Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሐዋርያት ሥራ 19:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ብዙ​ዎች አስ​ማ​ተ​ኞ​ችም መጽ​ሐ​ፎ​ቻ​ቸ​ውን እየ​ሰ​በ​ሰቡ እያ​መጡ በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት በእ​ሳት ያቃ​ጥሉ ነበር፤ ያቃ​ጠ​ሏ​ቸው የመ​ጽ​ሐ​ፎች ዋጋም አምሳ ሺህ ብር ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ሲጠነቍሉ ከነበሩትም መካከል ብዙዎች መጽሐፋቸውን ሰብስበው በማምጣት በሕዝብ ፊት አቃጠሉ፤ ዋጋቸውም ሲሰላ ዐምሳ ሺሕ ብር ያህል ሆኖ ተገኘ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ከአስማተኞችም ብዙዎቹ መጽሐፋቸውን ሰብስበው በሰው ሁሉ ፊት አቃጠሉት፤ ዋጋውም ቢታሰብ አምሳ ሺህ ብር ሆኖ ተገኘ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ብዙ አስማተኞችም የአስማት መጽሐፎቻቸውን ሰብስበው በሕዝቡ ሁሉ ፊት አቃጠሉአቸው፤ የመጽሐፎቹ ዋጋ ሲተመን ኀምሳ ሺህ ጥሬ ብር ሆኖ ተገኘ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ከአስማተኞችም ብዙዎቹ መጽሐፋቸውን ሰብስበው በሰው ሁሉ ፊት አቃጠሉት፤ ዋጋውም ቢታሰብ አምሳ ሺህ ብር ሆኖ ተገኘ።

Ver Capítulo Cópia de




ሐዋርያት ሥራ 19:19
23 Referências Cruzadas  

በእ​ጃ​ቸው ያሉ​ት​ንም እን​ግ​ዶች አማ​ል​ክት ሁሉ፥ በጆ​ሮ​አ​ቸ​ውም ያሉ​ትን ጉት​ቾች ለያ​ዕ​ቆብ ሰጡት፤ ያዕ​ቆ​ብም በሴ​ቄም አጠ​ገብ ካለ​ችው ዛፍ በታች ቀበ​ራ​ቸው። እስከ ዛሬም ድረስ አጠ​ፋ​ቸው።


እን​ዲሁ ሳኦል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ስላ​ደ​ረ​ገው ኀጢ​አት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስላ​ል​ጠ​በቀ ሞተ። ደግ​ሞም መና​ፍ​ስት ጠሪን ጠየቀ።


በሄ​ኖ​ምም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ልጆ​ቹን በእ​ሳት አቃ​ጠለ፤ ሞራ ገላ​ጭም ሆነ፤ አስ​ማ​ትም አደ​ረገ። መተ​ተ​ኛም ነበረ፤ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ች​ንም ሰበ​ሰበ፤ ያስ​ቈ​ጣ​ውም ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጅግ ክፉ ነገ​ርን አደ​ረገ።


የሠ​ሩ​ት​ንም ጥጃ ወስዶ በእ​ሳት አቀ​ለ​ጠው፤ ፈጨው፤ አደ​ቀ​ቀ​ውም፤ በው​ኃም ላይ በተ​ነው፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አጠ​ጣ​ቸው።


ፈር​ዖ​ንም ጠቢ​ባ​ን​ንና መተ​ተ​ኞ​ችን ጠራ፤ የግ​ብ​ፅም ጠን​ቋ​ዮች በአ​ስ​ማ​ታ​ቸው እን​ዲሁ ደግሞ አደ​ረጉ።


የግ​ብ​ፅም ጠን​ቋ​ዮች በአ​ስ​ማ​ታ​ቸው እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ የፈ​ር​ዖን ልብ ጸና፤ አል​ሰ​ማ​ቸ​ው​ምም።


በብ​ርም ወደ ተለ​በጡ፥ በወ​ር​ቅም ወደ አጌጡ ወደ ጣዖ​ታቱ እን​ሂድ የሚሉ ናቸው፤ ያን​ጊዜ እንደ ትቢያ የደ​ቀቁ ይሆ​ናሉ፤ እንደ ውኃም ይደ​ፈ​ር​ሳሉ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ጥራ​ጊ​ዎ​ችን ይጥ​ሉ​ባ​ቸ​ዋል።


እነ​ር​ሱም፥ “ድም​ፃ​ቸ​ውን ዝቅ አድ​ር​ገው የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን ጠይቁ” ባሉ​አ​ችሁ ጊዜ፥ ሕዝቡ ከአ​ም​ላኩ መጠ​የቅ አይ​ገ​ባ​ው​ምን? ወይስ ለሕ​ያ​ዋን ሲሉ ሙታ​ንን ይጠ​ይ​ቃ​ሉን?


ልብ​ሱን ያቃ​ጥ​ላል፤ ድሩ ወይም ማጉ የበግ ጠጕር ወይም የተ​ልባ እግር ቢሆን ወይም ከቆዳ የተ​ደ​ረገ ቢሆን፥ ደዌ ያለ​በት ሁሉ እየ​ፋገ የሚ​ሄድ ለምጽ ነውና በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላል።


እን​ግ​ዲህ እን​ደ​ዚሁ ከእ​ና​ንተ ወገን ከሁሉ ያል​ወጣ፥ የእ​ርሱ ገን​ዘብ ከሆ​ነ​ውም ሁሉ ያል​ተ​ለየ ደቀ መዝ​ሙሬ ሊሆን አይ​ች​ልም።


“ዐሥር ድሪም ያላት ሴት ብት​ኖር፥ አን​ዲቱ ብት​ጠ​ፋ​ባት መብ​ራት አብ​ርታ በቤቷ ያለ​ውን ሁሉ እየ​ፈ​ነ​ቀ​ለች እስ​ክ​ታ​ገ​ኛት ድረስ ተግታ ትፈ​ልግ የለ​ምን?


በደ​ሴ​ቲ​ቱም ሁሉ ሲዘ​ዋ​ወሩ ጳፉ ወደ​ም​ት​ባል ሀገር ደረሱ፤ በዚ​ያም አንድ አይ​ሁ​ዳዊ የሆነ ሐሰ​ተኛ ነቢ​ይና አስ​ማ​ተኛ ሰው አገኙ፤ ስሙም በር​ያ​ሱስ ይባ​ላል።


አስ​ማ​ተ​ኛው ኤል​ማ​ስም የስሙ ትር​ጓሜ እን​ዲህ ነበ​ረና፥ ገዥ​ውን ከማ​መን ሊከ​ለ​ክ​ለው ፈልጎ ተቃ​ወ​ማ​ቸው።


ያመ​ኑ​ትም ሁሉ እየ​መጡ ስለ ሠሩት ንስሓ ይገቡ ነበር።


በእ​ስ​ራ​ቴም ጊዜ ከእኔ ጋር በመ​ከራ ተባ​ብ​ራ​ች​ኋል፤ የገ​ን​ዘ​ባ​ች​ሁ​ንም መዘ​ረፍ በደ​ስታ ተቀ​ብ​ላ​ች​ኋል፤ በሰ​ማ​ያት ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ኖር ከዚህ የሚ​በ​ል​ጥና የተ​ሻለ ገን​ዘብ እን​ዳ​ላ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios