Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሐዋርያት ሥራ 18:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ጌታ​ች​ንም ጳው​ሎ​ስን በሌ​ሊት ራእይ እን​ዲህ አለው፥ “አት​ፍራ፥ ነገር ግን ተና​ገር፥ ዝምም አት​በል፤

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ጌታም ሌሊት በራእይ ጳውሎስን እንዲህ አለው፤ “አትፍራ፤ ተናገር፣ ዝምም አትበል፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9-10 ጌታም ሌሊት በራእይ ጳውሎስን “እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ ማንም ክፉ ሊያደርግብህ የሚነሣብህ የለምና አትፍራ፤ ነገር ግን ተናገር፤ ዝምም አትበል፤ በዚህ ከተማ ብዙ ሕዝብ አሉኝና፤” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ጌታም ጳውሎስን ሌሊት በራእይ እንዲህ አለው፦ “አትፍራ፤ ተናገር፤ ዝም አትበል፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9-10 ጌታም ሌሊት በራእይ ጳውሎስን፦ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ ማንም ክፉ ሊያደርግብህ የሚነሣብህ የለምና አትፍራ፥ ነገር ግን ተናገር ዝምም አትበል፤ በዚህ ከተማ ብዙ ሕዝብ አሉኝና አለው።

Ver Capítulo Cópia de




ሐዋርያት ሥራ 18:9
17 Referências Cruzadas  

በኀ​ይ​ልህ ጩኽ፤ አት​ቈ​ጥብ፤ ድም​ፅ​ህን እንደ መለ​ከት አንሣ፤ ለሕ​ዝቤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን፥ ለያ​ዕ​ቆብ ቤትም በደ​ላ​ቸ​ውን ንገር።


አንተ ግን ወገ​ብ​ህን ታጠቅ፤ ተነ​ሥም፤ ያዘ​ዝ​ሁ​ህ​ንም ሁሉ ንገ​ራ​ቸው፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ አት​ፍራ። በፊ​ታ​ቸ​ውም አት​ደ​ን​ግጥ አድ​ንህ ዘንድ እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በጠ​ራ​ሁህ ቀን ወደ እኔ ቅረብ፤ “አት​ፍ​ራም” በለኝ።


“ተነ​ሥ​ተህ ወደ​ዚ​ያች ወደ ታላ​ቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ የነ​ገ​ር​ሁ​ህ​ንም የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውን ስብ​ከት ስበ​ክ​ላት” አለው።


እኔ ግን በደሉን ለያዕቆብ፥ ኃጢአቱንም ለእስራኤል እነግር ዘንድ በእግዚአብሔር መንፈስ ኃይልንና ፍርድን ብርታትንም ተሞልቻለሁ።


ለጳ​ው​ሎ​ስም በሌ​ሊት አንድ መቄ​ዶ​ናዊ ሰው ቁሞ፥ “ወደ እኛ ወደ መቄ​ዶ​ንያ ዕለ​ፍና ርዳን” እያለ ሲማ​ል​ደው በራ​እይ ተገ​ለ​ጸ​ለት።


እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና ማንም ሊጐ​ዳህ የሚ​ነ​ሣ​ብህ የለም፤ በዚች ከተማ ብዙ ሕዝብ አሉ​ኝና።”


‘ስለ እኔ የም​ት​መ​ሰ​ክ​ረ​ውን ምስ​ክ​ር​ነት አይ​ቀ​በ​ሉ​ህ​ምና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ፈጥ​ነህ ውጣ’ ሲለኝ አየ​ሁት።


በሁ​ለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ሌሊት ጌታ​ችን ለጳ​ው​ሎስ ተገ​ልጦ፥ “ጽና፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ምስ​ክር እንደ ሆን​ኸኝ እን​ዲሁ በሮም ምስ​ክር ትሆ​ነ​ኛ​ለህ” አለው።


በደ​ማ​ስ​ቆም ስሙን ሐና​ንያ የሚ​ሉት አንድ ደቀ መዝ​ሙር ነበር፤ ጌታም በራ​እይ ተገ​ልጦ፥ “ሐና​ንያ” ብሎ ጠራው፤ እር​ሱም፥ “አቤቱ፥ እነ​ሆኝ” አለ።


እኔ ነጻ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ሐዋ​ር​ያስ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ያየሁ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? እና​ን​ተስ በጌ​ታ​ችን ሥራዬ አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን?


ነገር ግን እንደምታውቁት በፊልጵስዩስ አስቀድመን መከራ ተቀብለን ተንገላትተንም፥ በብዙ ገድል የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ እንናገር ዘንድ በአምላካችን ደፈርን።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios