Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሐዋርያት ሥራ 10:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ጴጥ​ሮ​ስም ስለ አየው ራእይ ምን እንደ ሆነ ሲያ​ወ​ጣና ሲያ​ወ​ርድ ከቆ​ር​ኔ​ሌ​ዎስ ተል​ከው የመጡ ሰዎች የስ​ም​ዖ​ንን ቤት እየ​ጠ​የቁ በደጅ ቁመው ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ጴጥሮስም ስላየው ራእይ ትርጕም እጅግ ተጨንቆ በማሰላሰል ላይ ሳለ፣ ቆርኔሌዎስ የላካቸው ሰዎች የስምዖንን ቤት ፈልገው ካገኙ በኋላ መጥተው በሩ ላይ ቆሙ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ጴጥሮስም ስላየው ራእይ “ምን ይሆን?” ብሎ በልቡ ሲያመነታ፥ እነሆ፥ ቆርኔሌዎስ የላካቸው ሰዎች ስለ ስምዖን ቤት ጠይቀው ወደ ደጁ ቀረቡ፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ጴጥሮስ የራእዩ ፍች “ምን ይሆን?” እያለ በሐሳቡ ሲጨነቅ ቆርኔሌዎስ የላካቸው ሰዎች በጥያቄ የስምዖንን ቤት አግኝተው በበር ቆመው ነበር፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ጴጥሮስም ስላየው ራእይ፦ “ምን ይሆን?” ብሎ በልቡ ሲያመነታ፥ እነሆ፥ ቆርኔሌዎስ የላካቸው ሰዎች ስለ ስምዖን ቤት ጠይቀው ወደ ደጁ ቀረቡ፤

Ver Capítulo Cópia de




ሐዋርያት ሥራ 10:17
9 Referências Cruzadas  

እግ​ራ​ቸ​ው​ንም ካጠ​ባ​ቸው በኋላ ልብ​ሱን አን​ሥቶ ለበ​ሰና እንደ ገና ከእ​ነ​ርሱ ጋር ተቀ​መጠ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ያደ​ረ​ግ​ሁ​ላ​ች​ሁን ዐወ​ቃ​ች​ሁን?


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም በራ​እይ ከቀኑ በዘ​ጠኝ ሰዓት በግ​ልጥ ታየው፤ ወደ እር​ሱም ገብቶ፥ “ቆር​ኔ​ሌ​ዎስ ሆይ፥” አለው።


ሁሉም ተገ​ረሙ፤ የሚ​ሉ​ት​ንም አጡ፥ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “እንጃ! ይህ ነገር ምን ይሆን?” ተባ​ባሉ።


ስለ ክር​ክ​ራ​ቸ​ውም የማ​ደ​ር​ገ​ውን አጥቼ ጳው​ሎ​ስን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሄደህ በዚያ ልት​ከ​ራ​ከር ትወ​ዳ​ለ​ህን? አል​ሁት።


ሊቃነ ካህ​ና​ትና የቤተ መቅ​ደሱ ሹምም ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ፥ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን አጥ​ተው፥ “እንጃ ይህ ምን ይሆን?” አሉ።


በደ​ማ​ስ​ቆም ስሙን ሐና​ንያ የሚ​ሉት አንድ ደቀ መዝ​ሙር ነበር፤ ጌታም በራ​እይ ተገ​ልጦ፥ “ሐና​ንያ” ብሎ ጠራው፤ እር​ሱም፥ “አቤቱ፥ እነ​ሆኝ” አለ።


ጴጥ​ሮ​ስም በኢ​ዮጴ በቍ​ር​በት ፋቂው በስ​ም​ዖን ቤት ብዙ ቀን ተቀ​መጠ።


በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ፥ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ እየመሰከረ፥ በምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios