Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሐዋርያት ሥራ 17:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 እኛ በእ​ርሱ ሕይ​ወ​ትን እና​ገ​ኛ​ለን፤ በእ​ር​ሱም እን​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሳ​ለን፤ በእ​ር​ሱም ጸን​ተን እን​ኖ​ራ​ለን፤ ከመ​ካ​ከ​ላ​ች​ሁም፦ ‘እኛ ዘመ​ዶቹ ነን’ የሚሉ ፈላ​ስ​ፎች አሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 የምንኖረውና የምንንቀሳቀሰው፣ ያለነውም በርሱ ነውና። ከራሳችሁ ባለቅኔዎችም አንዳንዶቹ እንዳሉት፣ ‘እኛም ደግሞ ልጆቹ ነን።’

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ከእናንተ ከባለ ቅኔዎች አንዳንዶች ደግሞ ‘እኛ ደግሞ ዘመዶቹ ነንና፤’ ብለው እንደ ተናገሩ፥ በእርሱ ሕያዋን ነንና እንንቀሳቀሳለን፤ እንኖርማለን።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ‘ሕይወት የምናገኘውና የምንንቀሳቀሰው፥ የምንኖረውም በእርሱ ነው፤’ ይህም የእናንተ ባለ ቅኔዎች ‘እኛ ሁላችን የእርሱ ልጆች ነን’ እንዳሉት ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ከእናንተ ከባለ ቅኔዎች አንዳንዶች ደግሞ፦ እኛ ደግሞ ዘመዶቹ ነንና ብለው እንደ ተናገሩ፥ በእርሱ ሕያዋን ነንና እንንቀሳቀሳለን እንኖርማለን።

Ver Capítulo Cópia de




ሐዋርያት ሥራ 17:28
16 Referências Cruzadas  

የሕ​ያ​ዋን ሁሉ ነፍስ፥ የሰ​ውም ሁሉ መን​ፈስ በእጁ ናትና።


ክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎች ይጠ​ፋ​ሉና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ግን እነ​ርሱ ምድ​ርን ይወ​ር​ሳሉ።


ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ፥ “ይህ​ችን ነፍስ የፈ​ጠ​ረ​ልን ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! አል​ገ​ድ​ል​ህም፤ ነፍ​ስ​ህ​ንም ለሚሹ ለእ​ነ​ዚህ ሰዎች እጅ አሳ​ልፌ አል​ሰ​ጥ​ህም” ብሎ በቈ​ይታ ለኤ​ር​ም​ያስ ማለ።


እን​ኪ​ያስ የሕ​ያ​ዋን አም​ላክ እንጂ የሙ​ታን አም​ላክ አይ​ደ​ለም፤ ሁሉም በእ​ርሱ ዘንድ ሕያ​ዋን ናቸ​ውና።”


የሄ​ኖስ ልጅ፥ የሴት ልጅ፥ የአ​ዳም ልጅ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም አላት፥ “ትን​ሣ​ኤና ሕይ​ወት እኔ ነኝ፤ የሚ​ያ​ም​ን​ብኝ ቢሞ​ትም ይነ​ሣል።


ለአብ በራሱ ሕይ​ወት እን​ዳ​ለው፥ እን​ዲ​ሁም ደግሞ ለወ​ልድ በራሱ ሕይ​ወት እን​ዲ​ኖ​ረው ሰጠው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ባ​ቶ​ችህ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም እን​ዲ​ሰ​ጣ​ቸው በማ​ለ​ላ​ቸው በም​ድ​ሪቱ ትቀ​መጥ ዘንድ፥ እርሱ ሕይ​ወ​ትህ፥ የዘ​መ​ን​ህም ርዝ​መት ነውና አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ውደ​ደው፤ ቃሉን ስማው፤ አጥ​ና​ውም።”


እርሱ ከሁሉ አስ​ቀ​ድሞ ነበረ፤ ሁሉም በእ​ርሱ ጸና።


የገዛ ራሳቸው ነቢይ የሆነ ከእነርሱ አንዱ “የቀርጤስ ሰዎች ዘወትር ውሸተኞች፥ ክፉዎች አራዊት፥ በላተኞች፥ ሥራ ፈቶች ናቸው፤” ብሎአል።


እር​ሱም የክ​ብሩ መን​ጸ​ባ​ረ​ቅና የመ​ልኩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥ​ል​ጣኑ ቃል እየ​ደ​ገፈ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰ​ማ​ያት በግ​ር​ማው ቀኝ ተቀ​መጠ።


በሥጋ የወ​ለ​ዱን አባ​ቶ​ቻ​ችን የሚ​ቀ​ጡን፥ እኛም የም​ን​ፈ​ራ​ቸው ከሆነ፥ እን​ግ​ዲያ ይል​ቁን ለመ​ን​ፈስ አባ​ታ​ችን ልን​ታ​ዘ​ዝና ልን​ገዛ በሕ​ይ​ወ​ትም ልን​ኖር እን​ዴት ይገ​ባን ይሆን?


እነ​ር​ሱን የቀ​ደ​ሳ​ቸው እርሱ፥ የተ​ቀ​ደ​ሱት እነ​ር​ሱም ሁሉም በአ​ን​ድ​ነት ከአ​ንዱ ናቸ​ውና። ስለ​ዚ​ህም እነ​ር​ሱን፥ “ወን​ድ​ሞች” ማለ​ትን አያ​ፍ​ርም።


የሚ​ያ​ሳ​ድ​ድ​ህና ነፍ​ስ​ህን የሚሻ ሰው ቢነሣ፥ የጌ​ታዬ ነፍስ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በሕ​ይ​ወት ማሰ​ሪያ የታ​ሰ​ረች ትሆ​ና​ለች፤ የጠ​ላ​ቶ​ችህ ነፍስ ግን በወ​ን​ጭፍ እን​ደ​ሚ​ወ​ነ​ጨፍ ትሁን።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios