Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሐዋርያት ሥራ 15:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አት​ፈ​ታ​ተ​ኑት፤ እኛም አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ልን​ሸ​ከ​መው ያል​ቻ​ል​ነ​ውን ቀን​በር በደቀ መዛ​ሙ​ርት ጫንቃ ላይ ለምን ትጭ​ና​ላ​ችሁ?

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እንግዲህ፣ አባቶቻችንም እኛም ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን ለምን አሁን እግዚአብሔርን ትፈታተኑታላችሁ?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እንግዲህ አባቶቻችንና እኛ ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን እግዚአብሔርን አሁን ስለምን ትፈታተናላችሁ?

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ታዲያ፥ አባቶቻችንም ሆኑ እኛ ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በአማኞች ጫንቃ ላይ በመጫን ለምን አሁን እግዚአብሔርን ትፈታተኑታላችሁ?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እንግዲህ አባቶቻችንና እኛ ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን እግዚአብሔርን አሁን ስለ ምን ትፈታተናላችሁ?

Ver Capítulo Cópia de




ሐዋርያት ሥራ 15:10
11 Referências Cruzadas  

ሕዝ​ቡም ሙሴን ተጣ​ሉት፥ “የም​ን​ጠ​ጣ​ውን ውኃ ስጠን” አሉ። ሙሴም፥ “ለምን ትጣ​ሉ​ኛ​ላ​ችሁ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንስ ለምን ትፈ​ታ​ተ​ና​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው።


አካ​ዝም፥ “አል​ለ​ም​ንም፤ አም​ላኬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ፈ​ታ​ተ​ንም” አለ።


ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ፤ እነርሱ ግን በጣታቸው ስንኳ ሊነኩት አይወዱም።


ኢየሱስም “ ‘ጌታን አምላክህን አትፈታተነው’ ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል” አለው።


ጴጥ​ሮ​ስም፥ “እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ፈስ ትፈ​ታ​ተ​ኑት ዘንድ እን​ዴት ተባ​በ​ራ​ችሁ? እነሆ፥ ባል​ሽን የቀ​በ​ሩት ሰዎች እግ​ሮች በበር ናቸው፤ አን​ቺ​ንም ይወ​ስ​ዱ​ሻል” አላት።


ዛሬ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዐወ​ቃ​ች​ሁት፤ ይል​ቁ​ንም እርሱ ዐወ​ቃ​ችሁ፤ እንደ ገና ደግሞ ወደ​ዚያ ወደ ደካ​ማው፥ ወደ ድሀው ወደ​ዚህ ዓለም ጣዖት ተመ​ል​ሳ​ችሁ፥ ትገ​ዙ​ላ​ቸው ዘንድ እን​ዴት ፈጠ​ራን ትሻ​ላ​ችሁ?


እን​ግ​ዲህ ጸን​ታ​ችሁ ቁሙ፤ እንደ ገናም በባ​ር​ነት ቀን​በር አት​ኑሩ።


የተ​ፈ​ታ​ተ​ኑኝ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ፈተ​ኑኝ፤ አርባ ዘመ​ንም ሥራ​ዬን አዩ።


ነገር ግን ለሚ​ያ​ቀ​ር​በው ሰው ግዳጅ መፈ​ጸም የማ​ይ​ቻ​ለ​ውን መባና መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ቡ​በት የነ​በ​ረው ለዚህ ዘመን ምሳሌ ሆነ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios