Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ሳሙኤል 5:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ አድ​ርጎ እን​ዳ​ዘ​ጋ​ጀው፥ ስለ ሕዝቡ ስለ እስ​ራ​ኤ​ልም መን​ግ​ሥ​ቱን ከፍ እን​ዳ​ደ​ረገ ዐወቀ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ዳዊትም እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ንጉሥነቱን እንዳጸናለት፣ ስለ ሕዝቡ ስለ እስራኤልም ሲል መንግሥቱን ከፍ ከፍ እንዳደረገለት ተገነዘበ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ጌታ በእስራኤል ላይ ንጉሥነቱን እንዳጸናለት፥ ስለ ሕዝቡም ስለ እስራኤል መንግሥቱን እንዳሰፋለት ዳዊት ዐወቀ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ዳዊትም እግዚአብሔር የእስራኤል ንጉሥ አድርጎ እንዳጸናውና ለሕዝቡም ሲል መንግሥቱን ከፍ እንዳደረገለት ተገነዘበ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ዳዊትም እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ እንዳጸናው፥ ስለ ሕዝቡ ስለ እስራኤልም መንግሥቱን ከፍ እንዳደረገ አወቀ።

Ver Capítulo Cópia de




2 ሳሙኤል 5:12
10 Referências Cruzadas  

የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራም ወደ ዳዊት መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን፥ የዝ​ግባ እን​ጨ​ት​ንም፥ አና​ጢ​ዎ​ች​ንም፥ ድን​ጋይ ጠራ​ቢ​ዎ​ች​ንም ላከ፤ ለዳ​ዊ​ትም ቤት ሠሩ​ለት።


ዳዊ​ትም ከኬ​ብ​ሮን ከመጣ በኋላ እንደ ገና ቁባ​ቶ​ቹ​ንና ሚስ​ቶ​ቹን ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወሰደ፤ ለዳ​ዊ​ትም ደግሞ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት።


ቤቱ የታ​መነ ይሆ​ናል፤ መን​ግ​ሥ​ቱም በፊቴ ለዘ​ለ​ዓ​ለም፥ ዙፋ​ኑም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጸ​ናል።”


አን​ተን በእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን ያስ​ቀ​ም​ጥህ ዘንድ የወ​ደደ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ሰ​ገነ ይሁን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ራ​ኤ​ልን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያጸ​ናው ዘንድ ወድ​ዶ​ታ​ልና ስለ​ዚህ በየ​ነ​ገ​ራ​ቸው ጽድ​ቅና ፍርድ ታደ​ርግ ዘንድ በላ​ያ​ቸው አነ​ገ​ሠህ።”


ስለ ሕዝ​ቡም ስለ እስ​ራ​ኤል፥ መን​ግ​ሥቱ እጅግ ከፍ ብሎ​አ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ እን​ዲ​ሆን እን​ዳ​ዘ​ጋ​ጀው ዳዊት ዐወቀ።


የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራ​ምም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ወድ​ዶ​አ​ልና በላ​ያ​ቸው አነ​ገ​ሠህ” ሲል ለሰ​ሎ​ሞን ጻፈ​ለት።


ከዘሩ ሰው ይወ​ጣል፤ ብዙ ሕዝ​ብ​ንም ይገ​ዛል፥ መን​ግ​ሥ​ቱም ከአ​ጋግ ይልቅ ከፍ ከፍ ትላ​ለች፥ መን​ግ​ሥ​ቱም ትሰ​ፋ​ለች።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios