Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሐዋርያት ሥራ 14:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ከበ​ቡት፤ ነገር ግን ተነ​ሥቶ አብ​ሮ​አ​ቸው ወደ ከተማ ገባ፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም ከበ​ር​ና​ባስ ጋር ወደ ደር​ቤን ሄደ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ሆኖም ደቀ መዛሙርት ከብበውት እንዳሉ ተነሣ፤ ወደ ከተማም ገባ። በማግስቱም ከበርናባስ ጋራ ወደ ደርቤን ሄዱ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ደቀ መዛሙርት ግን ከበውት ሳሉ፥ ተነሥቶ ወደ ከተማ ገባ። በነገውም ከበርናባስ ጋር ወደ ደርቤን ወጣ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ነገር ግን ደቀ መዛሙርቱ መጥተው በዙሪያው በቆሙ ጊዜ ጳውሎስ ተነሣና ወደ ከተማ ገባ፤ በማግስቱም ከበርናባስ ጋር ወደ ደርቤ ሄደ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ደቀ መዛሙርት ግን ከበውት ሳሉ፥ ተነስቶ ወደ ከተማ ገባ። በነገውም ከበርናባስ ጋር ወደ ደርቤን ወጣ።

Ver Capítulo Cópia de




ሐዋርያት ሥራ 14:20
13 Referências Cruzadas  

በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም አንድ ዓመት አብ​ረው ተቀ​መጡ፤ ብዙ ሕዝ​ብ​ንም አስ​ተ​ማሩ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም መጀ​መ​ሪያ በአ​ን​ጾ​ኪያ ክር​ስ​ቲ​ያን ተብ​ለው ተጠሩ።


ከዚ​ህም በኋላ ደቀ መዛ​ሙ​ርት እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው የሚ​ች​ሉ​ትን ያህል አወ​ጣ​ጥ​ተው በይ​ሁዳ ሀገር ለሚ​ኖ​ሩት ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ርዳ​ታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ።


እርሱ ግን ዝም እን​ዲሉ በእጁ አመ​ለ​ከ​ታ​ቸው፤ ከወ​ኅኒ ቤትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አወ​ጣው ነገ​ራ​ቸው፤ “ይህ​ንም ለያ​ዕ​ቆ​ብና ለወ​ን​ድ​ሞች ሁሉ ንገሩ” አላ​ቸው፤ ከዚ​ያም ወጥቶ ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ።


የደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ንም ልቡና አጽ​ናኑ፤ በሃ​ይ​ማ​ኖ​ትም እን​ዲ​ጸኑ፦“ በብዙ ድካ​ምና መከራ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እን​ገባ ዘንድ ይገ​ባ​ናል” እያሉ መከ​ሩ​አ​ቸው።


ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም ጋር አያሌ ቀን ተቀ​መጡ።


ሐዋ​ር​ያ​ትም ይህን ዐው​ቀው ወደ ሊቃ​ኦ​ንያ ከተ​ሞች ወደ ልስ​ጥ​ራ​ንና ወደ ደር​ቤን፥ ወደ​የ​አ​ው​ራ​ጃ​ውም ሸሹ።


ወደ ደር​ቤ​ንና ወደ ልስ​ጥ​ራን ከተ​ማም ደረሰ፤ እነ​ሆም፥ በዚያ የአ​ን​ዲት ያመ​ነች አይ​ሁ​ዳ​ዊት ልጅ ጢሞ​ቴ​ዎስ የሚ​ባል አንድ ደቀ መዝ​ሙር ነበር፤ አባቱ ግን አረ​ማዊ ነበረ።


ከወ​ኅኒ ቤቱም ከወጡ በኋላ ወደ ልድያ ቤት ገብ​ተው ወን​ድ​ሞ​ችን አገኙ፤ አጽ​ና​ን​ተ​ዋ​ቸ​ውም ሔዱ።


ክር​ክ​ሩም ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ ጳው​ሎስ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን ጠራና አጽ​ና​ና​ቸው፤ ተሰ​ና​በ​ታ​ቸ​ውም፤ ወጥ​ቶም ወደ መቄ​ዶ​ንያ ሄደ።


እን​ደ​ማ​ይ​ታ​ወቁ ስን​ታይ የታ​ወ​ቅን ነን፤ እንደ ሰነ​ፎች ስን​ታ​ይም ልባ​ሞች ነን፤ እንደ ሙታን ስን​ታይ ሕያ​ዋን ነን፤ የተ​ቀ​ጣን ስን​ሆ​ንም አን​ገ​ደ​ልም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios