​ደ​ሉ​አ​ቸ​ውን መቃ​ብ​ራ​ቸ​ውን እና​ንተ ትሠ​ራ​ላ​ች​ሁና።


ይህ​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ረ​ግ​ሁት፤ ከሊ​ቃነ ካህ​ና​ትም ሥል​ጣን ተቀ​ብዬ ከቅ​ዱ​ሳን ብዙ​ዎ​ችን ወደ ወኅኒ ቤት አስ​ገ​ባ​ኋ​ቸው፤ ሲገ​ድ​ሏ​ቸ​ውም አብሬ እመ​ክር ነበ​ርሁ።


ይህም ነገር በእ​ነ​ርሱ ዘንድ የተ​ወ​ደደ ሆነ፤ ሃይ​ማ​ኖቱ የቀ​ናና መን​ፈስ ቅዱስ ያደ​ረ​በ​ትን ሰው እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስን፥ ፊል​ጶ​ስን፥ ጵሮ​ኮ​ሮ​ስን፥ ኒቃ​ሮ​ናን፥ ጢሞ​ናን፥ ጰር​ሜ​ናን፥ ወደ ይሁ​ዲ​ነት የተ​መ​ለ​ሰ​ውን የአ​ን​ጾ​ኪ​ያ​ውን ኒቆ​ላ​ዎ​ስ​ንም መረጡ።


ከከ​ተ​ማም ወደ ውጭ ጐት​ተው አው​ጥ​ተው ወገ​ሩት፤ የሚ​ወ​ግ​ሩት ሰዎ​ችም ልብ​ሳ​ቸ​ውን ሳውል በሚ​ባል ጐል​ማሳ እግር አጠ​ገብ አስ​ቀ​መጡ።


በዚያ ወራ​ትም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለ​ችው ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ላይ ታላቅ ስደት ሆነ፤ ከሐ​ዋ​ር​ያ​ትም በቀር ሁሉም በይ​ሁ​ዳና በሰ​ማ​ርያ ባሉ አው​ራ​ጃ​ዎች ሁሉ ተበ​ተኑ።


ይህን እን​ዲህ ላደ​ረገ ሞት እን​ደ​ሚ​ገ​ባው እነ​ርሱ ራሳ​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍርድ እያ​ወቁ፥ እነ​ርሱ ብቻ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉት አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ሌላ​ውን ያነ​ሣ​ሡ​ታል፤ ያሠ​ሩ​ታ​ልም።


ሴቲቱም በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት። ባየኋትም ጊዜ እጅግ ታላቅ ድንቅ አደነቅሁ።


“የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፤ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ ሃይማኖቴን አልካድህም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios