Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ሳሙኤል 23:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የዳ​ዊት ኀያ​ላን ስም ይህ ነው። የሦ​ስ​ተ​ኛው ክፍል አለቃ የሆነ ከነ​ዓ​ና​ዊው ኢያ​ቡ​ስቴ ነበረ፤ ጎራ​ዴ​ውን መዝዞ ስም​ንት መቶ ያህል ጭፍ​ሮ​ችን በአ​ንድ ጊዜ የገ​ደለ አሶ​ና​ዊው አዲ​ኖን ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የዳዊት ኀያላን ሰዎች ስም ይህ ነው፤ የታሕክሞን ሰው ዮሴብ በሴትቤት የሦስቱ አለቆች አለቃ ሲሆን፣ እርሱም ጦሩን ሰብቆ በአንድ ውጊያ ላይ ስምንት መቶ ሰው የገደለ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የዳዊት ኀያላን ሰዎች ስም የሚከተለው ነው፤ የታሕክሞን ሰው ዮሼብ ባሼቤት የሦስቱ አለቆች አለቃ ሲሆን፥ እርሱም ጦሩን ሰብቆ በአንድ ውጊያ ላይ ስምንት መቶ ሰው በአንዴ የገደለ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ዝነኞች የሆኑት የዳዊት ወታደሮች ስም ዝርዝር ከዚህ በታች እንደ ተመለከተው ነው፤ የመጀመሪያው የታሕክሞን ተወላጅ ዮሼብ ባሼቤት የተባለው ሲሆን እርሱም ከሦስቱ ኀያላን ብልጫ ያለው ተቀዳሚ ነው፤ ይህ ሰው በአንድ ውጊያ ላይ ጦሩን አንሥቶ ስምንት መቶ ኀያላን ሰዎችን ገደለ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የዳዊት ኃያላን ስም ይህ ነው። የአለቆች አለቃ የሆነ ከነዓናዊው ኢያቡስቴ ነበረ፥ እርሱም ጦሩን አንሥቶ ስምንት መቶ ያህል በአንድ ጊዜ ገደለ።

Ver Capítulo Cópia de




2 ሳሙኤል 23:8
8 Referências Cruzadas  

ዳዊ​ትም በሰማ ጊዜ ኢዮ​አ​ብ​ንና የኀ​ያ​ላ​ኑን ሰራ​ዊት ሁሉ ላከ።


ነገር ግን ካህኑ ሳዶ​ቅና የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ ነቢ​ዩም ናታን፥ ሳሚም፥ ሬሲም፥ የዳ​ዊ​ትም ኀያ​ላን አዶ​ን​ያ​ስን አል​ተ​ከ​ተ​ሉም ነበር።


ለዳ​ዊ​ትም የነ​በ​ሩት ኀያ​ላን አለ​ቆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ስለ እስ​ራ​ኤል እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ያነ​ግ​ሡት ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ጋር በመ​ን​ግ​ሥቱ አጸ​ኑት።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆ​ችና የሺህ አለ​ቆች፥ የመቶ አለ​ቆ​ችም ለን​ጉ​ሡና ለን​ጉሡ ትእ​ዛዝ ሁሉ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ሹማ​ምት እንደ ቍጥ​ራ​ቸው በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸው እነ​ዚህ ነበሩ። እነ​ዚ​ህም ክፍ​ሎች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ሃያ አራት ሺህ ሆነው በዓ​መቱ ወራት ሁሉ በየ​ወሩ ይገ​ቡና ይወጡ ነበር።


ለመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በአ​ን​ደ​ኛው ክፍል ላይ የዘ​ብ​ድ​ኤል ልጅ ያሶ​ብ​አም ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።


አስ​ተ​ዋ​ይና ጸሓፊ የነ​በ​ረው በአ​ባቱ በኩል የዳ​ዊት አጎት ዮና​ታን አማ​ካሪ ነበረ፤ የአ​ክ​ማ​ኔም ልጅ ኢያ​ሔ​ኤል ከን​ጉሡ ልጆች ጋር ነበረ፤


የወ​ደቀ የአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ን​ት​ንም በመ​ን​ገድ አገኘ። እጁ​ንም ዘር​ግቶ ወሰ​ደው፤ በእ​ር​ሱም አንድ ሺህ ሰው ገደለ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios