Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሐዋርያት ሥራ 16:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ጳው​ሎ​ስም ከእ​ርሱ ጋር ይዞት ሊሄድ ወደደ፤ በዚ​ያም ሀገር ስለ አሉት አይ​ሁድ ወስዶ ገረ​ዘው፤ አባቱ አረ​ማዊ እንደ ነበረ ሁሉም ያውቁ ነበ​ርና።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ጳውሎስም ይህ ሰው ከርሱ ጋራ እንዲሄድ ፈለገ፤ ስለዚህ በዚያ አካባቢ በነበሩ አይሁድ ምክንያት ይዞ ገረዘው፤ እነዚህ አይሁድ በሙሉ የጢሞቴዎስ አባት የግሪክ ሰው እንደ ሆነ ያውቁ ነበርና።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ጳውሎስ ይህ ከእርሱ ጋር ይወጣ ዘንድ ወደደ፤ በእነዚያም ስፍራዎች ስለ ነበሩ አይሁድ ይዞ ገረዘው፤ አባቱ የግሪክ ሰው እንደሆነ ሁሉ ያውቁ ነበርና።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ጳውሎስ ጢሞቴዎስን ይዞ መሄድ ስለ ፈለገ በዚያ ስፍራ በነበሩት አይሁድ ምክንያት እንዲገረዝ አደረገው፤ ይህንንም ያደረገው እነርሱ የጢሞቴዎስ አባት አረማዊ መሆኑን ያውቁ ስለ ነበረ ስለ እነርሱ ብሎ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ጳውሎስ ይህ ከእርሱ ጋር ይወጣ ዘንድ ወደደ፥ በእነዚያም ስፍራዎች ስለ ነበሩ አይሁድ ይዞ ገረዘው፤ አባቱ የግሪክ ሰው እንደ ሆነ ሁሉ ያውቁ ነበርና።

Ver Capítulo Cópia de




ሐዋርያት ሥራ 16:3
10 Referências Cruzadas  

ነገር ግን ለጣ​ዖት ከሚ​ሠ​ዋው፥ ከዝ​ሙት፥ ሞቶ የተ​ገ​ኘ​ው​ንና ደም ከመ​ብ​ላት እን​ዲ​ርቁ፥ ለራ​ሳ​ቸው የሚ​ጠ​ሉ​ት​ንም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ላይ እን​ዳ​ያ​ደ​ርጉ እዘ​ዙ​አ​ቸው።


በር​ና​ባ​ስም ማር​ቆስ የተ​ባ​ለ​ውን ዮሐ​ን​ስን ከእ​ነ​ርሱ ጋር ይዞት ሊሄድ ወደደ።


ጳው​ሎስ ግን ሲላ​ስን መረጠ፤ ወን​ድ​ሞ​ችም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አደራ ከሰ​ጡት በኋላ ሄደ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ መጠ​በቅ ነው እንጂ መገ​ዘ​ርም አይ​ጠ​ቅ​ምም፤ አለ​መ​ገ​ዘ​ርም አይ​ጎ​ዳም።


አይ​ሁ​ድን እጠ​ቅ​ማ​ቸው ዘንድ ለአ​ይ​ሁድ እንደ አይ​ሁ​ዳዊ ሆን​ሁ​ላ​ቸው፤ ከኦ​ሪት በታች ያሉ​ትን እጠ​ቅም ዘንድ እኔ ራሴ ከኦ​ሪት በታች ሳል​ሆን ከኦ​ሪት በታች ላሉት ከኦ​ሪት በታች እን​ዳለ ሰው ሆን​ሁ​ላ​ቸው።


አብ​ሮኝ የነ​በ​ረው ቲቶም አረ​ማዊ ሲሆን እን​ዲ​ገ​ዘር ግድ አላ​ል​ሁ​ትም።


ወደ ተገ​ዘሩ አይ​ሁድ በተ​ላከ ጊዜ ጴጥ​ሮ​ስን የረ​ዳው እርሱ እኔ​ንም ባል​ተ​ገ​ዘሩ አሕ​ዛብ ዘንድ ረዳኝ።


በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘንድ በፍ​ቅር የም​ት​ሠራ እም​ነት እንጂ መገ​ዘር አይ​ጠ​ቅ​ም​ምና፤ አለ​መ​ገ​ዘ​ርም ግዳጅ አይ​ፈ​ጽ​ም​ምና።


ልጅ አባ​ቱን እን​ደ​ሚ​ያ​ገ​ለ​ግል፥ በወ​ን​ጌል ትም​ህ​ርት እንደ አገ​ለ​ገ​ለኝ፥ የዚ​ህን ሰው ጠባ​ዩን ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios