Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ሳሙኤል 23:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ዳዊ​ትም፥ “በበሩ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ማን ባጠ​ጣኝ?” ብሎ ተመኘ። ያን​ጊ​ዜም የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ኀይል በቤተ ልሔም ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ዳዊትም በናፍቆት፣ “በቤተ ልሔም በር አጠገብ ካለችው ጕድጓድ ውሃ ማን ባመጣልኝ!” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ዳዊትም በናፍቆት፥ “በበሩ አጠገብ ካለችው ከቤተልሔም ጉድጓድ ውሃ ማን ባመጣልኝ!” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ዳዊትም አገሩን በመናፈቅ “በቤተልሔም ቅጽር በር አጠገብ ካለው የውሃ ጒድጓድ የምጠጣው ውሃ የሚያመጣልኝ ሰው ምነው ባገኘሁ!” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ዳዊትም፦ በበሩ አጠገብ ካለችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ማን ባጠጣኝ? ብሎ ተመኘ።

Ver Capítulo Cópia de




2 ሳሙኤል 23:15
12 Referências Cruzadas  

ራሔ​ልም ሞተች፤ ወደ ኤፍ​ራ​ታም በም​ት​ወ​ስድ መን​ገድ ተቀ​በ​ረች፤ እር​ስ​ዋም ቤተ ልሔም ናት።


ሦስ​ቱም ኀያ​ላን የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ሠራ​ዊት ሰን​ጥ​ቀው ሄዱ፤ በበ​ሩም አጠ​ገብ ካለ​ችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ቀዱ፤ ይዘ​ውም ለዳ​ዊት አመ​ጡ​ለት፤ እርሱ ግን ሊጠጣ አል​ወ​ደ​ደም፤ ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፈ​ሰ​ሰው።


ዳዊ​ትም፥ “በበሩ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ማን ይሰ​ጠ​ኛል?” ብሎ ተመኘ።


አቤቱ፥ ወደ አንተ የለ​መ​ን​ሁ​ትን ጸሎ​ቴን ስማኝ፥ ከጠ​ላ​ትም ጥር​ጥር ነፍ​ሴን አድ​ናት።


ድሆ​ችና ምስ​ኪ​ኖች ውኃ ይሻሉ፤ አያ​ገ​ኙ​ምም፤ ምላ​ሳ​ቸ​ውም በጥ​ማት ደር​ቋል፤ እኔ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሰ​ማ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እኔ አል​ተ​ዋ​ቸ​ውም።


በደ​ረቅ መሬት ላይ ለሚ​ሄ​ድና ለተ​ጠማ ውኃን እሰ​ጣ​ለሁ፤ መን​ፈ​ሴን በዘ​ርህ ላይ፥ በረ​ከ​ቴ​ንም በል​ጆ​ችህ ላይ አኖ​ራ​ለሁ፤


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስጦ​ታና ውኃ አጠ​ጪኝ ብሎ የሚ​ለ​ም​ንሽ ማን እንደ ሆነ ብታ​ው​ቂስ አንቺ ደግሞ በለ​መ​ን​ሺው ነበር፤ እር​ሱም የሕ​ይ​ወ​ትን ውኃ በሰ​ጠሽ ነበር” ብሎ መለ​ሰ​ላት።


እኔ ከም​ሰ​ጠው ውኃ የሚ​ጠጣ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ጠ​ማም፤ እኔ የም​ሰ​ጠው ውኃ በው​ስጡ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት የሚ​ፈ​ልቅ የውኃ ምንጭ ይሆ​ን​ለ​ታል እንጂ።”


በኋ​ለ​ኛ​ዪቱ በታ​ላ​ቅዋ የበ​ዓል ቀንም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ቆመና ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ እን​ዲህ አለ፥ “የተ​ጠማ ወደ እኔ ይም​ጣና ይጠጣ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios